ከሰኔ ፳፩
እስከ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓም በተደረው የESFNA ፴፪ ኛ ዓመታዊ በዓል ላይ ተሳተፈ
በበዓሉ ላይ IUEOTCFF በርካታ ሥራዎችን
ለኢትዮጵያውያን በማቅረብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሞክሯል
በዚሁ በዓል መጠናቀቂያ ላይ
IUEOTCFF ትልቅ ጉባኤ በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ አዘጋጅቶ ለምዕማናን በገዳሙ ላይ እየደረሰ ያለውን እና በገዳሙ አካባቢ
የደረሰውን ተዓምራት ለምዕመናን ተገልጿል
ይሄንኑ የESFNA በዓል ተከትሎ የማኅበሩ
አጠቃላይ ጉባኤ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን አድርጎ የውሳኔ ሃሳቦችን አስተላልፏል
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ከተመሠረተበት ሦስት ዓመታት ከግማሽ
ጀምሮ ጉባኤ ዘርግቶ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን በማዛጋጀት ለትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ የዓለም
ማኅበረሰብ የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት፣ ለዓለም ማኅበረሰብ ደብዳቤ በመጻፍና በአካል በመገናኘት ገለጻዎችን በማድረግ ብሎም
በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመገኘት እየደረሰ ያለውን ጥፋት እና እንግልት ለኢትዮጵያውያን ሲያስገነዝብ
እና የእምነቱ ተከታዮችን አለኝታነታቸው እንዲያሳዩ ሲያሳስብ መረጃዎችን ሲያደርስ ቆይቷል። አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ስፖርት
ፌደሬሽን ሰሜን አሜሪካ ፴፪ኛው ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት ለምዕመናን እንዲሁም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያን በዋልድባ ገዳም ላይ
እየደረሰ ያለውን እንግልት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስውር ደባ፣ በምዕመናን ላይ እየተፈጠረ
ያለውን ውዥንብር ለኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘዴዎች ለማድረስ ጥረት ተደርጓል፤ ከነዚህም መካከል