በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን
Saturday, April 25, 2020
የሐሙስ ሚያዚያ ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ ም ጉባኤ በመጋቢ ሐዲስ መክብብ
Thursday, April 23, 2020
ለበውክሙኑ፡ አስተውላችኋልን? ዮሐ ፲፫ ፥ ፲፩ በመጋቢ ጥበብ በዕምነት ምትኩ
ቀኖቹ ከፍተዋል፡ ዘመኑን ዋጁ በመጋቢ ጥበብ ምትኩ
Tuesday, April 14, 2020
በኢትዮጵያ ታላቅ መናወጥ ይመጣል በሙሉጌታ ውዱ ከሦስት ዓመት በፊት የተነገረ
Friday, April 10, 2020
ዘወትር ሐሙስ ዋልድባን እንታደግ ጉባኤ ዲ/ን ታዲዎስ ግርማ ያስተላለፉት ቃለ እግዚአብሔር
ዘወትር ሐሙስ ዋልድባን እንታደግ ጉባኤ ዲ/ን ታዲዎስ ግርማ ያስተላለፉት ቃለ እግዚአብሔር
ዋልድባን እንታደግ የሐሙስ ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. መርኅግብር ዘወትር ሐሙስ በጉባኤው ለመታደም ቢፈልጉ፥ የሚከተሉትን ቁጥሮች በመጠቀም በጉባኤው ተሳታፊ በመሆን በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን እንድናገኝ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁልን፤
Dial:1-848-220-3300
Pass Code: 3760937#
ዋልድባን እንታደግ
©SaveWaldba2020
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Thursday, April 9, 2020
የሙሉጌታ ዘርፉ ውዱ 2ኛ ዓመት መታሠቢያ
ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ ቆሮ ፳፩ ፥ ፶፭
የሙሉጌታ ውዱ ፪ኛ ዓመት መታሠቢያ፤ ወንድማችን ሙሉጌታ ውዱ ለቤተክርስቲያን ተሟጋች፣ ለቤተሰቡ አሳቢ ሁልጌዜ ደከመኝ የማይል በሙያው በጉልበቱ ለሃገሩ እና ለቤተክርስቲያን በሙሉ ልቡ የሚታገል ወንድም ነበር የዛሬ ሁለት ዓመት በሚያዚያ ፬ ቀን ግን፤ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ በተባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ወንድማችን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይህችን ዓለም የሚወዳቸውን ቤተሰቡን ትቶ ወደማያልፈው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሄዷል፥ ነፍሱን በቅዱሳን አጠገብ ያኑርልን።
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Wednesday, April 8, 2020
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል: በአራት የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ይተላለፋል
መጋቢት 28 ጀምሮ በየምሽቱ ከ3፡00 እስከ 4፡00 ለአንድ ወር ይተላለፋል!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰባት አብያተ እምነት መሪዎች፣ ዛሬ እሑድ፣ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ 8፡00 ላይ፣ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል፣ ስለ ብሔራዊ የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብሩ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
~~~

- ሰባቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል አብያተ እምነቶች በፈረቃ ይሳተፋሉ፤
- የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋራ መክሮ ያመቻቸው ነው፤
- ከነገ መጋቢት 28 ጀምሮ ለአንድ ወር፣ ጸሎት እና የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት ይሰጣሉ፤
- የተንሰራፋውን ግለኝነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ኢሰብአዊነትና ርኵሰት እያወገዙም ያስተምራሉ፤
- ጤናማ እና ሰላማዊ ማኅበራዊ ግንኙነት፣መከባበር እና መተዛዘን እንዲጎለብት ይመክራሉ፤
***
እውን በኢትዮጵያ መንግሥት አለ?
- ገዳማውያን ዛሬም እየተገደሉ ነው
- ስደት፣ መከራ፣ መሳደድ ቀጥሏል በዋልድባ
- ገዳማውያን ተሳደው በጎንደር ተጠልለዋል
በቅዱስ ዋልድባ ገዳም
እንደ ትላንቱ መከራው ቀጥሏል፣ ትናንት ገዳማውያን ያለ ጥፋታቸው ታሥረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተሳደዋል፣ ተገለዋል፤ ታዲያ ይሄ ሁሉ
ሲደርስ ጠቅላይ ቤተክህነቱም ምንም አለማለቱ መንግሥትም በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ዓሕመድ አማካኝነት የገዳሙን ጉዳይ እንደሚመለከቱት
ቃል ቢገቡም ሁሉም የውሃ ሽታ ብቻ ሳይሆን ከትናንት በባሰ ሁኔታ ዛሬ ጭራሽ ገዳማውያኑን እንደ ከብት አንገት ቀልቶ (አርዶ) መግደል ምን አይነት የክፋት ጥግ ነው? ለገዳማውያኑ ገና ጥንት ቤቴን ንብረቴን ሳይሉ
በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ገዳም ሲገቡ በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት ፫ ፥ ፲፬ “ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳን መከራን ብትቀበሉ እናንተ ብፁዓን ናችሁ” ተብሎላቸው ወደ
እዚህ ቀን ከሌሊት ስብሃተ እግዚአብሔር ከማይቋረጥበት ቃለ እግዚአብሔር እንደ ጅረት በሚፈስበት ገዳም የገቡት ያንን ጽድቁን ሽተው
ብለሆነ፥ ከእነሱ የሚቀር የለም እንደ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ በሰማዕትነት ክብር ተቀዳጅተው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት
እንደሚገቡ ምንም ጥርጥር የለውም።
Subscribe to:
Posts (Atom)