የዋልድባ እንታደግ ዓለም አቀፍ ንዑስ ኮሚቴ የሳን ሆዜ ብራንች ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደብዳቤ ላከ
ዋልድባን ለመታደግ ከተቋቋመው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ የሳን ሆዜ ንዕስ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ የአቋም መግለጫ ፳፩ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ልከዋል። የሳንሆዜ ንዕስ ኮሚቴ በዚሁ በተጠቀሰው ቀን በሳንሆዜ እና ኦክላንድ ተዋሪዎችን ስብሰባ ጠርቶ መጠነ ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ማዘጋጀቱ ይታወሳል በዚሁ ዕለትም ለበርካታ የሁለቱ ከተማ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ሰበብ እያደረሰ ያለውን የሃይማኖት ማጥፋት እና የድንበር መጋፋት በሃይማኖታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ እና ክብር ያለው የዋልድባ ገዳም መነካቱ (መደፈሩ) በእጅጉ የከተማውን ነዋሪዎች እንዳስቆጣና ለዚህም ደግሞ መንግሥት ከሃላፊነት እንደማያመልጥ ጠቁመዋል። የሁለቱ ከተማ ነዋሪች እየተሰራ ያለውን የስኳር ልማት ፕሮጀክት በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል።
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ መልሳችንን በቅርቡ ይጠብቁን፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤