Monday, April 30, 2012

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መጓዛቸውን ኢሳት ዘገበ፣


  • "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ብሏል የኢሳት ዜና፤
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 ዓ.ም፤ April 30/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦፦ “በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መትመማቸውን እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን” ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ዘገባው አስታወቀ። “የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ያለው ዜና ተቋሙ የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም” ሲል አክሏል።

ዘገባው ቀጥሎም “ከ5ሺ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም ርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግትና ዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት” መግለጡን አብራርቷል።

“ሰራተኞቹ እኛ ለዝብ ልማት ይውላል ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?” በማለት አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ራው ሙሉ በሙሉ ቆሟል።” ያለው ኢሳት “መንግራው ተቋርጧል በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ራው መቋረጡን ከልብ አምነን ለመቀበል አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል” ብሏል።

የአካባቢው ዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሏል” ሲል ኢሳት አብራርቷል። የገዳሙ አባቶች ይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።” በማለት ሰሞኑን ዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። ያለው ኢሳት “መንግት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል” ብሏል። “አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። የዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነው ያሉት እኝህ ሰው፣ መንግት ከዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ” ማስጠንቀቃቸውን ጠቅሶ “የመንግት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም” ብሏል።
ስኳር ገዳም ገባ
እያንገራገሩ ሕዝብ እያባባ፣
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ፣
እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ፣
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ፣
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ፣
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ።
ሲጠፋ ሰሰወር ሲወድቅ ቆይቶ፣
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ፣
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ፣
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ፣
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ፣
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ፣
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ።
አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ፣
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ፣
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ፣
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ፣
በውሳኔው ጸንቶ
ኽረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም፣
ከአቅም በላይ ሆኖ ሕዝብ ቢበደልም፣
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድ የለም።
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ፣
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ፣
ጸሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ፣
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ።
በአዜብ ሮባ 
April 3, 2012

No comments:

Post a Comment

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤