·
ከትንሳኤ በኃላ ከገዳሙ የሚባረሩ እንደሚኖሩም ተጠቁሟል
·
ማቄን ጨርቄን ሳትሉ ቦታውን ጥላችሁ ውጡልን
በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ባለፈው አርብ እለት ማታ በተከሰተው በታጣቂዎች በማይለበጣ
እናበዳንዶሮቃ ዘረፋ ከተፈጸመ በኃላ በቀጣዩ እለት ማለትም ቅዳሜ መናኝ ኃይለመለኮት የተባሉትን አባት ያለ ጥፋታቸው ወደ ማይጸብሪ
በመውሰድ በእስር ላይ እንደነበሩ ይታወሳል። በእለቱ አሉ ተብለው ለእስር የዳረጋቸውም “ታጣቂዎች ይዘርፉናል፥ ታጣቂዎች የዳኙናል” በሚል ሰበብ እንደነበረ
ዘግበን እንደነበረ ይታወሳል። በዚሁ እለትም በታጣቂዎች ተደብድበው የሕክምና እድል እንኳን ማግኘት ያልቻሉትንም አባ ፍቅረማርያምን
እስከ አሁን ድረስ ደማቸውን ከሚጠራርጉላቸው ወንድሞቻቸው በቀር የረባ ሕክምና ወደ ማይጋባ ወስደን እናሳክም ብለው የጠየቁትን “አይመለከታችሁም አርፋችሁ
ተቀመጡ” በማለት ማስፈራራት ደርሶባቸዋል፥ እኝህ አባትም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ምንም አይነት ህክምና ሳያገኙ
መቆየታቸውን ስጋታቸው አባቶች ገለጸውልናል፥ ነገር ግን ከሰዎቹ ፈቃድ ውጪ ምንም ለማድረግ አለመቻላቸውም በእጅጉ አሳዝኗቸዋል።