Thursday, May 17, 2012

የጸሎት እና የምስጋና ጥሪ በመላው ኢትዮጵያ ለምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ!እንደሚታወቀው በመጪው ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፥ ሰልፉም የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል በሚገኘው ታላቁ የዋልድባ ገዳም አካባቢ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ፣ የፓርክ ይዞታ፣ እንዲሁም የመንገድ ጥርጊያ እሰራለሁ በሚል ሰበብ የዋልድባ ገዳም ይዞታን የተለያዩ ከባድና ቀላል የእርሻ መሳሪያዎችን በመጠቀም አጽመ ቅዱሳንን በማፍለስ፣ ቦታውንም በዶዘር በማረስ መጠነ ሰፊ የሆነ የጥፋት ዘማቻ ከጀመረ ውሎ አድሯል፤ ቦታው የመድኃኒዓለም ስም የሚወደስበት የሚሰለስበት ቅዱስ ቦታ ነው ያሉ ገዳማውያኑም አቤቱታቸውን ከማይፀብሪ አውራጃ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ብሎም በመንበረ ፖትሪያሪኩ ጽ/ቤት ድረስ አቅርበው ነበር ነገር ግን ሰሚ ሊያገኙ አልቻሉም። ለዚህም ነው ድምጻቸው ድምጻችን ነው፣ አቤቱታቸው አቤቱታችን ነው፣ መገፋታቸው መገፋታችን ነው ያልን በተለያዩ ዓለማት የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆንን በሃገር ውስጥ የገዳማውያኑን አቤቱታ ሊሰማ የፈቀደ ከመንግሥትም ከቤተክህነቱም ስለሌለ እኛ ልጆቻቸው አቤቱታቸውን ለዓለም ሕብረተሰብ ማሰማት ይኖርብናል በሚል ቅን ሀሳብ በመጪው ግንቦት ፳፯ የመድኅኒዓለም እለት በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅ የምንወጣው፥ 
በኢትዮጵያ ሀገራችን የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ከገዳማውያኑ ጋር የዓላማ አንድነታችንን ለማሳየት፣ ይልቁንም እንደሻማ ቀልጠው ብርሃን ለሆኑት ለክርስቶስ ፍቅር ብለው በረሃ ለበረሃ ለተቅበዘበዙት አባቶቻችን መነኩሳት በዚሁ እለት የመድኅኒዓለም እለት የመድኀኒዓለም ታቦት ባለበት ቦታ ሁሉ አባቶች፣ እናቶች፣ እህቶች፣ ወንድሞች በአንድነት በፍቅር ሆነን እነዚህን ሦስት መዝሙራት እየዘመርን የአላማ አንድነታችንን እንድናሳውቅ መልክታችንን በመላው የኢትዮጵያ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ያስተላልፉን።
በአዲስ አበባ (ቦሌ መድኅኒዓለም)፣ በመቌሌ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደሴ፣ በሸዋ፣ በደብረዘይት፣ በናዝሬት፣ በነቀምት፣ በአርዚ፣ በሐዋሳ፣ በዲላ፣ በይርጋለም፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ፣ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በይርጋለም፣ በሻሸመኔ፣ በአባ ምንጭ፣ እና በደብረብርሃን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከተሞች በሙሉ በሚገኙ የመድኀኒዓለም ደብር በሙሉ በግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. 


፩ኛ/ "ማርያም ሐዘነ ልቦና ታቀላለች"
፪ኛ/ "መድኀኒዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ"
፫ኛ/ "ኀይል የእግዚአብሔር ነው"


ማሳሰቢያ: ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ፍፁም ሰላማዊ ናትና መርኃ ግብሩሰላማይሆን ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ገዳማቶቿን በቸርነቱ ይጠብቅልን !!!

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ጊዚያዊ 

ኮሚቴ
ሰሜን አሜሪካ

4 comments:

 1. may the help of almighty God with his blessed mother be with us!
  "tigeu wetseleyu kemeitbau west mensute"

  ReplyDelete
 2. I am just wondering how this pssive action is going to help our current problem. To my understanding the center of the problem is Paulos. How can Scattered protest all over the place remove this person?

  It is confusing.

  On one hand, if we are saying we are peaceful and honestly believe in prayer to fight against SEYTAN there is no need to put a program out there to do it. Everyone of us should fill the pasin and cry out to God whenever and whereever.

  On the other hand, if we are saying let us show how big our united action is to our worldly enemies whoever they are let us show it out there in the open air specialy in Ethiopia like our muslim brothers.

  I just don't get it.

  ReplyDelete
 3. Well! the Anonymous above, I hope you got it by now! and your question should be answered. The scattered protest and the three songs were enough to be heard by God!

  ReplyDelete
 4. የዋልድባ ነገር የሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ሁሉ አይን ነው እባካችሁን ያለውን ነገር ሁሉ ተከታትላችሁ አሳውቁን መቼም ካልጠፋ መሬት እንዴት ዋልድባ ለመንግስት ታየው ዓላማው ቤተክርስቲያንና ገዳማቱን ፣ ልጆቿን ለማጥፋት የታለመ መሆኑ በግልጽ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ዛሬ ወጣቱ ለሀይማኖቱ ያለውን ጥንካሬ ያሳየበት ወቅት ነው እግዚአብሔር ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን እናንተንም ያበርታችሁ እባካችሁን የኢትዮጵያ ሚዲያ እውሸት እንጂ እውነት ተናግሮ አያውቅም እውነት ለመናገርም አልተፈበረከም በሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ የቤተክርስቲያኒቱንና የገዳማቱን ችግር የአባቶች ችግርና መከራ ምእመኑ ምን እየተደረገ መሆኑን በግልጽ እንዲያውቅ ብትጥሩልን ያለውን ነገር ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ ሊያግዝ ይችላል፡፡
  እግዚአብሔም አምላክ ያስበን
  የበላይሰብ እመቤት ወላዲተአምላክ እሷ ትታደገን

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤