![]() |
የፈለገ ሕይወት መጥምቁ ዮሐንስ ወቅስት ሐና ወቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ |
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው ፈለገ ሕይወት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ የቅዱስ ዑራኤል፣ እና የእናታችን የቅድስት ሐና ቤተክርስቲያን ጸበል ለመባረክ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው የግንቦት ልደታ እለት ከቤተክርስቲያኑ ወጥተው በመመለስ ላይ እያሉ በግምት ወደ ሁለት መቶ
ሜትር ርቀት ላይ በሚደርሱበት ጊዜ የእናታችን የቅድስት ሃናን ጽላት የተሸከሙት አባት እግራቸው ይተሳሰራል፣ መራመድ ይሳናቸዋል በዚህም ከሌሎቹ ታቦታት ወደኃላ በሚቀሩበት ጊዜ ካሕናት አባቶች እና በቦታው የነበሩ አባቶች በሁኔታው ተደናግጠው ምክንያታቸውን ባለማወቃቸው የቅድስት ሃናን ታቦተ ጽላት ወደተሸከሙት አባት ጠጋ ብለው እንዳመማቸው ወይንም እንደደከማቸው ቢጠይቋቸውም ምንም እንዳላመማቸው እና ነገር ግን መራመድ እንዳልቻሉ ይናገራሉ፣ ምናልባት አባታችን ደክሟቸው ይሆናል የእግዚአብሔር የቃልኪዳኑ ታቦት እሳተ መለኮት የሚያድርበት በመሆኑ በሌላ አባት እንሞክር ተብሎ ይሞከራል ሌላኛውም አባት ተቀብለው ለመራመድ ሲሞክሩ እንደፊተኛው እግራቸው በገመድ የታሰረ ያህል ከነበሩበት መንቀሳቀስ ይሳናቸዋል፣በድጋሚ በሌላ አባት በድጋሚ እንሞክር በማለት ለመጨረሻ ጊዜ ተቀይረው ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ልክ እንደፊተኞቹ በነበሩበት ቦታ ተተክለው ይቀራሉ ወዲያው አይ ምናልባት ቅድስት ሃና በእዚሁ ለማደር ፈቅዷ ሊሆን ይችላል እና በዚሁ ድንኳን ደኩነን በዚሁ አዳር ይሁን እና በሚቀጥለው ቀን በእናታችን ፈቃድ ለመንቀሳቀስ እንሞክራለን በማለት በዕለቱ አዳር በዚያው ቦታ ይሆንና በሚቀጥለው ቀን ከጸሎት እና ከኪዳን በኃላ የቃልኪዳኑን ታቦት ከመንበረ ክብሯ ለመመለስ በድጋቢ ሙከራ ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞ በዚያው አዳር ይሆናል፥ በዕለቱም ሌሊቱን ካህናት አባቶች በጸሎት ተጠምደው የነግህ ጸሎትም አድርሰው ኪዳኑንም አቅርበው ያድራሉ።
![]() |
በአሁኑ ሰዓት የቅድስት ሃና ጽላት ያለበት ድንኳን |
በሚቀጥለው ቀን በሰውኛ ቀጠሮ በድጋሚ የቅድስት እናታችንን ታቦተ ጽላት ከነበረበረበት ተነስቶ ወደ መንበረ ክብሯ ለመውሰድ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ፈቃዷ ሳይሆን ቀርቶ በእዛው በወጣችበት በድንኳን ከተቀመጠች ይኽው ከሦስት ሳምንታት በላይ ተቆጥሯዋል። የደብሩ ካህናት በድንኳን እለት እለት ውዳሴዋን፣ ድርሳኗን እያደረሱ ቢቀመጡም የቅድስት ሃናን ታቦተ ጽላት ወደ መንበረ ክብሯ ለመመለስ ግን በፍጹም እንዳልተቻላቸው ካገኘናቸው ካህናት ለመረዳት ችለናል። ይኽ በእኛ ዘመን እያየን ያለነውን ተዓምር ለዓለም መድረስ ስላለበት በዚህ ዝግጅት ክፍል በኩል ወደ አካባቢው ተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ የተጣራ መረጃ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ፍላጎታችን በመሆኑ የደብሩን ካህናት፣ የአካባቢውን ምዕመናን በመላክ በቦታው ያለውን በፎቶ ጭምር ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲያደርሱልን በጠየቅነው መሰረት የተለያዩ መረጃዎች እየደረሱን ነው ከነዚህም መካከል በፎቶግራፍ የተደገፈ መረጃ፣ የቪዲዮ መረጃዎች ጭምር እንዲሁም አጭር የድምጽ ቃለ መጠየቅ ከደብሩ አስተዳዳሪ ለማግኘት ችለናል።
እስከአሁን ዕለት ድረስ
ወደ ሦስት ሱባኤ በድንኳን ቢያሳልፉም የአካባቢው መስተዳደር ቢሮ ምንም ምላሽ መስጠት አልቻለም፥ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ቤተክርስቲያን ለመስራት ፈልገው ነው እንዲህ የሚያደርጉት” በሚል ፈሊጥ መልስ ሊገኝ አለመቻሉ በእጅቱ
ያሳዝናል፣ ያስገርማልም፥ ሌላው በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ተወካዮች በቦታው በመገኘት እየተፈጸመ ያለውን ተዓምራት በዓይናቸው
ተመልክተው በሁኔታውም የእናታችን ተዓምራቷን እየተናገሩ እንደሚገኙ እና የአዲስ አበባ ክልል መስተዳደር ቢሮንም ግፊት ለማድረግ
ቃል በመግባት ከቅድስት ሃና በረከት ለመካፈል በቦታው ተገኝተው እንደነበር ለመረዳት ችለናል። የቤተክሕነት ተወካዮች የቤተክርስቲያኒቱን
አስተዳደር ክፍል ጉዳዩን ከካህናቱ ለመረዳት እና የተፈጠረውንም እንዲያስረዷቸው ጠይቀው እንደነበር እና የተመለከቱን እና የሰሙትን
በሙሉ ለሚመለከታቸው ክፍሎች እንደሚያስረዱ በጉዳዩ ላይ ክትትል የሚያደርጉት የአካባቢው ምዕመናን አስረድተውናል ፤ይሄ በእኛ ዘመን
እየታየ ያለ ተዓምር ነው ምናልባት የእናታችን ፈቃድ በስደት በየበረሃው እና በየሰው ሃገር እየተንገላታ፣ በዓማንያን
ካራ አንገቱን እየተቀላ፣ በጥይት እየተደበደበ ያለውን፣ በእሳት እየተቃጠለ ያለውን፣የበረሃ ንዳድ እየበላው ያለውን፣ የባሕር አውሬ
እየዋጠው ያለውን ወገናችን በተለያየ ስቃይ ያለውን ወገናችን አሳስቧት እነርሱ በየበርሃው፣ በየጉድባው ሆነው ልጆቼ እኔ ወደ ቤቴ
አልገባም ብላስ እንደሆን የአምላክ ተዓምረቱ ብዙ ነው በተለይ የእናታችን የጭንቅ አማላጅቱ ተዓምራቷ፣ ሩህሩህነቷ፣ አማላጅነቷ ዘወትር
ከኢትዮጵያውያን ጋር እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ መሆኑን እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ጠንቅቀን እናውቃለን።
በመጨረሻ የዝግጅት ክፍላችን በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን የቅድስት ሃና ወዳጆች እመ ብርሃንን
ለምነን በጭንቃችን የምትደርስልን እናታችን በቦታው ያለውን ሁኔታ በአካባቢው ምዕማናን እያደረጉ ያለውን ተጋድሎ፣ እንድትመለከቱ
እየጋበዝን ጊዜው እና የቦታው እርቀት የማይገድባችሁ የእመቤታችን ወዳጆች በቦታው ተገኝታችሁ የበረከቷ ተካፋዮች እንድትሆኑ በማንኛውም
መልኩ ልትራዱ የምትፈልጉም የደብሩን ካህናት እያነጋገራችሁ የበኩላችንን ትብብር እንድናደርግ በእናታችን በቅድስተ ቅዱሳን ስም እየጠየቅን
ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጡትንም መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጋብዛለን።
የእናታችን የቅድስት
ሃና ረደኤቷ እና በረከቷ ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጋር ይደርብን አሜንበቅርቡ የቪዲዮ መረጃውን ይጠብቁ
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
ማሕበራችንን ይባርክ። እንዴሁም ለማሕበሩ አባላት እድሜ ጤና ና ፀጋውን ይስጠችሑ።
ReplyDelete