Monday, April 30, 2012

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መጓዛቸውን ኢሳት ዘገበ፣


 • "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ብሏል የኢሳት ዜና፤
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 ዓ.ም፤ April 30/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦፦ “በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መትመማቸውን እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን” ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ዘገባው አስታወቀ። “የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ያለው ዜና ተቋሙ የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም” ሲል አክሏል።

ዘገባው ቀጥሎም “ከ5ሺ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም ርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግትና ዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት” መግለጡን አብራርቷል።

Saturday, April 28, 2012

ዋልድባ አሁንም አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው (ጥልቅ ሪፖርታዥ)


READ THIS ARTICLE IN PDF.
·         ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከፓትርያሪኩ እና ከመንግሥት ጋራ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 
·     ማኅበሩ የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ላይ ስለሚያደርሰው ተጽዕኖ ያጠናቀረውን ሪፖርት አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል::
·     “እስከ 20 ሄ/ር የገዳሙ መሬት በግድቡ ውኃ ይሸፈናል፤ ፕሮጀክቱ የገዳሙን 40% የምርት ገቢ 60% የምእመናን ድጋፍ ያሳጣዋል” (የማኅበሩ አጥኚ ቡድን ሪፖርት)::
·       ማኅበሩ የፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚለወጥበት እስከ ዲዛየን ማሻሻያ የሚደርስ የጥናት አማራጭ እንዲያቀርብ፣ ገዳማውያኑ ስለ ፕሮጀክቱ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ያላቸው ሐሳብ የሚደመጥበት አቋማቸውንም ያለጫና የሚያሳውቁበት መድረክ እንዲያመቻች ተጠይቋል::
·        የስኳር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክትና ፋብሪካ ማኔጅመንት የአቅም ማነስ ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል::
·     “ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ ከመግባታችን አስቀድሞ መነኰሳቱን እንደ መንግሥት በአለማነጋገራችን አጥፍተናል፤ እነርሱን [የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን] ማማከር ነበረብን፡፡” (የፕሮጀክቱ ሓላፊዎችና የወረዳው ባለሥልጣናት)::
·         መንግሥት የፕሮጀክቱን የጥናት ሰነዶች ይፋ ያድርግ (አንድ የኢንቫይሮመንታል ዲዛይን ምሁር)::
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 19/2004 ዓ.ም፤ April 27/2012 )፦ መንግሥት በክልል ትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ በሚገኘው የዛሬማ፣ ዱቁቆ እና ተከዜ ሸለቆ በሚያካሂደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የተነሣ ከአገራችን ታላላቅና ቀደምት ቅዱሳት መካናት አንዱ በኾነው በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የተጋረጠው አደጋ ለብዙኀን መገናኛ ዘገባ ከዋለ ድፍን ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡

Thursday, April 26, 2012

ማስታወቂያታላቅ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ስለ ታላቁ ዋልድባ ገዳም በሳን ሆዜ 
ቦታው                                                      ቀንና ሰዓት
2500 Masonic Drive                           እሑድ April 29, 2012
San Jose, CA 95125                          ከ 2:00 PM. - 5:00 PM. 

ለተጨማሪ መረጃዎች ይደውሉ
408-582-4299
408-218-6904
408-421-5163
408-417-2329

Friday, April 20, 2012

በዋልድባ መንግስት ሬሳ መልቀምን ተያይዞታል


አጽመ ቅዱሳንን ማፍለቱ እንደቀጠለ ነው

አንድ አድረገን ሚያዚያ 11 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ጉዳይን በቅርቡ በአካል ቦታው ድረስ ሄደው የተመለከቱት ሰዎች ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በጥቂቱም ቢሆን ያዩትንና የሰሙትን አካፍለውናል ፤ ቦታው በፖሊሶች እንደተከበበ ገዳሙ የጸሎት ቦታ መሆኑ የቀረ እስኪመስል ድረስ የጦር አውድማ በሚመስል መልኩ በታጠቁ ወታደሮች ተከቧል ፤ አበው መነኮሳቱን ከበአታቸውን እንደ ወንጀለኛ  በጠገበ ወታደር እያዳፉ ሲወስዷቸው በዓይናቸው ተመልክተዋል ፤ በተነሳ ጥያቄ መሰረት ጥይት ተኩሰውባቸዋል ፤ ስውራን አባቶችም እናንተ ባላችሁበት ጸልዩ በማለት ቦታው ላይ በተገኙ ወንድሞቻችን አማካኝነት ለእኛ መልዕክት አስተላልፈውልናል ፤ መንግስትስም ለፕሮጀክቱ መፋጠን መኪኖችን ወደ ቦታው እያመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ባለፈው ቅዳሜ 08-08-2004 ዓ.ም በቪኦኤ ላይ የገዳሙን አንድ አባት አግኝተው እንዳናገሯቸው መንግስት አሁንም አጠናክሮ ስራውን እየሰራ መሆኑን ለቪኦኤ አስረድተዋል ፤ በፊት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት አባት አንዳች ስህተት እንዳልሰሩ የተናገሩት ሁሉ ትክክል እንደሆነ ተነግሯቸዋል ፤ ግን ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ አክለው ገልጸዋል፡፡ ብጹእ አቡነ ጳውሎስና ጥቂት ጳጳሳት ለገዳሙ አባቶች ያልተከፈተ ጆሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚሰጡት ወቅታዊ አስተያየት የላይኛውን የተወካዬች ምክር ቤት ወንበር ተቆናጥተውት በኢቲቪ ተመልክተናል ፡፡


Wednesday, April 18, 2012

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ ይበልጡኑ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ ይበልጡኑ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል
 • በተለያዩ የአሜሪካን ስቴቶች ውይይቶች፣ ስብሰባዎች፣ ሰላማዊ ሰልፍ ታቅዷል
 • በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን እንዲሁም አባቶች በአጠቃላይ ወደ አንድ አቋም  እየመጡ ነው (መንግስት በአስቸኳይ በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚያደርሰውን እንግልት፣ ማሳደድ፣ ማፍረስ፣ እንዲያቆም ተጠይቋል)
 • በኒውዮርክ፣ በሳን ሆዜ፣ በቶሮንቶ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሰላማዊ ትዕይንት እንዲሁም ውይይቶች እንደሚደረጉ ተነግሮናል፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳመ ዋልድባ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በተለየ መልኩ የሀገርን ሃብትና የወገንን
 ቅርስ ለማጥፋት ከጥፋት ሃይሎች ጋር በመሰለፍ በተለይ ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ እና ትውፊት ያለውን የዋልድባ ገዳም አካባቢ የስኳር ፋብሪካ እገነባለሁ፣ የፖርክ ክልል እከልላለሁ በማለት አያሌ ሰቆቃዎችን እያደረሰ ይገኛል። በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በገዳሙ በጸሎት ተወስነው ያሉትን አረጋዊያን ገዳማዊያን በማንገላታት፣ ከጸሎታቸው በማስተጓጎል፣ በውጪ ሚዲያ የተናገሩትን አውጡ በማለት በገዳሙ ቅጽር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ክብራቸውን በሚነካ መልኩ ወታደሮች ወደ መቅደሱ በጫማቸው በመግባት፣ መናኒያኑን ማንገላታቱን ቀጥለውበታል። ወደ አካባቢው ለጸሎት እንዲሁም ከአካባቢው በረከት ለመቀበል ወደ ቦታው ሄደው የነበሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ብዙ እንግልት እና ማስፈራራት ደርሶባቸው እንደተመለሱ በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ወጥቶ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

የዋልድባ ገዳም ህልውና "ሳይቃጠል በቅጠል"

ከዘላለም ወልደኢትዮጵያ

የዋልድባ ገዳማውያን

መቼም ልምድ ነውና ልምድ ብቻ አይደለም ባህላችንም ነውና በሰላምታ ልጀምር፡፡ውድ ኢትዮጵውያን ወገኖቼ እንደምን አላችሁ ኑሮስ አንዴት ነው? አለን መቼስ "ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል" እንደምትሉ ይገባኛል፡፡
ውድ ወገኖቼ እኔ ቃላትን ከቃላት አሳክቼ መፃፍም ሆነ ማንበብ አልችልም፤ ነገር ግን ግድ ሆነብኝና ለትምህርት የምጠቀምባትን ብዕሬን አውጥቼ ይህችን ጦማር ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፡፡ ግን ግራ ገባኝ ለማን ነው ምፅፈው? ምን አገባኝ ልፃፈውና እንደኔ የቆረቆረው ካለ የሃሳቤ ተካፋይ ይሁን ባይሆን እንኳን ህሊናዬ ትንሽ እረፍት ያገኝ ዘንድ እንደ አንድ ዓመት ህፃን ዳዴ ማለት ጀመርሁ፡፡ነገሩ እንዲህ ነው ሰሞኑን ታላቁ የዋልድባ ገዳም ህልውና አደጋ ላይ መሆኑን የግል መገናኛ ብዙሃን እያሳዩንና እያስነበቡን ይገኛሉ፡፡በእርግጥ ይህ ዜና እውነት ነው፤ ስለሆነም እንዳባቶቻችን "የሰይጣን ጀሮ አይስማው" ብለን ምናልፈው አልሆነም፡፡ይልቅስ ሰውም ሰይጣኑም ከሰማው ዋለ አደረ፡፡

ፒቲሽኑን ይፈርሙ!


Tuesday, April 17, 2012

ሪፖርታዥ፦ የዋልድባ መድኃኔዓለም ተሳላሚዎች ምስክርነት


 • READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • ገዳሙ በከፍተኛ የፖሊስ ኀይል ስምሪት ውስጥ ወድቋል
 •  መነኰሳት በአባትነታቸው አይከበሩም፤ ይዘለፋሉ፤ ይታሰራሉ፤ ጸሎተ ምሕላ በማኅበር እንዳያደርሱ ተከልክለዋል
 • ከአንድ ኪ.ሜ ያላነሰ የገዳሙ መሬት የፕሮጀክቱ አካል ኾኗል
 •  “ስለሚታረሰው አያገባችኹም፤ ስለተተኮሰባችኹና ስለተደበደባችኹት አያገባንም” /አቡነ ኤልሳዕ ለተሳላሚዎቹ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ/። 
 •  “እውነቱን ከማኅበረ ቅዱሳን ልኡካን ሪፖርትና መግለጫ እንጠብቃለን” /ተሳላሚ ምእመናኑ/

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 8/2004 ዓ.ም፤ April 16/2012)፦ መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ.ም፤ የመድኃኔዓለምን በዓል በአብረንታንት ዋልድባ ገዳም ለማክበር ወደዚያው ለማምራት ተዘጋጅተናል፡፡ መነሻችን ከጎንደር ከተማ ነው፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋራ ሲነጻጸር ዘንድሮ  የተሳላሚው ቁጥር አንሶ ይታያል፤ ከጉዟችን በፊት መንገዱ እንደሚዘጋና በርካታ የፌዴራል ፖሊስ ኀይል እንደተላከ አብዝቶ በመሰማቱ የቀረው ሰው ብዙ ነው፡፡

Monday, April 16, 2012

የስልክ ኮንፈረንስ በመጪው ሐሙስ April 19, 2012

 


በላስቬጋስ የሚገኘው የዋልድባን እናድን ግብረኃይል ዘወትር ረቡዕ የሚያዘጋጀውን የስልክ ኮንፈረን ዛሬም በመጪው ሐሙስ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ይገኛል። በተለያየ 
የአሜሪካን እና የዓለም ግዛት የምትገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን  ልጆች እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የሀገር ቅርስ ወዳጆች፣ ላልሰሙ ወገኖቻችን በማሰማት የበኩልዎን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን በታላቅ ትህትና
 እናቀርባለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን።

ያስታውሱ የስልክ ቁጥሩን
559-726-1200 በመደወል 157715# የመግቢያ ቁጥሩን ይጠቀሙ
ጥያቄ ለመጠየቅ ወይም አስተያየት ለመስጠት በኮንፈረንሱ ላይ 
*6 በመቀጠል 1 ቢጫኑ በተራዎት መሰረት ጥያቄዎችን ተቀብለን እናስተናግዳን።
ቸር ያሰማን አሜን

Thursday, April 12, 2012

በቪኦኤ የቀረቡትን ካልጠቆማችኹ በሚል ሦስት ገዳማውያን ታስረው ተፈተዋል::

 • እስሩናአደኑየቤተሚናስመነኰሳትበተለይም1997 .ወዲህለሚደርስባቸውልዩጫናግልጽአመልካችነውተብሏል::
 • 1980 .የገዳሙንሰሜናዊክፍል (በእንስያወንዝ) የጦርካምፕለማድረግየተቃጣውሙከራበኅቡኣንአበውኵናትመወገዱተነግሯል::
 • አባ ሳሙኤል ዘ
     
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 29/2004 .ም፤ April 7/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF) የመንግሥት ባለሥልጣናት በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ ከሚያደርሱባቸው ወከባና ማስፈራሪያ እንዲታቀቡ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሦስት የገዳሙ ማኅበር አባላት በፖሊስ ታስረው መፈታታቸው ተሰማ፡፡ መነኰሳቱ ለእስር የተዳረጉትለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት አባት የት እንዳሉ ተናገሩከሚል የፖሊስ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ መረጃ ኮማንደር በየነ በሚባል የፀለምት ወረዳ ፖሊስ መጋቢት 23 ቀን 2004 . ከገዳሙ የተወሰዱት ሦስቱም ታሳሪዎች በገዳሙ በዲቁና የሚያገለግሉ ሲሆኑ ከሦስቱ ሁለቱ መናንያን መሆናቸው ተገልጧል፡፡

ዋልድባ


መናኒያን በዋልድባ ገዳም

የዋልድባ ገዳም የሚገኘው በሰሜን ተራራዎች እግር ስር ነው፣ የዋልድባ ገዳም የተመሠረተው በ፬ኛው ምዕተ ዓመን እንደነበር ሲያያዝ የመጣው ትውፊታዊ ታሪክ ያስረዳል። የዋልድባን ገዳም ያደራጁና የተባሕትዎን ኑሮ ያጠናከሩ ቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ናቸው።እርሳቸውም በ14ኛው ማለቂያና በ15ኛው መጀመሪያ በአፄ ዳዊት ከ1365 - 1395 ዓ.ም. በዋልድባ ኑረዋል። አንድ የመነኩሳት ቡድን ከደብረሊባኖስ ተንቀሳቅሶ ዋልድባ ደርሷል፥ የቡድኑም አባላት አባ ሙሴ፣ አባ አናንያ፣ አባ እስጢፋኖስ፣ አባ ገብረ መስቀል፣ አባ ገብረ ክርስቶስ ነበሩ። እነዚህ አባቶች የገዳሙን ኑሮ መልክ በመስጠት ቋሚና ዘላቂ ሥራ ሠርተዋል።

Tuesday, April 10, 2012

በዋልድባ የመጀመሪያው ምልክት

ልብ ያለው ልብ ይበል!
መቅሰፍት ፩ ጀምሯል! መንግስት "ቅዱሱን ገዳም አንነካውም" በማለት ሥራውን ቀጥሏል፥ ነገስ ምን እንደሚመጣ እናውቃለን?


አቤቱ የሆነብንን ሁሉ አስብ

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 1 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ ላይ የሚሰራው ስኳር ፋብሪካ ውዝግቡ ያለ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው ፤ መንግስት አልደረስኩም በማለት ስራውን እያከናወነ ይገኛል፤ አባቶችም በጸሎት እየበረቱ ይገኛሉ ፤ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት  በቦታው ላይ ያለው ስራውን የሚያከናውን ተቀጣሪ መሃንዲስ ባልታወቀ ምክንያት ሞቷል ፣ ስው ለመስራት የተቀመጡ  ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎቹ በየሰአቱ እየተበላሹ ይገኛሉ ካልታወቀ ቦታ የተለያዩ አውሬዎች እየወጡ ሰራተኛውን መተናኮል ጀምረዋል ፣እነዚህን እና የመሳሰሉት መከራዎች በቦታው በስራ ላይ በስራ በሚገኙ ሰዎች ላይ እየደረሰ ነው፡፡
 ¨ሰው ሲጨርስ ባለቤቱ ስራ ይጀምራል¨  መዝሙረ ዳዊት 12፤4 ‹‹እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋም›› ተብሎ ተፅፏል ፤ እውነት ነው አምላካችን አያንቀላፋም ፤ ይህ ምልክት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም ፤ አሁንም ከእኩይ ምግባራችሁ ትመለሱ ዘንድ መልዕክታችን ነው ፤ የዘመናችሁ መጨረሻ መጀመሪያ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡  1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፤12 ‹‹ ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ›› ቤተክርስትያን ላይ እጁን አንስቶ በሰላም የኖረ ስልጣነ መንግስቱ የተደላደለለት መንግስት ባለፉት 2000 ዓመታት  አላየንም ፤ መልካቸው እየቀያየሩ ብዙዎች ተነስተውባታል ፤ የተነሱባት ሁሉ አሁን ስም አጠራራቸው የለም እሷ ግን አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች ፤ ይህች ቅድስት ቤተክርስትያን ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማቴዎስ ወንጌል 18 ፤18 ‹‹ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።›› ብሎ ተናግሮላታል ፤ ወደፊት የሚከሰተውን እየተከታተልን እናንተው ዘንድ እናደርሳለን

(ማስታወቂያ) በዋሽንግተን ዲሲ:- መንፈሳዊ የውይይት መድረክ

“ የአባቶቼን ርስት እሰጥ ዘንድ ከእኔ ይራቅ”
(መጽ. ነገሥት ቀዳ. ፳ ፥ ፫) 
 የዋልድባ ገዳምን ለመታደግ የሰላማዊ ሰልፍ ያስተባበረው ኮሚቴ ሁለተኛውን ክፍልና ቀጣዩን ሂደት ለመጠቆም እና ለመወያየት ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ስብሰባ የሆሳዕና ዕለት ተዘጋጅቷል። እርስዎም በቦታው ተገኝተው የበኩልዎን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።


        ቦታ:                                                ቀንና ሰዓት
St. George Ball Room                      3:00 - 8:00 PM. April 8, 2012             4335 16th Street. NW.                ፱:፴ - ፰ ከሰዓት በኋላ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም.
Washington, DC 20011

ለቪኦኤ የተናገሩት የዋልድባው አባት በፖሊስ እየታደኑ ነው


 • ያሉበትን ካልጠቆማችኹ በሚል ሦስት ገዳማውያን ታስረው ተፈተዋል::
 • እስሩና ‹አደኑ› የቤተ ሚናስ መነኰሳት በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ለሚደርስባቸው ልዩ ጫና ግልጽ አመልካች ነው ተብሏል::
 • በ1980 ዓ.ም የገዳሙን ሰሜናዊ ክፍል (በእንስያ ወንዝ) የጦር ካምፕ ለማድረግ የተቃጣው ሙከራ ኅቡኣን አበው ኵናት መወገዱ ተነግሯል::
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 29/2004 ዓ.ም፤ April 7/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንግሥት ባለሥልጣናት በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ ከሚያደርሱባቸው ወከባና ማስፈራሪያ እንዲታቀቡ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሦስት የገዳሙ ማኅበር አባላት በፖሊስ ታስረው መፈታታቸው ተሰማ፡፡ መነኰሳቱ ለእስር የተዳረጉት “ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት አባ የት እንዳሉ ተናገሩ” ከሚል የፖሊስ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ መረጃ ኮማንደር በየነ በሚባል የፀለምት ወረዳ ፖሊስ መጋቢት 23 ቀን 2004 ዓ.ም ከገዳሙ የተወሰዱት ሦስቱም ታሳሪዎች በገዳሙ በዲቁና የሚያገለግሉ ሲሆኑ ከሦስቱ ሁለቱ መናንያን መሆናቸው ተገልጧል፡፡

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)


 • በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ::
 • በሊቀ ጳጳሱ አቋም ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዟል::
 • በዋልድባ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ እንዳይደርሱ በፖሊስ ታግደዋል::
 • የማኅበረ ቅዱሳን አጥኚ ቡድን ነገ ወደ ዋልድባ ያመራል::

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 24/2004 ዓ.ም፤ April 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች ጥምረትና የጥምቀት በዓል አከባበር ወጣቶች ማኅበራት ጥምረት ኮሚቴዎች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የስድስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጋራ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡

አቤቱ የሆነብንን አስብ

በዝቋላ አቦ ገዳም የደረሰውን የሚያሳይ ስዕላዊ መግለጫ

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ (ክፍል አንድ)


·         ስብሰባ የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ
“ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)።
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት” በዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ “የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማት” የሚል ስብሰባ ትንት መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል


 • ምእመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው መቆም ያለባቸው ጊዜ ላይ መደረሱ ተወስቷል፡፡
 • ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይቀጥላል።
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በዋልድባ እና በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ የተቀሰቀሰው ቁጣ በሕዝባዊ ውይይቶች ታጅቦ እየቀጠለ መሆኑን የሰሜን አሜሪካ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በመላው የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ኮንፈረንስ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ እያደረገ ባለው በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የምእመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስለ ዋልድባ ይዞታ መደፈር ወይም ስለ ዝቋላ እና አሰቦት ገዳማት የእሳት አደጋ ብቻ ሳይሆን “በጠቅላላው ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ነው መነጋገር ያለብን” ወደሚለው ገዢ ሐሳብ በመምጣት ላይ ናቸው ተብሏል።


በዚሁ በፈቃደኛ ምእመናን በተጠራው እና በልባቸው በየቤታቸው ሲቃጠሉ የነበሩ ምእመናንን እየቀሰቀሰ በመጣው የስልክ-ጉባኤ አያሌ መሠረታዊ ጥያቄዎች በመነሣት ላይ ናቸው። “እኔ ምንም የሌለኝ አንድ ደካማ ሰው ነኝ” ሲሉ የጀመሩ አንድ ምእመን እንዲህ አሉ። “ስለ ዋልድባ ጉዳይ የአካባቢው ባለሥልጣን ሲናገሩ ሰምቻለኹ። መነኮሳቱም ሲናገሩ ሰምቻለኹ። እንግዲህ ይህ ገዳም ለሁለት ሺህ ዓመት የቆየ ነው። እንዲያው ምንም ችግር ከሌለ እንዴት ገዳማውያኑ እስከ አዲስ አበባ፣ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ ለመሔድ ይነሣሉ?” ሲሉ ተጠየቃዊ ሐሳብ አቅርበዋል። አክለውም “እኔ ስለዋልድባ ብቻ አይደለም የምናገረው። ከዚህ በፊት አኩሱም ላይ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ከዚያ ሰው ሞተ። የሚገርመው ገዳዩ ማን ነው ሳይባል ሁከቱን የቀሰቀሰው ማን ነው? ይቅርታ ይጠይቅ የሚል ነገር ተነሣ። ይህ መንግሥት (ኢሕአዴግ) ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ሀሳብ መጠየቅ አለብን። በዚህ በ20 ዓመት ውስጥ የሌሎች እምነቶች ንብረቶች እንዲህ ሆኑ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ነው የሚጠፋው። የሚቃጠለው። ይህ እኮ ሕጋዊ ጥያቄም ነው። መንግሥት ለእምነቶች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት። ለዜጎች። የዋልድባ መነኮሳት ከተማን ሸሽተው፣ ዓለምን ንቀው ነው የሄዱት። ለከተማ ለከተማማ በየከተማው ባሉ አብያተ ክርስቲያናት መኖር ይችሉ ነበር እኮ። እነርሱም ዜጋ ናቸው። መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል” ሲሉ ልብ የሚነካ ንግግር አድርገዋል።

“ሥር ነቀል የምእመናን እንቅስቃሴ ነው የሚያስፈልገው” ያሉ ሌላ ተናጋሪም ኮፕት ቤተ ክርስቲያንን በአብነት በመጥቀስ ምእመኑ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት፣ አባቶችን ብቻ በመጠበቅ ጊዜው እንዳያልፍበት፣ እስካሁን ጠብቆ ምንም ያገኘው ነገር አለመኖሩን፣ በመላው ዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት በመነሣት ቤተ ክርስቲያናቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው አስረድተዋል። “ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ በአገር ቤት አስተዳደር ስር ያለ እያልን ተበታትነን ቀረን። የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ፖለቲካ እየሠሩ ነው። እኛ እነርሱን ተከትለን መጥፋት የለብንም” ካሉ በኋላ “አሁንም በፍፁም ንጽህና ፣ በንፁህ ልብ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ መሥራት አለብን። ፖለቲከኞች አሁን እኛን ተዉን። ፖለቲካችሁን ሌላ ቦታ ውሰዱ። እኛ የምንሠራው ለቤተ ክርስቲያን ነው” ብለዋል።

አክለውም “ሁላችሁንም በእግዚአብሔር ስም አንድ ነገር እለምናችኋለሁ። ከዘረኝነት ራሳችንን እናጽዳ። ዘር ለዱባና ለድንች እንጂ ሁላችን ከአንድ ከክርስቶስ ከማይጠፋው ዘር የተወለድን ነን” ሲሉ በሰሜን አሜሪካ ትልቅ በሽታ የሆነውን የዘረኝነትን ጉዳይ በቀጥታ አንሥተዋል።ሌሎች ተናጋሪዎችም በይዘት ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ብዙ ሐሳብ ጠቅሰዋል።

ጉባኤው በዚሁ ቀጥሎ ሰላማዊ ሰልፎችን መቀጠል እንደሚገባ፣ በየአካባቢው የምእመናን አስተባባሪ ኮሚቴዎችን ማቋቋም እንደሚያስፈልግ፣ ይህ ሁሉ ችግር በእግዚአብሔር ቸርነት ይወገድ ዘንድ እና የተጀመረው እንቅስቃሴም ፍሬ እንዲያፈራ የምሕላ ጸሎት መደረግ እንዳለበት፣ ጊዜያዊ ችግር ያለባቸው ለዝቋላ እና ለደብረ አሰቦት ዓይነት ገዳማት የተጀመረው ርዳታ ማስተባበር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በረዥም ጊዜም ዓለም አቀፍ የሆነ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ፋውንዴሽን መቋቋም እንዳለበት የቀረበው ሐሳብ በዓላማነት ተቀምጧል።

ይኸው የምእመናን መነሣሣት እና ሕዝባዊ ውይይት በሌሎች አህጉሮች ማለትም በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በአፍሪካ እና በአረብ አገሮች ወዘተ ባሉ ምእመናን ዘንድም ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

ር ወሬ ያሰማን
 አሜን፡፡

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ


አርእስተ ጉዳዮች፡-
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም፤ ማርች 28/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦
·         ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የዋልድባ ገዳም ይዞታ መደፈርን የተቃወመ ሰላማዊ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ


·         ኤምባሲው ለሙስሊም ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊ ወገኖቻችን ያሳየውን ከበሬታ ለክርስቲያኖቹ አለማሰየቱ ግርምት ፈጥሯል፤
·         “መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይንቃታል፤ ክርስቲያኑንም ይንቃል” (ሕዝብ)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 18/2004 ዓ.ም፤ ማርች 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የኢሕአዴግ መንግሥት በዋልድባ እና አካባቢው  በግድብ ሥራ፣ በፓርክ እና በስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስም የሚያካሒደውን ገዳሙን ድንበር፣ ትውፊት እና መንፈሳዊ ይዞታ የመግፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ላሉ ገዳማውያን አበው እና እመው ያላቸውን አለኝታነት ለመግለጽ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሰለፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

Ethiopian Christians Protest in DC (የአሜሪካ ድምጽ ሪፖርታዥ)

የደጀ ሰላም ሪፖርታዥ