ቀን
7 - 4 - 2006
ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን
በደላችንን በሞቱ፣ ሃጢያታችንን በቸርነቱ ያጠፋልን እስከ ሞት ድረስ የወደደን የአበው አምላክ እግዚአብሔር ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የከበረ የተመሰገነ ይሁን አሜን።
 |
ገዳማውያን እናቶች ከተገዛው አቡጀዲ ጋር |
ምንጊዜም ሠላምን ጠንነትን ለምንመኝላችሁ የቤተክርስቲያን እና የገዳማትእረዳት ለሆናችሁት የክርስቶስ ቤተሰቦች ለዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ማኅበር በሙሉ ለተከበረው ውድ ጤንነታችሁ እንደምን ከርማችኃል እንደምን አላችሁልን እኛ ገዳማውያን መነኮሳይት ለጤናችን አምላከ አበው ይክበር ይመስገን ደህና ነን።
አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መራባችንን እና መታረዛችንን በመስማታችሁ $4000.00 ዶላር 72,500.00 (ሰባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ልካችሁልን
 |
ገዳማውያን እናቶች ከተገዛው የአቡጀዲ ጋር |
1ኛ/ 60 ጣቃ አቡጀዲ
(ለአንዱ ጣቃ 550 ብር በመግዛት በአጠቃላይ
60 x 550 = 33,000 (ሠላሳ ሦስት ሺህ ብር)
ተገዝቶ መጥቶልን ገዳመ መነኮሳይቱ አንድ ጣቃ አቡጀዲ ለአራት መነኮሳይት ደርሶናል በድምሩ
240 መነኮሳይት አልባሳት አገኝተዋል።
2ኛ/ እህሉም ዛሬማ ገበያ ተገዝቶልን
40 ኩንታል ማሽላ እና ዳጉሳ ለአንድ ኩንታል እህል
900 ብር (ዘጠኝ መቶ ብር)
በመግዛት 40 x 900 = 36, 000 (ሠላሳ ስድስት ሺህ ብር)
በአጠቃላይ እህሉ ሲገዛ በቀሪው ብር በግመል እስከ ገዳሙ ተጭኖ ተረክበናል።