![]() |
የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት ይደርብን |
ዛሬ ረፋዱ ላይ አንድ ማንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ባለሥልጣን፣ የሥኳር ፋብሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አማናይ መስፍን የሥኳር ፋብሪካው ፕሮጀክት የበላይ ተቆጣጣሪ እንዲሁም ጥቂት የአካባቢው የመንግሥት ሹማምንት በተገኙበት በወልቃይት ወረዳ ማይገባ ከተማ ላይ ወደ ሃያ የሚጠጉ መነኮሳት ጋር ስብሰባው ተካሂዶ ነበር።
በስብሰባውም ላይ የተሳተፉት ከአበረንታንት መድኅኒዓለም ዋልድባ የአንድነት ገዳም የቤተ - ሚናስ እና የቤተ - ጣዕመ ማኅበራት
ቢኖሩም በዛሬው ስብሰባ ላይ ከተገኙት መነኮሳት መካከል አንድም ከቤተ - ጣዕመ የመጣ መነኮሴ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል። በስብሰባው
ላይ የተገኙት መነኮሳት ቁጥር ወደ ሃያ የሚጠጉ ሲሆን በሙሉ የመጡት ከቤተ - ሚናስ ዋልድባ የሆኑና ከዚህ በፊት ቆራጥ ውሳኔያቸውን ያሳዩና በወሳኔያቸውም ምንም ለውጥ እንደሌለ
ያሳወቁት የመነኮሳቱ ቡድን በቀጣይነት በቀጠሮ የስብሰባ ጊዜ ቢሰጣቸውም ወሳኔያቸው ምንም ለውጥ እንደማይኖረው አስቀድመው ለመግለጽ
ሞክረዋል።