በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን
Friday, May 27, 2016
የእንደራሴ ምደባ በፈጠረው መካረር ስብሰባው በድንገት ተቋረጠ፤ ፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ አዝነውበትና ጸልይውበትይወስኑበታል
Tuesday, May 10, 2016
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም ልደት ደስታ ሆነ!
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም - በድንግል ማርያም
ልደት ደስታ ሆነ!

አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ “ለመኑ ዘዘገብነ ዘንተ መዛግብቲነ አልብነ ውሉድ ዘይወርሰነ
- ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ
ሴት አላውቅም” አላት። እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ
ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳን ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት። እሷም አምላከ
እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በሕልሜ “ርኢኩ በሕልምየ ጸዓዳ ጣዕዋ ወጽአት እምከርስየ -
ነጭ ጥጃ ከማኅጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ ፯ት
ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው።
Subscribe to:
Posts (Atom)