- ምደባው፥ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግና አደራን የመጠበቅ ጉዳይ እንደኾነ ተገልጧል፤
- የልዩ ጽ/ቤትና የአ/አበባ ሀ/ስብከት አጀንዳዎች እንዲሰረዙ በያዙት ተቃውሞ ቀጥለዋል፤
- “አንሡኝ!”ላሉበት አቋማቸው፣ “ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ እናደርገዋለን!” ተብለዋል፤
- በጎጥና በጎሳ ለማሸማቀቅ የሞከሩ የምልዓተ ጉባኤው አባላት በከፍተኛ ደረጃ ተገሥጸዋል፤
* * *
- የ3 ዓመት ዘመነ ፕትርክና አፈጻጸማቸው በምልዓተ ጉባኤው ተገምግሟል፤
- የፀረ ሙስና አቋማቸው ንግግር በማሣመር የተወሰነና ተግባር የራቀው ነው፤
- የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመጣስ አማሳኞችን ተባብረዋል፤ ከለላም ሰጥተዋል፤
- የመናፍቃን ቅጥረኞችና አማሳኞች፣ በአባቶች ላይ ለመዝመት እየመከሩ ነው፤
* * *
- ብር 800ሺሕ የወጣበት በዓለ ሢመት፣ ብክነትና መንበረ ፓትርያርኩን ያዋረደ ነው፤
- ለቤትና ለጂምናዝየም ዕቃዎች ማሟያ፣ 2 ሚ. ብር ከአ/አ ሀ/ስብከት ወጪ ተደርጓል፤
- በደቡብ አፍሪቃ፣ የልዩ ጽ/ቤታቸው ጣልቃ ገብነት ችግሩን አባብሶ ለውርደት ዳርጎናል፤
- በዱባይ የተሐድሶ መናፍቃን ያሉበት ደረጃ፣ በጉዳዩ ላይ ለዘብተኝነታቸውን አሳይቷል፤
* * *

- “ኃይል አለኝ፤ ነገር ግን መጠቀም አልፈልግም” በሚል በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ ዝተዋል፤
- የአማሳኞች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ለመሰንበት የሙጥኝ ብሏቸዋል፤
- ለ፩ ሰዓት የቆየው የተሲዓቱ የጉባኤው ውሎ፣ በሐሳብ መካረሩ በድንገት ተቋርጧል፤
- የተባበረ አቋም የያዘው ጉባኤ፥ እስከ ሰኞ አዝኖበትና ጸልዮበት ለመወሰን ቆርጧል፡፡
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
No comments:
Post a Comment
እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ መልሳችንን በቅርቡ ይጠብቁን፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤