
- ኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ በመንፈሳዊና አስተዳደራዊ ተግባር በየድርሻቸው የሚያገለግሉበት ታላቅ ስምምነት ነው፤
- የኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ በዓለ ሢመተ ፕትርክና፣ የቤተ ክርስቲያን በዓል ኾኖ ይከበራል፤
- በኹለቱም በኩል የተላለፈው ቃለ ውግዘት ይነሣል፤ የተሾሙ ሊቃነ ጳጳሳትም ለአንዱ ቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ ኾነው ሓላፊነታቸውን ይወጣሉ፤
- በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የተሾሙ አባቶች፣ በፍላጎታቸው መሠረት በውጭም በውስጥም አህጉረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው ይሠራሉ፤
- የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታዊ ድጋፍ፣ የቤተ ክርስቲያንን የዓመታት የሰላም ጥረት ፍሬያማ እንዲኾን አድርጓል – “በእግዚአብሔር ቀን”
†††