Wednesday, April 18, 2012

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ ይበልጡኑ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ ይበልጡኑ አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል
 • በተለያዩ የአሜሪካን ስቴቶች ውይይቶች፣ ስብሰባዎች፣ ሰላማዊ ሰልፍ ታቅዷል
 • በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን እንዲሁም አባቶች በአጠቃላይ ወደ አንድ አቋም  እየመጡ ነው (መንግስት በአስቸኳይ በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚያደርሰውን እንግልት፣ ማሳደድ፣ ማፍረስ፣ እንዲያቆም ተጠይቋል)
 • በኒውዮርክ፣ በሳን ሆዜ፣ በቶሮንቶ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሰላማዊ ትዕይንት እንዲሁም ውይይቶች እንደሚደረጉ ተነግሮናል፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳመ ዋልድባ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በተለየ መልኩ የሀገርን ሃብትና የወገንን
 ቅርስ ለማጥፋት ከጥፋት ሃይሎች ጋር በመሰለፍ በተለይ ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ እና ትውፊት ያለውን የዋልድባ ገዳም አካባቢ የስኳር ፋብሪካ እገነባለሁ፣ የፖርክ ክልል እከልላለሁ በማለት አያሌ ሰቆቃዎችን እያደረሰ ይገኛል። በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በገዳሙ በጸሎት ተወስነው ያሉትን አረጋዊያን ገዳማዊያን በማንገላታት፣ ከጸሎታቸው በማስተጓጎል፣ በውጪ ሚዲያ የተናገሩትን አውጡ በማለት በገዳሙ ቅጽር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ክብራቸውን በሚነካ መልኩ ወታደሮች ወደ መቅደሱ በጫማቸው በመግባት፣ መናኒያኑን ማንገላታቱን ቀጥለውበታል። ወደ አካባቢው ለጸሎት እንዲሁም ከአካባቢው በረከት ለመቀበል ወደ ቦታው ሄደው የነበሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ብዙ እንግልት እና ማስፈራራት ደርሶባቸው እንደተመለሱ በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ወጥቶ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

ይህ በሀገራችን መንግስት እያደረሰ ያለውን የሃይማኖት ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች፣ ሀገር ወዳድ የቅርስ እና ትውፊት ተቆርቋሪዎች በአሁን ሰዓት ልክ ቀፎው እንደተነካ ንብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከትልቅ እስከ ትንሽ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት፣ ለዚህም አይነተኛ ምስክሮች በመጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት እና በኒውዮርክ የኢትዮጵያው ዩናትትድ ኔሽን አምባሳደር ቤት ፊት ለፊት የተደረጉት ሰላማዊ ትዕይንቶችን ተከተትሎ በኮንፈረንስ እንዲሁም በውይይት መድረኮች ላይ እየተዘጋጀ የሰዎች መነጋገሪያ የሆነውን የሰሞንኛ የገዳመ ዋልድባ ጉዳይ እንደሆነ ማንም መገመት እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል። እነዚህ ሕዝባዊ ቁጣዎች እና የሕዝብ አቤቱታዎች መንግስት እንደመንግስትነቱ ተመልክቶ መልስ ሊሰጥበት እንዲሁም እያደረገ ካለው የጥፋት ዘመቻ ጊዜ ሳይሰጥ ማቆም እንዳለበት ሊያስገነዝብ የሚችል ይመስለናል።

እነዚህ ሕዝባዊ ትዕይንቶች በመቀጠል በተለያዩ ከተሞች እየተዘጋጁ እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል ከነዚህም በጥቂቱ በቅርቡ በApril 29, 2012 ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ ላይ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እንደሚደረግ የደረሰን  ሪፖርት ጨምሮ ገልጿል።
አድራሻውም እንደሚከተለው ነው ከ2:00 - 5:00 PM. የስብሰባ ጥሪ
2500 MASONIC DRIVE
SAN JOSE, CA 95125
ለተጨማሪ መረጃ
408-421-5163, 408-582-4599, 408-218-6904 OR 408-417-2329
በኒው ዮርክ ሲቲ በመጪው ማክሰኞ ጠዋት ከ10:30 AM. ጀምሮ ሰላማዊ ትዕይንት
The Waldorf Astoria
301 Park Avenue
New York City, NY
ለተጨማሪ መረጃ 718-321-3619

በቶሮንቶ ካናዳ በቅርብ ቀን እንደሚደረግ ነግረውናል ሙሉ መረጃው እንደደረሰን እናቀርበዋለን

ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን፣ ለሃገራችን እድገትን፣ ለሕዝባችን መልካም አስተዳደርን እንመኛለን
ቸር ያሰማን

Let's SAVE WALDBA, together.

2 comments:

 1. ዋሊ
  ገዳመ ዋሊ(ዋልድባ) በሚል ርዕስ
   ከገዳሙ አመሠራረት እስከ አሁን ያለውን ሁኔታ
   የገዳመ ዋልድባ ልዩ ልዩ ባሕርያትን (ገዳመ ዋልድባን ከሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት ልዩ የሚያደርገውን)
   በቅርቡ የተከሰተውን የስኳር ፋብሪካና ገዳማውያኑ አሁን ያሉበት እውነተኛ ሁኔታ እንዲሁም የመንግሥት አቋም
   ከመንግሥት/ከማየ ጸብሪ ወረዳ አስተዳደር፣ ከአማራ ክልል ብአዴን፣ ከስካር ፋብሪካው የበላይ ኃላፊ አቦይ ጸሐዬ፣ ከጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ(በቅርቡም ሚያዝያ 9 አካባቢ ለተዋካዮች ምክር ቤት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን)/፣ ከቤተክህነት/ ከሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፣ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በሊቀካህናቱ መሪነት የተሰጠውን መግለጫ፣ እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን የተላኩት አጣሪ ኮሚቴዎች ያጣሩትንና የዘገቡትን ምን እንደሚመስል፤ (ማኅበረ ቅዱሳን የማጣራቱን ሥራ ሰርቷል ወደፊት ዘገባ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቀውን)
   ገዳሙ ለመንግስትና ለተለያዩ የቤተክህነት ቅርንጫፎች የጻፈውን ደብዳቤ
   በገዳመ ዋልድባ ውስጥ ስለሚገኙት የማኅበር ገዳማት(አብረንታንት፣ ዳልሽህ፣ ሰቋር)
   በአብረንታንት ገዳም ውስጥ ስለሚገኙት ቤተ ሚናስና ቤተ ጣዕማ፤ ትምህርታቸው፣ልዩነታቸው፣…. ሌሎቹንም ምን እንደሚመስል
  ……..በቅርቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዤላችሁ እቀርባለሁ፡፡ ዋሊ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድማችን ዋሊ ስለምታደርገው ትብብር በሙሉ በዝግጅት ክፍላችን ስም ስናመሰግን ለልብ በመነጨ ነው። ሥራህን እግዚአብሔር ይባርክ፣ ቤተክርስቲያንን ከፈተና ይጠብቅልን።
   በወቅቱ የተነሱባትንም ያስታግስልን አሜን
   ሴቭ ዋልድባ

   Delete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤