
- የ32ቱ ክሥ የተቋረጠበትና የ3ቱ ተከሣሾች ሳይቋርጥ የቀረበት የሕግ ምክንያት አልተገለጸም፤
- የሥነ ሥርዓት ሕጎች ተለጥጠው ከተተረጎሙ በተከሠሡት ላይ የማይመለስ ጉዳት ያስከትላል፤
- በተለይም በታሰሩ ሰዎች ላይ፣ አለ የተባለ ማስረጃ በሰዓቱ ቀርቦ የተፋጠነ ፍትሕ ይሰጣቸው፤
- በፍርድ ሒደት ነጻ ቢባሉም እንኳን፣ ጉዳታቸው የበዛ እንዳይኾን ዐቃቤ ሕግ ሓላፊነቱን ይወጣ፤
- በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት ኹኔታ ፍ/ቤቱ፥“ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ”ያለው ሊያነጋግር ይችላል፤
- ከሣሹ አካል፥ በሕግ ፊት የተከሠሡ ሰዎች እኩል መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ ትልቅ ዋጋ በመስጠት ከተለዋጩ ቀጠሮ በፊት የሚወስነው ውሳኔ ካለ እንጠብቃለን፡፡
†††