Friday, April 20, 2012

በዋልድባ መንግስት ሬሳ መልቀምን ተያይዞታል


አጽመ ቅዱሳንን ማፍለቱ እንደቀጠለ ነው

አንድ አድረገን ሚያዚያ 11 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ጉዳይን በቅርቡ በአካል ቦታው ድረስ ሄደው የተመለከቱት ሰዎች ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በጥቂቱም ቢሆን ያዩትንና የሰሙትን አካፍለውናል ፤ ቦታው በፖሊሶች እንደተከበበ ገዳሙ የጸሎት ቦታ መሆኑ የቀረ እስኪመስል ድረስ የጦር አውድማ በሚመስል መልኩ በታጠቁ ወታደሮች ተከቧል ፤ አበው መነኮሳቱን ከበአታቸውን እንደ ወንጀለኛ  በጠገበ ወታደር እያዳፉ ሲወስዷቸው በዓይናቸው ተመልክተዋል ፤ በተነሳ ጥያቄ መሰረት ጥይት ተኩሰውባቸዋል ፤ ስውራን አባቶችም እናንተ ባላችሁበት ጸልዩ በማለት ቦታው ላይ በተገኙ ወንድሞቻችን አማካኝነት ለእኛ መልዕክት አስተላልፈውልናል ፤ መንግስትስም ለፕሮጀክቱ መፋጠን መኪኖችን ወደ ቦታው እያመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ባለፈው ቅዳሜ 08-08-2004 ዓ.ም በቪኦኤ ላይ የገዳሙን አንድ አባት አግኝተው እንዳናገሯቸው መንግስት አሁንም አጠናክሮ ስራውን እየሰራ መሆኑን ለቪኦኤ አስረድተዋል ፤ በፊት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት አባት አንዳች ስህተት እንዳልሰሩ የተናገሩት ሁሉ ትክክል እንደሆነ ተነግሯቸዋል ፤ ግን ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ አክለው ገልጸዋል፡፡ ብጹእ አቡነ ጳውሎስና ጥቂት ጳጳሳት ለገዳሙ አባቶች ያልተከፈተ ጆሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚሰጡት ወቅታዊ አስተያየት የላይኛውን የተወካዬች ምክር ቤት ወንበር ተቆናጥተውት በኢቲቪ ተመልክተናል ፡፡
ከዚህ በፊት በቦታው ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት አንድ መሀንዲስ መሞቱን ገልጸን ነበር ፤ ከየት እንደመጡ ባልታወቁ ከዱር የወጡ አውሬዎች ቦታው ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችን እየተተናኮላቸው መሆኑን አክለን ገልጸናል ፤ አሁን ደግሞ በቦታው ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ስራውን እየሰሩ ባልታወቀ ምክንያት በየቦታው እየተፈነገሉ ይገኛሉ ፤ በቦታው ላይ የሟች ቁጥር ስድስት ደርሷል ፤ መንግስት ምክንያቱን አልደረሰበትም ፤ መንግስትም ሬሳ ለቀማውን ተያይዞታል ፤ ጊዜው ደርሶ የእነርሱም ሬሳ እስኪለቀም ድረስ ፤ ይህ ነገር በሚዲያ እንዳይወጣ ዝምታን የመረጠ ይመስላል ፤ ወሬው ቢሰማ ለስራው ጥሩ ስላልሆነ ሲሞቱ ብቻ ሬሳ ማንሳትን መርጧል ፤ እስከ አሁን ድረስ  ስድስት ሰዎች ሞተው ተገኝተዋል ፤ ነገ ደግሞ ስራቸውን ከቀጠሉ የባሰ እንደማይመጣ እርግጠኞች አይደለንም ፡፡ እነዚህ ሰዎች በምን ሞቱ ይባላል ?
‹‹ እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ›› ትንቢተ ሚልክያስ 4፤5 ከእኩይ ተግባራችሁ ተመለሱ ፡፡ ‹‹ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል›› የሐዋርያት ሥራ 26፤ 14 ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሳውልን በጊዜው እንዲህ ነበር ያለው ፤ አሁንም የመውጊያውን ጫፍ እየነኩ መከራውን እየተቀበሉ ፤ በእነርሱ እየባሰ ይገኛል ፤ ዋልድባን ነክቶ የሰላም አየር መተንፈስ የለም ፤ ለናንተ የምጥ መጀመሪያም  ሊሆን ይችላል ፡፡

መንግስት በህገመንግስቱ ዘወትር ‹‹መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም›› ይላል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው የዋልድባ ገዳም አባቶች ምህላ እንኳን በህብረት ሆነው ወደ አምላካቸው እንዳያደርሱ ተከልክለዋል ፤ ምህላ ጸሎት ነው ፤ ጸሎት ማድረግ በመንግስት ከተከለከልን እንዴት መንግስት ጣልቃ አልገባም ማለት እንችላለን ? ፤ የምህላውን ውጤቱን ከኛ ይልቅ እነርሱ የተገነዘቡት ይመስለኛል ፤ የዛሬ 20 ዓመት ገዳሙን የጦር ካምፕ ለማድረግ ሲያስቡ ፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲፈፅሙ የደረሰባቸው አደጋ ትምህርት ሊሆናቸው አልቻለም ፤

እግዚአብሔር በርካታ ጊዜ በሙሴ አማካኝነት ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎ በቀጥታ ነግሮታል ፤ ፈርኦንም ልቡን ክፉኛ አደንድኖ ነበር ፤ በስተመጨረሻም እግዚአብሔር በተዓምር ህዝቡን አስለቅቋል ፤ አሁንም ይህን የስኳር ልማት እንዳትሰሩ ፤ ህገ ወጥ ስራችሁ የገዳሙን ህልውና እንዳይፈታተነው በርካታ ጊዜ በአባቶች እና በምዕመኑ ተመክራችኋል ተዘክራችኋል ፤ ልቦናችሁ ደንቁሮ ዝም ብላችኋል ፤ አሁን አንድ በአንድ እያለ ይለቅማችኋል ፤ እናንተን ሲለቅም እኛን ቁጭ ብለን አንቆጥራለን ፤ የእግዚአብሔርንም ስራ በእምነት እናደንቃለን ፤ ሲጀመር የመጀመሪያው ሰው ሞት ገርሞን ነበር ፤ አሁን ግን ስድስት ሰው መድረሱን ማወቅ ችለናል ፤ እናንተ ልባችሁን ለማደንደን ባሰባችሁ ቁጥር መቅሰፍቱ ከአንድ ሰው ወደ ስድስት ሰው እያደገ ይሄዳል ፤ አምላካችን ዋድባን በተአምር ያስለቅቃችኋ ፤ የአቡነ ተክለኃይማኖት ፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፤ የአቡነ እስትንፋሰክርስቶስ ፤ የቅድስት አርሴማ አምላክ እኛን አይተወንም ፤ እንደ እኛ ሐጥያት ሳይሆን እንደ አባቶቻችን ጸሎት ብሎ ገዳሙን ከአደጋ እንደሚጠብቀው ጽኑ እምነታችን ነው፡፡

የሐዋርያት ሥራ 1፤14 ላይ ‹‹በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።›› ይላል ፤  እስኪ እኛም በአንድ ልብ ሆነን ስለ ዋልድባ ገዳም በርትተን እየጸለይን  እንትጋ ….የእግዚአብሔርንም እጅ እንጠብቅ ፡፡
የሚቀጥለውን ተዓምር ይጠብቁን

6 comments:

 1. where can I find dc's public meeting on Waldeba???? I want to listen to the papers presented and the raised oppinions

  ReplyDelete
  Replies
  1. የደብዳቤውን ሙሉ ቃል እዚህ ጋር ያገኙታል
   http://savewaldba.blogspot.com/p/blog-page_7228.html ወይም ደግሞ
   https://docs.google.com/file/d/0B08ihe6dWn9HTEJVdjBGQjVheE0/edit
   ከሁለቱ ሊንኮች በአንደኛው ቢጠቀሙ የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ሊያገኙ ይችላሉ።
   ቸር ይግጠመን አሜን

   Delete
 2. how can an orthodox christian works in this evil act...the engineer, the drivers and also the day laborers...please what happens...also the christian followers negligency for the churchs teaching should be discussed and dealt later on
  may GOD give us bright future

  ReplyDelete
 3. በምን ቋንቋ ልናገር እባካችሁ በተለይ ማህበረ ቅዱሳን ስሙኝ ቃሉ አንድ ነው:: በየአላችሁበት ፀጥ ብላችሁ በጥብቅ ለጾሎት ትጉ ውጤቱን በሰው ሳይሆን በጌታ የቀን ፍቃድ ያልቃል እሩቅም አይደለም::
  ሁሉን ማድረግ የማይሳነው አምላክ ከኛጋር ይሁን:: አሜን!

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤