በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን::
የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል:: የሐዋርያት ሥራ ምዕ ፱ ቁ ፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ_ክርስቲያን ይዞታዎችና በበዓላት ማክበሪያ ሥፍራዎች
እንዲሁም በእምነቷ ተከታዮች ላይ በልማት ሽፋን የሚፈጸመውን የቦታ ቅሚያና የክርስቲያኖች ግድያ በማስመልከት ከዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ_ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የወጣ መግለጫ
“እንግዲህ አትፍሩአቸው የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና::
በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል
የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: . . . ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ:: በሰው ፊትም የሚክደኝን
ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ::” የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ከቁጥር ፳፮ እስከ ፴፫