ልብ ያለው ልብ ይበል!
መቅሰፍት ፩ ጀምሯል! መንግስት "ቅዱሱን ገዳም አንነካውም" በማለት ሥራውን ቀጥሏል፥ ነገስ ምን እንደሚመጣ እናውቃለን?
![]() |
አቤቱ የሆነብንን ሁሉ አስብ |
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 1 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ ላይ የሚሰራው ስኳር ፋብሪካ ውዝግቡ ያለ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው ፤ መንግስት አልደረስኩም በማለት ስራውን እያከናወነ ይገኛል፤ አባቶችም በጸሎት እየበረቱ ይገኛሉ ፤ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት በቦታው ላይ ያለው ስራውን የሚያከናውን ተቀጣሪ መሃንዲስ ባልታወቀ ምክንያት ሞቷል ፣ ስው ለመስራት የተቀመጡ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎቹ በየሰአቱ እየተበላሹ ይገኛሉ ፣ ካልታወቀ ቦታ የተለያዩ አውሬዎች እየወጡ ሰራተኛውን መተናኮል ጀምረዋል ፣እነዚህን እና የመሳሰሉት መከራዎች በቦታው በስራ ላይ በስራ በሚገኙ ሰዎች ላይ እየደረሰ ነው፡፡
¨ሰው ሲጨርስ ባለቤቱ ስራ ይጀምራል¨ መዝሙረ ዳዊት 12፤4 ‹‹እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋም›› ተብሎ ተፅፏል ፤ እውነት ነው አምላካችን አያንቀላፋም ፤ ይህ ምልክት የመጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም ፤ አሁንም ከእኩይ ምግባራችሁ ትመለሱ ዘንድ መልዕክታችን ነው ፤ የዘመናችሁ መጨረሻ መጀመሪያ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፤12 ‹‹ ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ›› ቤተክርስትያን ላይ እጁን አንስቶ በሰላም የኖረ ስልጣነ መንግስቱ የተደላደለለት መንግስት ባለፉት 2000 ዓመታት አላየንም ፤ መልካቸው እየቀያየሩ ብዙዎች ተነስተውባታል ፤ የተነሱባት ሁሉ አሁን ስም አጠራራቸው የለም እሷ ግን አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች ፤ ይህች ቅድስት ቤተክርስትያን ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማቴዎስ ወንጌል 18 ፤18 ‹‹ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።›› ብሎ ተናግሮላታል ፤ ወደፊት የሚከሰተውን እየተከታተልን እናንተው ዘንድ እናደርሳለን
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ መልሳችንን በቅርቡ ይጠብቁን፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤