Wednesday, March 15, 2017

የዋልድባው አባት ለእስር ያበቃቸው ቃለ ምልልስ

የዋልድባውን አባት ለእስር ያበቃው ቃለ ምልልስ ከVOA ጋር Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Tuesday, March 14, 2017

ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የዋልድባውን መነኩሴ የአባ ገብረ ኢየሱስን በመንግሥት ታጣቂዎች መታፈን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መጋቢት  ፭ ቀን ፪፻፱ ዓ ም
ቁጥር 20170311045
ጉዳዩ ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የዋልድባውን መነኩሴ የአባ ገብረ ኢየሱስን በመንግሥት ታጣቂዎች መታፈን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
“. . . እንግዲህ አትፍሩአቸው የማይገለጥ የተከደነ፣ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሀነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። . . .” ማቴዎስ ፲ ከ፳፮ - ፳፰

Tuesday, February 28, 2017

Monday, February 20, 2017

እንኳን ለታላቁ ለዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ


እንኳን ለታላቁ ለዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ በማለት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች እየተመኘ፥ መጪው የጾም ወራት

ሃጢዓት       ⍆      የሚጠፋበት

ጽድቅ          ⍆      የሚነግስበት

ሥጋ             ⍆      የሚደክምበት

ነፍስ           ⍆      የምትጠገንበት

መለያየት     ⍆     የሌለበት

ፍቅር          ⍆     የሚታይበት

ሕወታችን    ⍆      የሚትታነጽበት


ከፈጣሪ       ⍆     ይቅርታን የምናገኝበት የጾም ወራት እንዲሆን እንመኛለን


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, February 5, 2017

እንኳን ለነነዌ ጾም በሰላም አደረሳችሁ
በመጪው ሰኞ የሚጀመረው የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተ ክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡ ይህ የነነዌ ሰዎች የንስሐ ታሪክ በቤተ ክርስቲያናችን በጣም ታላቅ ዋጋ ያለውና የራሱ መዝሙር የሚዘመርለት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት ታላቅ መታሰቢያ ያለው ታሪክ ነው፡፡ ራሱ ጌታችንም የነነዌ ሰዎችን የንስሐ ታሪክ በመጥቀስ አይሁድን ገስጾበታል፤ በፍርድ ቀንም በዚያ ትውልድ ዘንድ እንደሚፈርዱበት ተናግሯል፡፡ ይህም የሆነበት የነነዌ ሰዎች ደስ የሚያሰኝ የንስሐ ታሪክ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ይህን አስደሳች የንስሐ ታሪክ በጾመ ነነዌ ከሚነበቡ የቅዳሴ ምንባባት አንጻር ለመመርመር እንሞከራለን፡፡ 

Monday, January 23, 2017

የዋልድባ ቅን አምባ ኪዳነ ምሕረት የደናግላን ገዳም በፌደራል ወታደሮች ቤተመቅደሱ ተመዘበረ

Related image


በሰሜን ጎንደር ዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገኘው የዋልድባ ቅን አምባ ኪዳነ ምሕረት የደናግላን ገዳም ትላንት ረፋዱ ላይ በፌደራል ወታደሮች መወረሩን የአካባቢው የዓይም ምሥክሮች የደረሰውን ውዝግብ እና የመንግሥት ወታደሮች በሃይማኖታችን ላይ እያደረሱት ያሉትን መጠነ ሰፊ የሆነ ምዝበራ እና ቤተመቅደስ የማዋረድ ሥራቸውን እግዚአብሔር እንዲያስታግስልን ምዕመናን በጸሎት እንዲያግዙን ብለው መልዕክታቸውን አስተላልፈውልናል።

Thursday, January 19, 2017

እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
 እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ በማለት ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልካም ምኞቻችንን እንገልጻለን  
ጥር ፲፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+
ቃና ዘገሊላ+
+'
ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ) የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው::
ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም::
+
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት
መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::
+
ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን ቻይ' እያልን የምንጠራው::