Tuesday, April 24, 2018

Friday, April 13, 2018

በመጨረሻ አባቶቻችን ነፃ ተለቀዋል፥ አምላከ አበው የብዙዎችን ልቅሶ ተቀብሏል እንኳን ደስ አለን ለመላው ኢትዮጵያዊ በሙሉ

received_646981535648903FB_IMG_1523529318111

received_646982172315506
በመጨረሻም፣ በዐቃቤ ሕግ የተመሠረተባቸው የ“ሽብር ክሥ” የተቋረጠላቸው ኹለቱ የዋልድባ መነኰሳት ከእስር ተፈቱ፡፡

ዐቃቤ ሕግ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ክሡን ማቋረጡን፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ያስታወቀ ሲኾን፤ ተከሣሾቹ ለሚገኙበት ለቂሊንጦ እስር ቤት የመፍቻ ትእዛዝ እንዲጻፍለት በጠየቀው መሠረት ፍ/ቤቱ በሰጠው ትእዛዝ ኹለቱ አበው መነኰሳት ዛሬ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከእስር ተፈተዋል፡፡

ከአባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት ገብረ መድኅን ጋራ ለአንድ ዓመት ከአራት ወራት በእስር የቆዩት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም ካሴ(በፎቶው: በስተግራ የሚታዩት)፣ በዋልድባ አካባቢ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ከ2004 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ፣ የገዳሙን ይዞታ ለማስከበር ማኅበረ መነኰሳቱን በመወከል ባደረጉት ጥረት ይታወቃሉ፡፡
ከኹለቱ አበው መነኰሳት ጋራ በአንድ መዝገብ የተከሠሠውና ከቃሊቲ እስር ቤት ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው፣ አቶ ነጋ ዘላለም መንግሥቴም ከእስር የመፈቻ ትእዛዝ እንደወጣለት ተረጋግጧል፡፡ ከትላንት ጀምሮ ተፈጻሚ በኾነው የፍ/ቤቱ የፍች ትእዛዝ፣ ክሣቸው የተቋረጠላቸው 114 ተከሣሾች ከእስር እንደሚለቀቁ መዘገቡ ይታወሳል፡፡


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Wednesday, March 28, 2018

የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት: በሕግ ፊት እኩል ኾኖ የመታየት መብታቸው ተጥሷል – ጠበቃው

FB_IMG_1522057967519
 • የ32ቱ ክሥ የተቋረጠበትና የ3ቱ ተከሣሾች ሳቋርጥ የቀረበት የሕግ ምክንያት አልተገለጸም፤
 • የሥነ ሥርዓት ሕጎች ተለጥጠው ከተተረጎሙ በተከሠሡት ላይ የማይመለስ ጉዳት ያስከትላል፤
 • በተለይም በታሰሩ ሰዎች ላይ፣ አለ የተባለ ማስረጃ በሰዓቱ ቀርቦ የተፋጠነ ፍትሕ ይሰጣቸው፤
 • በፍርድ ሒደት ነጻ ቢባሉም እንኳን፣ ጉዳታቸው የበዛ እንዳይኾን ዐቃቤ ሕግ ሓላፊነቱን ይወጣ
 • በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት ኹኔታ ፍ/ቤቱ፥“ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ”ያለው ሊያነጋግር ይችላል፤
 • ከሣሹ አካል፥ በሕግ ፊት የተከሠሡ ሰዎች እኩል መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ ትልቅ ዋጋ በመስጠት ከተለዋጩ ቀጠሮ በፊት የሚወስነው ውሳኔ ካለ እንጠብቃለን፡፡
†††

Tuesday, March 27, 2018

በሁለቱ የዋልድባ መነኰሳት ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ባለማቅረቡ ፍ/ቤቱ ለሚያዝያ ፲፰ ቀን ፳፻፲ ቀን በድጋሚ ቀጠረ

FB_IMG_1522058589440
 • ዐቃቤ ሕግ እና ፖሊስ፣ “ምስክሮቹ ያልቀረቡበትን ምክንያት አናውቅም፤” አሉ
 • አብረውን ተከሠው ከነበሩት የምንለየውና የማንፈታው ለምንድን ነው? ያሰረንስ አካል ማን ነው?/መነኰሳቱ/
 • እግዚአብሔር አለ፤ እመቤታችን አለች፣ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር ዐዋቂ ነው፤”/አብሯቸው የተከሠሠው ነጋ ዘላለም/
†††

Saturday, March 24, 2018

በታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን ዝምታ እያነጋገረ ነው


waldibba monks and betekihnet
 • ከወንጀል ክሡ በመለስ፣ ሃይማኖታዊ ክብሯ በዐደባባይ ሲዋረድ ዝምታን መምረጧ ምነዋ ያሰኛል፤
 • በፓትርያርኩ አማካይነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስጦታ ማበርከቱ፣“ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምፀት ነው፤”
 • ጉዳዩ በምእመኑና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትኩረት እያገኘ ነው፤ የቤተ ክህነቱ ዝምታ አነጋጋሪ ኾኗል፤
†††
በእነተሻገር ወልደ ሚካኤል ክሥ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሠው በቂሊንጦ እስር ቤት በሚገኙት ኹለቱ የዋልድባ ገዳም መነኰሳት ጉዳይ፣ ቤተ ክርስቲያን ድምፅዋን አለማሰማቷ አነጋጋሪ መኾኑን ብዙኃን መገናኛዎች እየዘገቡ ነው፡፡
ዛሬ ቅዳሜ፣ መጋቢት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ታትመው የወጡት ቁም ነገር እና ግዮን መጽሔቶች፥ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ ኹለቱ አባቶች ልብሰ ምንኵስናቸውን ከመልበስ እንዳይከለከሉ ትእዛዝ መስጠቱን በመጥቀስ፣ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተ ክርስቲያን ዝምታን መምረጧ እያነጋገረ መኾኑን ዘግበዋል፡፡

Wednesday, March 21, 2018

የሕዝበ ክርስቲያኑን ጩኸት እግዚአብሔር ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም ይሰማል ! እናምናለን


ሃገራችን ኢትዮጵያ ከዛሬ ፳፮ ዓመት ከ፱ ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከ፳፮ ዓመት ከ፱ ወር ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የደረሱ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች የሰው ልጅ በሕሊናው ከሚያስበው በላይ እንደሆን ማንም ሰው ሊያጤነው የሚገባ እንደሆነ እንገምታለን፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በቁጭት እንደሚመለከቱት እናምናለን።
በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ዋነኞቹ የቤተክርስቲያን እሴቶች ጠፍተዋል፣ የቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መገለጫዎች ተመዝብረዋል፣ የማምለኪያ ቦታዎች በልማት ስም ተወስደዋል ፣ የቤተክርስቲያን አባቶች ተዋርደዋል፥ ክቡር የሆነውን ሕይወታቸውን ሰውተዋል፣ ቤተክርስቲያኒቱ ባለቤት እንደሌለው ለማንም መሳቂያ መሳለቂያ እስከመሆን ደርሰዋል፣ ታላላቅ ለቤተክርስቲያን ሊጸልዩ፣ ለሃገር ምሕረትን ሊያመጡ የሚችሉ አባቶች በግፍ ከትውልድ ሃገራቸው፣ ከሚወዷት ሃገራቸው ተገፍተው ተባረዋል፣ ብቻ ሌላም ሌላም ሊባል ይችላል፥ ታዲያ ይሄ ሁሉ ሲሆን ከልካይ፣ ጠያቂ፣ ኸረ የመድኅኒዓለም ያለህ ያለ ማንም አለመኖሩ እጅግ የሚያሳዝን የሚያስገርምም ነገር ነው።

የታሰሩት አባቶች ልብሰ ምንኵስናቸው ከመልበስ እንዳይከለከሉ ፍ/ቤት አዘዘ፤ “ክሡ የማይቋረጥበት ሕጋዊ ምክንያት አይታየኝም”/ጠበቃው/

waldiba menekosat

 • ምስክሮችን ለማቅረብ ዳተኝነት የታየበት ዐቃቤ ሕግ፣ በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ምስክሮቹን በዕለቱ እንዲያቀርብ ፍ/ቤቱ አስጠነቀቀ
 • አባ ገብረ ኢየሱስ ከ“ቅጣት ቤት” ወጥተዋል፤ ኹለቱም በዞን አንድ ይገኛሉ፤ አጠቃላይ ኹኔታው የተሻሻለ መኾኑን ገልጸዋል፤
†††

Monday, February 26, 2018

ለመነኰሳቱ አቤቱታ ማ/ቤቱ መልስ እንዲሰጥ ታዘዘ፤ ምስክር ይሰማባቸዋል፤“ያልነበረ ጉስቊልና ይስተዋልባቸዋል”

 • ማረሚየ ቤቱ፣ ለካቲት 30 ቀን መልስ እንዲሰጥ ታዘዘ፤
 • የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 18 ቀን ቀጠሮ ተያዘ፤
28166839_1981266108569045_7091172735053479014_n
የ“ሽብር” ክሥ ተመሥርቶባቸው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት ኹለቱ የዋልድባ ገዳም መነኰሳት፣ ልብሰ ምንኵስናቸውን እንዲያወልቁ እየተገደዱ እንዳሉ በጽሑፍ ላቀረቡት አቤቱታ፣ እስር ቤቱ ለየካቲት 30 ቀን መልስ እንዲሰጥ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዘዘ፡፡
በእነተሻገር ወልደ ሚካኤል የክሥ መዝገብ 4ኛ ተከሣሽ የኾኑት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም እና 5ኛ ተከሣሽ አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት፣“ልብሰ ምንኵስናችንን አናወልቅም” በማለታቸው ባለፉት ቀጠሮዎች ያልቀረቡ ሲኾን፣ በቅጣት ቤት እንደሚገኙ በአቤቱታቸው ገልጸዋል፡፡ “የኹለቱም መነኰሳት አካል ላይ ባለፉት ጊዜያት ያልነበረ ጉስቊልና ይስተዋላል፤” ብሏል የዛሬ ሰኞ የካቲት 19 ቀን የችሎት ውሏቸውን የተከታተለው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው፡፡
†††

ልብሰ ምንኵስናቸውን እንዲያወልቁ ጫና የተደረገባቸው የዋልድባ መነኰሳት ለፍ/ቤት በጽሑፍ ያቀረቡት አቤቱታ

28166839_1981266108569045_7091172735053479014_n27972350_1257453024398123_1419641619183814929_n
 • የእምነት ልብሳችንን ከምንቀይር የሥጋ ሞታችንን እንመርጣለን፤
 • “አልባሳታችን የምናወልቀው ስንሞት ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ይህን አልባሳታችንን እንድንለውጥ መገደድ ማለት ለእኛ እምነታችንን እንድንሽር፣ በእግዚአብሔር ስም የተሰጠንን ክብር እንዲዋረድ ማድረግ ነው፤”
 • 5ኛ ተከሳሽ የሆንኩት አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት ወደዚህ ፍ/ቤት ለመምጣት የእምነት ልብሴን እንዳወልቅ ስጠየቅ አላወልቅም በማለቴ ማዕርጋቸውንና የአባታቸውን ስም ያላወቅኋቸው ነገር ግን የደኅንነትና ጥበቃ ሓላፊ መሆናቸው የሚታወቁ ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ የእስር ቤቱ ሓላፊ እያዩና ራሳቸው እያገዙ ተፈሪ የተባለ ወታደር የጎማ ዱላ በመያዝ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታ ሊወስደኝ ሲሞክር ምሶሶ ላይ ተጠምጥሜ እምቢ ብልም ልብሴን ከላየ ላይ ለመግፈፍ በኃይል እየጎተተ ያንገላታኝ ከመሆኑም በላይ አቅም አንሶኝ ከመሬት ወድቄ ከእነ ልብሴ መሬት ላይ ጎትቶኛል፤
 • መነኰሳቱ፣ ነገ የካቲት 19 ቀን ቀጠሮ ያላቸው ሲሆን አቤቱታውም ለፍርድ ቤቱ ደርሷል
 †††

Saturday, January 6, 2018

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን!

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። ሉቃስ ፪ ፥ ፲፩

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን በማለት መልካም ምኞቻችንን እየገለጽን፥ በዚህ ታላቅ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ እለት በሃገራችን ኢትዮጵያ በችግር በሥቃይ እንዲሁም በተለያየ ግዞት ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን መፈታትን እረደኤትን እንዲያድልልን ከልብ የተመኘት ለመጪውም በዓለ ጥምቀቱ በሰላም እንዲያደርሰን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን በማለት እንመኛለን።
በተለይ በዚህ ሰዓት በእሥር ላይ ለሚገኙ አጠቃላይ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶቻችን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የሲቪክ ድርጅት አባሎች፣ ጋዜጠኞች ሌሎችን በአጠቃላይ እግዚአብሔር አምላክ ከታሰሩበት እሥራት እንዲያስፈታልን እና በሃገራቸው በእምነታቸው በነጻነት ይኖሩ ዘንድ የመድኅኒዓለም ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን በማለት በዓለ ልደቱ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍሰሃ በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።
IUEOTCFFLet's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!