በዚሁ የምሥራቅ ጎጃም ዞን በርካቶች የመቃጠል አደጋ ደርሶባቸዋል ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው
፩ኛ/ የአንጋታ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓም ተቃጥሏል
፪ኛ/ የዳገት እየሱስ ሚያዚያ 11 ቀን 2005 ዓም
፫ኛ/ ደረባን ሕዳር 8 ቀን 2005 ዓም
፬ኛ/ የደማሞ ማርያም ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓም
፭ኛ/ የሰንደባ ሚካኤል ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓም
፮ኛ/ ጥንታዊው የአንበር ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ኅዳር 13 ቀን 2005 ዓም የቃጠሎ አደጋ ሲደርስባቸው ሃላፊነት የወሰደ ወይንም
ችግሩ ደግሞ እንዳይከሰት ለማድረግ የሞከረ የመንግሥት አካላትም የሉም። የአካባቢው ነዋሪም ቀን ቀን ሦስት ሰው ማታ ማታ አራት ሰው በመሆን ጥበቃ ያደርጋሉ ነገር ግን ይሄ በቂ ሊሆን አልቻለም።
ሰላም ባለበት፣ የሃገር ልዕልና ባለበት የዜጎች መብት በሚከበርት ሃገር እንዴት የእምነት ቦታዎች በተለያየ ጊዜ እንዲህ ቃጠሎ ሊደርስባቸው ይችላል ይህንን የክልልሉ መንግሥትም ጉዳዩን ከምንም አለመቁጠሩ፤ ነገሮች የበለጠ እንዲወሳሰቡ ሆነዋል
በሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ አድባራት፣ ገዳማት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶች ባለፉት 20 ዓመታት ሲቃጠሉ፣ ሲወድሙ ተመልክተናል ነገር ግን ቤተክህነቱ ምንም ሊያደርግ አልቻለም ወይንም የእምነቱ ተከታዮች ምንም ማድረግ አልቻሉም ወይንም አይመለከተንም ብለው ተቀምጠዋል። በጣም በእጅጉ የሚያስፈራው በቀጣይነት ክርስቲያኖች በየቦታቸው እየታደኒ አደጋ እንዳይደርስባቸው ስጋት አለን።
እምነታችንን እና ሃይማኖታችንን ነቅተን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን
እግዚአብሔር ይሁነን
ሁሉም ነገር ሌሆን ግድ ቤልም ፤ በጾለት እንደሜፈታ እመኑ እንጅ አትጠራጠሩ።
ReplyDeleteአንበርታ!
አሜን ! እግዜአብሔር ይርዳን ። የቤተከርስቴያናችን ነገር አንቅልፍ የሜያስተኛ አልሆነም።
ReplyDelete