- የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በትምህርት ይከላከላል፤ ማስረጃዎችን እያቀረበ ያጋልጣል
- የጠቅ/ቤተ ክህነቱ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ይመራል
- ቋሚ ኮሚቴው፣ ከሰርጎ ገቦች የጸዳና አባላቱም በሃይማኖታቸው እንከን የሌላቸው ሊኾኑ ይገባል
![]() |
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፤የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ |
ቋሚ ኮሚቴው÷ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት እና ክርስቲያናዊ ትውፊት በመበረዝ እና አስተዳደራዊ አንድነቷን በማናጋት ለመከፋፈል አልያም ባለችበት አዳክሞ ለመውረስ ወደ መዋቅሯ ሰርገው የገቡትን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችንና የዋነኛ አዝማቾቻቸውን ሤራ በማስረጃ የማጋለጥ እና በትምህርት የመከላከል ተልእኮ የተሰጠው ሲኾን ዓላማውን የሚያስፈጽምበት መዋቅርም በዘላቂነት እንዲዘረጋ ነው የተወሰነው፡፡