
ታኅሣሥ 12
እንኳን ለታላቁ ጻድቅ "አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ" እና ለሰማዕታት "አንቂጦስ ወፎጢኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
አባ ሳሙኤል ዘዋሊ
ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን:: በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ ቦታ አላቸው:: በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል : ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል::
እነዚህም:-
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው::