የገዳማቱ ህልውና


 

የዓብጽ ጾም በዓላት ክፍል ፩


የዓብይ ጾም በዓላት ክፍል ፪

 
የዓብይ ጾም በዓላት ክፍል ፫

 
የዓብይ ጾም በዓላት ክፍል ፬ የመጨረሻው ክፍል 

በዓብይ ጾም ውስጥ የሚከበሩ የንግሥ በዓላት ላይ ከበሮ እየተመታ፣ በቸብቸቦ መዝሙሮች የሚከበሩ በዓላት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ጋር ይጻረራል፣ ስለዚህ በዓብይ ጾም ወቅት የሚከበሩ በዓላት ተለዋጭ በዓላት አላቸው በሥርዓት የተሰራላቸው እነዚህም በዓላት መካከል ጥቂቶቹ
  • የመጋቢት መድኅዓኒዓለም ክብረበዓል
  • የየካቲት ኪዳነ ምሕረት
  • የመጋቢት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ) 
ስለእነዚህ ሊቃውንቱ ምን ይላሉ በማር ፕሮዳክሽን የቀረበ ተከታታይ ትምህርቶች ስላሉ ተከታተሉ
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የጌታችን የመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በCNN ጋዜጠኛ በጎንደር ከተማ በተዘገበበት ወቅት


 --------------------------------------------------------------------------------------------

Ethiopian monasteries by Getachew Bekele tells the socio economic benefits of Ethiopian monasteries. It also address the potentials and major problems the monasteries are facing today. Mr. Getachew has forwarded recommendations how Ethiopian can maximize benefits from its monasteries by taking the right managment instrument.  


  • -------------------------------------------------------------------------------------------------

የዋልድባ ገዳም አመሠራረትና ታሪክ፣ ዋልድባ ገዳም በዛሬማ፣ በማይዘሁል፣ በእስያ፣ እና በተከዜ ወንዞች የተከበበ ታሪካዊ ገዳም ነው፣ ገዳሙም ከተመሠረት ከ1600 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በአሁን ሰዓት በውስጡ ከ3000 በላይ መናኒያን ሲኖሩ (ስውራኑን መናኒያን ሳይቆጠር) የሚሩበት ገዳም ነው በገዳሙ ውስጥ ስቋር፣ አበረንታት፣ አባ ነፃ፣ ደሻል፣ ቤተ ሚናስ፣ የሚባሉ ገዳማት ያሉበት ቦታ ነው። በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ መንግሥት የስኳር ፋብሪካ እንዲሁም ፖርክ ይዞታ እንገነባለን በማለት በዚህ በቅዱስ ቦታ ላይ በግምት ወደ 50,000 ሰዎችን ለማስፈር በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፣ እንደ መንግሥት ገለጻም በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ ግንባታው ከተጠናቀቀ ዋልድባ የሚባለው ቅዱሱ እና ከገዳማት ሁሉ ታሪካዊውና ቅዱሱ ገዳም ለመጨረሻ ግዜ ሕልውናው በከባድ ጥያቄ ላይ ይወድቃል።
መንግሥታችንን የምንጠይቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ያልታረሱ እና ያልለሙ ድንግል መሬቶች እያሉ ወንዞቹም የሰውን ሃገር የሚያጠጡት እንደነ ዋቢሸበሌ አባይ እንዲሁም ተከዜ እያሉ ለምን ወደ ዋልባ ገዳም ድረስ በመምጣት ይህንን እኩይ ሥራ ለመሥራት ተገደዳችሁ? የሳዑዲ ገንዘብ ወይስ እግዚአብሔርን መዳፈር? መልሱን ለመንግሥታችን እንተወውና. . .
እያንዳንዱ ሀገር ወዳድ፣ የቅርስ እና የትውፊት ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኦርቶዶክስ እስላም ክርስቲያን በሙሉ የቅርስ ተቆርቋሪ የሆናችሁ በሙሉ ለዚህ ሀገረዊ ጥሪ በያላችሁበት ሀገራዊ ምላሻችሁን እንደምትሰጡ እናምናለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃት አሜን
                                                                        ክፍል ፪

                                                                       ክፍል ፫

1600 ዓመታትን ያስቆጠረው የዋልድባ ገዳም፥ ዛሬ በስኳር ፋብሪካና የፖርክ ይዞታን ለመከለል በሚል ሽፋን ጥፋት፣ ማፍረስ፣ እንዲሁም ለሃገራችን እና ለመላው ዓለም የሚጸልዩ መናኒያይን ባዕታቸው ተደፍሯል። ቅዱሱን ገዳም በግድም በውድም ለማፍረስ መንግስት ተነስቷል። ስለዚህ እያንዳንዱ ሀገር ወዳድ የሃይማኖቱ ተቆርቋሪ ልንጮህ እና ድምጻችንን ልናሰማ ይገባል። 
የገዳሙ አመሠራረት እና ታሪክ ባጭሩ ክፍል ፬ኛው እና የመጨረሻው ክፍል።


በገዳማቱ ላይ እየደረሰ ያለው ጥፋት ባጭሩ

No comments:

Post a Comment