በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን
Tuesday, December 29, 2020
Friday, December 18, 2020
Friday, December 11, 2020
Sunday, December 6, 2020
Tuesday, December 1, 2020
Monday, November 23, 2020
Saturday, November 14, 2020
Friday, November 13, 2020
የህወሀት ሴራ በዋልድባ ገዳም ሰላዩ መነኩሴ ቅዱሳት መጻሕፍት እየተዘረፉ ነው TPLF |TOP SECRET
Thursday, November 12, 2020
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዐረፉ
Tuesday, November 10, 2020
Thursday, November 5, 2020
አካባቢን በንቃት በመጠበቅ ከልብ በኾነ ለቅሶ ወደ ፈጣሪ በመጮኽ ጸሎት የሚደረግበት ጊዜ ነው – ብፁዕ አቡነ አብርሃም
- ከኅዳር 1 እስከ 7 ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ በቅዱስ ሲኖዶስ የታወጀውን፣ ምእመናን በየአጥቢያቸው እየተገኙ እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላለፉ፤
- በግድያ እና ማፈናቀል ተጎድተው በምግብ እና በሰላም ዕጦት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ላሉ ወገኖቻችን፣ ሕዝብ እና መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፀኑ፤
- በተለይ በዓመታዊ በዓላት፣ በቅርሶች እና በምእመናን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ወጣቱ ተገቢውን ፍተሻ በማካሔድ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳሰቡ፤
***
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ፡፡ ወቅቱ፣ ከልብ በኾነ ለቅሶ ወደ ፈጣሪ በመጮኽ ጸሎት የሚደረግበት ጊዜ እንደኾነም ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ: በምዕራብ ወለጋ፣ በጉራፈርዳ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጅምላ ጭፍጨፋ አወገዘ
Sunday, November 1, 2020
Thursday, October 29, 2020
ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እና የሽማግሌ ቡድኑ ሰብሳቢ ላእከ ሰላም ባያብል ሙላቴ፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና ስለተደረሰበት ስምምነት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
- “ጥያቄአችን ከአስተዳደር ችግር የመነጨ እንጂ ሃይማኖታዊ አልነበረም፤ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ናት አሸናፊዋ፤ ቤተ ክርስቲያን አሸናፊ ከኾነች ኹሉም አሸናፊ ነው፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ እና በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ሥር ኾነን አገልግሎታችንን እንቀጥላለን፤ ሕዝባችንን እናገለግላለን፤ ያሳዘነውን እናስደስታለን፤
- እኛ የቤተ ክርስቲያን ከኾን፣ የኦሲኤን ቴሌቪዥን ጣቢያም የቤተ ክርስቲያን ነው፤ ቤተ ክርስቲያን፥ ኹለት ሦስት ብቻ ሳይኾን ብዙ ያስፈልጋታል፡፡”
/ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን/
Saturday, October 24, 2020
ሰበር ዜና – ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!
- የሕግ ባለሞያዎች፥ በሀገር ውስጥ እና በውጪ አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያን ውክልና እየተሰጣቸው ግፈኞችንና ያለስሟ እና ያለግብሯ በሐሰተኛ ትርክት ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱትን እንዲፋረዱ ወሰነ!
- በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመሩ ኹለት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ሰላም መንግሥትንና የፖሊቲካ ኃይሎችን በቀጥታ ያነጋግራሉ፤
- ሕዝብ እየተገደለና አገር እየጠፋ ያለው፣ በፖሊቲካው ትርምስ በመኾኑ፣ በቅራኔ የተፋጠጡ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ ይማፀናሉ፤ ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ካሳን፣ ለተፈናቀሉት መመለስን፣ በሐሰት ተከሰው በእስር ለሚንገላቱት መፈታተን፣ ለተደፈሩት ይዞታዎች መከበርን እንዲያነብር መንግሥትን ይጠይቃሉ፤
- የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን የመዘርጋቱ ሥራ፣ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአስቸኳይ እንዲጀመር፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቅላይ ጽ/ቤቱን አሳስቧል፤
- ለድንገተኛ አደጋዎች እና ችግሮች ፈጣን ምላሽ እና ርዳታ የሚሰጥ አስተባባሪ አካል፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በማእከል እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል፤ በተለይ የውጪ አህጉረ ስብከት፣ ፋይናንሳዊ፣ ማቴሪያላዊ እና ሞያዊ ድጋፎችን እንዲያስተባብሩለት ተስማምቷል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት ለመከላከል በሚያስችሉ ስልታዊ አማራጮች ላይ እየተወያየ ነው
Thursday, October 15, 2020
አጠቃላይ ጉባኤው: ለቅዱስነታቸው ራስን በራስ የመከላከል ጥሪ የጋለ ድጋፍ በመስጠት ዝግጁነቱን ገለጸ፤ ባለ15 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ዓመታዊ ስብሰባውን አጠናቀቀ
- ቅዱስ ሲኖዶስ ግፉን ከመሠረቱ ለማስቆም፣በምልአተ ጉባኤው ጠንክሮ እንዲወያይበት ጠየቀ፤
- በዓላትን በየሰበቡ የማስተጓጎል አድሏዊ አካሔድ እንዲታረምና ወጥ አሠራር እንዲበጅ አሳሰበ፤
- የቅድመ አደጋ ስጋት ክትትልና መከላከል ሥርዓት እንዲዘረጋ የተወሰነው እንዲፈጸም አዘከረ፤
- “ቅዱስ ፓትርያርኩ ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ራሳችንን እናዘጋጅ፡፡”
***
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የግፍ ጥቃት ለመግታት እና ፀራውያንን ለመቋቋም፣ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን አስተባብራ እና አደራጅታ ራስዋን በራስ ወደ መጠበቅ እንድትሸጋገር፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለአቀረቡት ማሳሰቢያ የጋለ ድጋፉን የሰጠው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ መላ አገልጋዮች እና ምእመናን ለተግባራዊነቱ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አስተላለፈ፡፡
Wednesday, October 14, 2020
ለመሎ ላሃ የሃይማኖት እስረኞች የድጋፍ ጥሪ
Tuesday, October 13, 2020
ቤተ ክርስቲያን የሚዘንብባትን መከራ ለመግታትና ለመቋቋም፣ ልጆችዋን አስተባብራና አደራጅታ ራስዋን ወደ መጠበቅ እንድትሸጋገር ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ
- “ከምንም ጊዜ በላይ ታጥቀን ለቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል እና ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሕይወት ዋስትና መረጋገጥ በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ነው፡፡”
***
በየዓመቱ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ 39ኛ ዓመታዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስብሰባውን ዛሬ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ረፋድ ማካሔድ ጀምሯል፡፡



ዐዲስ በተገነባው እና “ጽርሐ ተዋሕዶ” ተብሎ በተሰየመው አዳራሽ በጸሎተ ወንጌል በተጀመረው በዚኹ ዓመታዊ አጠቃላይ ጉባኤ መክፈቻ ላይ፣ “ወይኩን ቅኑተ ሐቈክሙ ወኅትወ መኃትዊክሙ፤ ወገባችኹ የታጠቀ፣ መብራታችኹም የበራ ይኹን፤”(ሉቃ. 12፥35)በሚል ርእስ መልእክት ያስተላለፉት ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፥ ቤተ ክርስቲያንን ከገጸ ምድር ለማጥፋት በየአቅጣጫው የተነሡ ኃይሎች በተበራከቱበት እና የሚፈጽሙባትም ግፍ እየተባባሰ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ፣ ጥቃቱን ለመመከት እና መከራውን ለመግታት፣ መላውን አገልጋዮች እና ምእመናን አስተባብሮ እና አደራጅቶ ራስን ወደ መጠበቅ አማራጭ መሸጋገር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፤ ጉባኤውም ተገቢውን መፍትሔ እንዲያስቀምጥ ኣሳስበዋል፡፡
Saturday, October 10, 2020
ላዕከ ወንጌል መምህር ሰሎሞን ኃይሌ
Saturday, October 3, 2020
ሊቀ ብርሃናት መልአክ አዲስ
Thursday, October 1, 2020
ቀሲስ ኢዩኤል በርታ
Monday, September 21, 2020
መልአከ ብርሃናት ጌታሁን
Tuesday, September 15, 2020
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
Monday, September 14, 2020
መምህር አዲስ ተፈራ
Saturday, September 5, 2020
መጋቤ ኃይማኖት ዋለልኝ ጫኔ
Tuesday, September 1, 2020
መጋቤ ጥበብ ሳሙኤል ግዛው
Friday, August 28, 2020
ዝማሬ ከግጥም ጋር በዋልድባ
Friday, August 21, 2020
ዲያቆን ጥበበ ማሞ
Monday, August 17, 2020
ቀሲስ ልዑልሰገድ ኃ:ማርያም
Friday, August 7, 2020
ቀሲስ አሸናፊ ዱጋ በዋልድባ እንታደግ
ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፈው የዋልድባን እንታደግ መደበኛ ጉባኤ በሐሙስ ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓም በቀሲስ አሸናፊ ዱጋ “. . .የምትለምኑትን አታውቁም? . . .” በማቴዎስ ፳፯ ፥ ፳፩ በመነሳት ያስተላለፉት ትምህርት እንደሚከተለው ቀርቧል፥ ይሄን ትምህርት ላልሰሙት በማሰማት፣ ላልደረሳቸው በማዳረስ እንድትራዱን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ፤ በተጨማሪ በትምህርቱ እንድንማርበት በሕይወታችንም እንድንጠቀምበት ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን እና በየሳምንቱ የሚተላለፈውን ትምህርት ለመከታተል ቢፈልጉ ሐሙስ ከ9:00 PM ጀመሮ በዋሺንግተን ዲሲ አቆጣጠር ይቀርባል፤ የሚከተሉትን ቁጥሮች በመጠቀም የጉባኤው ታዳሚ ይሁኑ፥
©SaveWaldba2020
Saturday, August 1, 2020
መልአከ ገነት በለጠ ይረፉ
Friday, July 24, 2020
ፀሐፌ ትዕዛዝ ታዲዎስ ግርማ
Monday, July 20, 2020
Thursday, July 16, 2020
በኢትዮጵያ በሃይማኖታቸው ምክንያት መስዋዕትነት ስለተቀበሉት ወገኖቻችን ይሄንን በመርዳት እንደግፍ
Friday, July 10, 2020
መጋቢ ምስጢር አእምሮ ተበጀ ሐምሌ ፪
Friday, July 3, 2020
ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፈው የዋልድባን እንታደግ መደበኛ ጉባኤ በሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓም
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Saturday, June 27, 2020
መልአከ ጽዮን ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ ሐሙስ ሰኔ ፲፰
Monday, June 22, 2020
የእመቤት ጃራ የግጥም መድብሎች በዋልድባ
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Saturday, June 20, 2020
የአፍሪካ ኅብረቱ መስጊድ እና ሕጋዊነቱ
- የቦታው አሰጣጥ፥ በሃይማኖት ተቋማት የአምልኮ ማካሔጃ ቦታ አፈቃቀድ መመሪያ ከተዘረዘሩት መሳፍርት አንዳቸውንም አያሟላም፤
- ከነባሩ ደብር 100 ሜትር በማይርቅ ቦታ መስጊድ እንዲተከል መፍቀድ፣ የእምነት ነፃነትን መጋፋት እንጂ ማስከበር ሊኾን አይችልም፤
- የከተማዋን ማስተር ፕላንም የተከተለ አይደለም፤ ደብሩ በልማት ስም ለተወሰደበት ቦታ ትክ ሳይሰጥ ከማስተር ፕላኑ ጋራ በሚጋጭ መልኩ ለሌላው መፍቀድ አግባብ አይደለም፤
- “ለልማት ይፈለጋል” በሚል ብዙኃን ምእመናን በጥድፊያ ከተፈናቀሉ ከ5 ዓመት በኋላ፣ ከደብሩ በቅርብ ርቀት ለመስጊድ ቦታ መስጠቱ ከፍተኛ ጥርጣሬንና የመገፋት ስሜትን ፈጥሯል፤
- ያላቸውን ቦታ ከኦርቶዶክሳውያን ጋራ እያነጻጸሩ፣ “እኛ አንሶናል” የሚሉ ተደጋጋሚ ጩኸቶች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከሕግ ውጭ እንዲሠራ ጫና ሳይፈጥሩበት አልቀሩም፤
- በኹለቱ እምነቶች ተከታዮች መካከል አላስፈጊ ግጭት የሚፈጥር ከመኾኑም በላይ፣ የአካባቢውን የድምፅ ብክለት ያንራል፤ የትራፊክ መጨናነቅም ያስከትላል፡፡
- ስለዚኽም የቦታ አሰጣጡ፥ ከሕግ፣ ከአካባቢ ሰላም እና ደኅንነት አኳያ በድጋሚ በአጽንዖት መታየት ይኖርበታል።
የቀሲስ መንግሥቱ ክፍል ፪ ትምህርት
ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፈው የዋልድባን እንታደግ መደበኛ ጉባኤ በሐሙስ ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓም በቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ) “. . .በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፤ በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ ኑሩ . . ." ቆላሲስ ፩ ፥ ፲ ካለፈው ሳምንት ተከታይ የሆነውን ክፍል ፪ በሚል ያስተላለፉት ትምህርት እንደሚከተለው ቀርቧል፥ እንድንማርበት በሕይወታችንም እንድንጠቀምበት ይረዳን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን እና በየሳምንቱ የሚተላለፈውን ትምህርት ለመከታተል ቢፈልጉ ሐሙስ ከ9:00 PM ጀመሮ በዋሺንግተን ዲሲ አቆጣጠር ይቀርባል፤ የሚከተሉትን ቁጥሮች በመጠቀም የጉባኤው ታዳሚ ይሁኑ፥ ዘወትር ሐሙስ ከ9:00 PM EST ጀምሮ ይተላለፋል Dial: 1(848)220-3300 Passcode: 376 0937# ይሄንን መልዕከት ለጓደኛ፣ ለወዳጅ፣ ለዘመድዎ በማስተላለፍ ቃሉ ያልደረሰላቸውን ያዳርሱ፣ ወቅታዊ መረጃዎችንም ለማግኘት ሰብስክራብ በማድረግ ደውሏን በመጫን አዲስ መረጃ ሲኖር ምልክት ይሰጥዎታል፤ https://www.facebook.com/savewaldba/ https://www.facebook.com/KidusWaldba https://www.youtube.com/savewaldba https://www.instagram.com/kiduswaldba/ ዋልድባን እንታደግ ዓለምአቀፈ ትብብር ግንቦት ፳፻፲፪ ዓም ©SaveWaldba2020
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Monday, June 15, 2020
ቀሲስ መንግሥቱ የእናቴ ልጅ በዋልድባ
Saturday, June 6, 2020
ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ድምፀ ግንቦት ፳፯ ሐሙስ ጉባኤ
Saturday, May 30, 2020
መጋቢ አዕላፍ ሥንታየሁ ደምስ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፪
Sunday, May 24, 2020
ቤተ ክርስቲያን ለምታሳድጋቸው ችግረኛ ሕፃናት ድርጅቱ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ
- በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሳቢያ የበጎ አድራጊዎች ርዳታ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል፤
- የመርጃ ማዕከሉን በግማሽ ቀንሷል፤ ከ39 ሺሕ በላይ ሕፃናትንና ቤተሰቦችን እየረዳ ነው፤
- ከ1965 ዓ.ም. ጀምሮ 42ሺሕ ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር በሚጠቅሙ ሞያዎች አሰማርቷል፤
- በዐቅሙ ተጠናክሮ ተልእኮውን ይቀጥል ዘንድ፣ ሥራ አስኪያጁ የርዳታ ጥሪ አቅርበዋል፤
- የምግብ ግብዓቶች፣ የጽዳት፣ የመድኃኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት፣ የኮሮና ቫይረስ ባሳደረው ተጽዕኖ ሳቢያ ችግር ውሰጥ በመግባቱ፣ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ አልባ ሕፃናት እና ችግረኞች ድጋፍ ጠየቀ፡፡
ድርጅቱ ከተቋቋመበት 1965 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በአገራችን የተለያዩ ከባቢዎች፣ 36 የሕፃናት መርጃ ማዕከላትን በመክፈት፣ 42 ሺሕ ያኽል ሕፃናትን አሳድጎ ለአገር እና ለወገን በሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ሞያዎች ላይ አሰማርቷል፤ ጠቃሚ ዜጎች እንዲኾኑም አድርጓል፡፡