በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት ሞረትና ጅሩ ወረዳ የሚገኘው
የመካከለኛው
መቶ ክፍለ ዘመን የደብረ ብሥራት
አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም ተፈትቶ፣ መናንያኑና
መነኰሳቱ መበተናቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ
ገለጹ፡፡
ጥንታዊው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ተፈታ ገዳሙ ጨርሶ ሳይጠፋ ጉዳያቸው በሲኖዶሱ እንዲታይ መናንያኑ ጠይቀዋል ጥንታዊውን ገዳም ለመፈታት፣ ማኅበረ
መነኰሳቱንም ለመበተን ያበቃቸው በአካባቢ
ተወላጅነት የገዳሙን መሬት በተለያዩ ጊዜያት
ተቆጣጥረው ለግላቸው ይጠቀሙ ከነበሩ ግለሰቦች
ጋር ተፈጥሮ የቆየውና በተለያዩ ምክንያቶች
እየተካረረ የመጣው አለመግባባት መኾኑን ምንጮቹ
ተናግረዋል፡፡
በኅዳር ወር 2006 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ገዳሙን ለቀው የወጡት በቁጥር ከ50 - 80 የሚገመቱ መነኰሳት፣ መነኰሳዪያትና መናንያን ከተለያዩ
አህጉረ ስብከትና ክልሎች የተሰባሰቡ ሲኾኑ
በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ከአስተዳዳሪነት የተነሡትን
አበምኔቱን መ/ር አባ ተክለ ብርሃን ሰሎሞንን
ጨምሮ ከፊሎቹ በአሁኑ ወቅት በደነባ በኣታ
ለማርያም ገዳም ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡