Friday, October 22, 2021

የአባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ራብዓይ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኃላፊ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት እና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የሲዳማ ክልል፣ የጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፡-

 በዚህ ሐዋርያዊ ጉባኤ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ተልእኮ እንድንወያይ በየጊዜው የሚሰበስበን እግዚአብሔር አምላካችን ከዚህ ዕለትና ሰዓት ስላደረሰን ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ወደዚህ ዓመታዊ ዓቢይ ጉባኤ እንኳን ደhና መጣችሁ።

<<ዕቀብ ማኅፀንተከ ዘተወፈይከ ከመ ትስብክ ቃሎ ቀዊመከ>> ቆመህ ቃሉን ትሰብክ ዘንድ የተቀበልከውን አደራ ጠብቅ”1 ጢሞ 4፡14)፡፡

 በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው በዓለም ያለው ኃላፊነት ሁሉ መንፈሳዊውም ሆነ ሥጋዊው ያለ አደራ የሚሰጥ አይደለም። ይልቁኑም ለቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አደራ ከሁሉም የላቀ እንደሆነ አንስተውም። ምክንያቱም ከሰው ሳይሆን በቀጥታ ከእግዚአብሔር የተሰጠ አደራ ከመሆኑም በተጨማሪ በሰማይም ሆነ በምድር ገደብ የለሽ  ኃላፊነት በመሆኑ ነው። ሌላው ተልእኮ የምድሩን ብቻ ሆኖ ከዚያም በጂኦግራፊ ወይም በመልክዐ ምድር ወይም በድንበር ወይም በሥጋዊና ዓለማዊ ጉዳዮች የተገደበ ነው የቅዱሰ ሲኖዶስ ተልእኮ ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው። በምድር ላይ ምንም ዓይነት ድንበርና ወሰን ስለሌለው ገደብ የለሽ ነው። ምክንያቱም ራሱ አደራ ሰጪው አምላክ <<ሑሩ ወመሀሩ ውስተ ኲሉ አጽናፈ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኲሉ ፍጥረት>> ወደ ዓለም ዳርቻዎች ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ”በማለት አዞናልና ነው። ተልእኮው ይህ ከሆነ ዘንድ ኃላፊነቱም በዚህ ልክ ተሰጥቶናል ማለት ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ አደራ በመንፈስ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ምእመናንን በነፍሳቸውም ሆነ በሥጋቸው በምልአት መጠበቅን የሚመለከት ነው። ማለትም ተልእኮአችን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑት ምእመናን በምድርም ሆነ በሰማይ፣ በሥጋም ሆነ በነፍስ ለጉዳት እንዳይጋለጡ መጠበቅ ነው ማለት ነው፡፡

Saturday, March 27, 2021

በዋልድባ አበረንታንት ገዳም የወሬ ዘመቻ ተከፍቶበታል

የዋልድባ አበረንታንት አባቶች በሥራ ላይ

በዋልድባ አበረንታንት ገዳም የወሬ ዘመቻ ተከፍቶበታል

·       ዋልድባ ከ1000 በላይ መነኮሳት ተሰደዋል

·       ዙ መነኮሳት ተገለዋል

·       ፋኖ ሃይል በገዳም በመግባት ድብደባ ፈጽሟል በማለት የሐሰት ዜናዎችን በማሰራጨት የተጠመዱ መነኮሳት በምዕራቡ አለም

ዋልድባ አበረንታንት ገዳም ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን ማሳለፉን፣ በተለይ የቀድሞው የዘራፊው መንግሥት ኦርቶዶክሳውያንን ለመጉዳት ይልቁንም የሃይማኖታችንን መሠረት የሆነውን የዋልድባ አበረንታንት ገዳምን እንዲነጥፍ ያላሰለሰ ጥረት ሲያድጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፤ የሥኳር ፋብሪካን እናቋቁማለን በሚል፣ የወርቅ ማውጫ በሚል፣ የእምነ በረድ ፋብሪካ እንገነባለን በሚል፣ የእጣን አዘጋጆች በሚል በተለያየ መልኩ ገዳሙን እና ክብሩን ባልጠበቀ ሁኔታ ብዙ ደባ ሲፈጸም እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።