Thursday, June 28, 2012

የቅዳሜው በዓዲርቃይ የተካሄደው ስብሰባ ዘገባ

የዋልድባ ገዳም ህልውና ይከበር! 

 • "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም" ከመነኩሳት ወገን ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
 • "ልማቱን በግድም በውድም መቀበል ይኖርባችኋል" የመንግሥት ተወካይ
 • "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግም" የአካባቢው ነዋሪ
 • በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡

Friday, June 15, 2012

ዋልድባን ከቅርብ ርቀት"እኔን የወደደ መስቀሌን ይዞ ይከተለኝ" 
መንግ በልማት ስም ቅዱስና ታሪካዊ የሆነውን የዋልድባን ገዳም ተጠግቶ የስኳር ፋብሪካ እገነባለሁ ካለ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ ከአገር አልፎ በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በስፋት ሲያነጋግር ሰንብቷል። ዋልድባ ለክፍለ ዘመናት ታፍሮና ተከብሮ "በጥብቅ" ሀይማኖታዊ ስርዓት የቆየ፣ ፍጹም ልዩ የሆነ መንፈሳዊና ታሪካዊ ዋጋ ያለው ስፍራ እንደመሆኑ በስፋት እየቀረበ ያለው ተቃውሞም በከፍተኛ ስሜት እና ቁጣ የታጀበ ሊሆን ችሏል።

                እኔም ችግሩ የአንድ ወቅት ትኩሳት ሆኖ የማይቆም፤ ይልቅስ የማንነት፣ የታሪክና የዕምነት ፅናት ጥያቄ መሆኑን በማመኔ ነበር በስፍራው ተገኝቼ ሁኔታውን መመርመር እንዳለብኝ የወሰንኩት። ያዩ፣ የሰሙትንና የታዘቡትን ለህዝብ ማካፈሉ ደግሞ የሙያ ብቻ ሳይሆን የዜግነትም ግዴታ ይመስለኛል።

                ዋልድባ ደርሼ የሆነውን ሁሉ ለመመርመር ያደረኩት ጥረት ግን በመስዋዕትነት የተከበበ፣ ብዙ ዋጋም ሊያስከፍለኝ ይችል እንነበ መሸሸግ አልችልም። ከአ.. ጎንደር፣ ከጎንደር ዋልድባ ለመድረስ ያለው የጉዞ ርዝማኔ እንዳለ ሆኖ ከገዳሙ ለመድረስ 30 በላይ ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩን ጀምሮ ያለው ጥብቅ ጥያቄና ምዝገባ ሁሉ እጅግ አስደንጋጭና ያልተለመደ ነው።

VOA June 14, 2012
ዛሬ ዛሬማ ላይ ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ በዛሬማ ነዋሪ ወጣቶች ከባድ ተቃውሞ ምክንያት ወደ ዓዲርቃይ የተዛወረው ስብሰባ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የመንግስት ተወካዮች፣ የገዳሙ ተወካዮች፣ እንዲሁም ጥቂት ገዳማውያን እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት መንግሥት ልማቱን አትቃወሙ በማለት ለማስፈራራት የሞከረበት ስብስበባ እንደነበር ከእማኞች ለመረዳት ችለናል። አባቶችም ይልቁንም የሰቋር ኪዳነ ምሕረት እናቶች በወኒያቸው ኮርተናል "አባቶቻችን በደማቸው ያቆዩልንን ርስት፣ ቆመን እያየን ሊወሰድ አይችልም" "መጀመሪያ እኛን ገላችሁ" በማለት ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።
የሃገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ "ልማትን አትቃወሙ" ማለታቸው በመነኩሳቱ ዘንድ ከባድ ቁጣን አስነስቶባቸዋል

Monday, June 11, 2012

ሰሞኑን በዋልድባ እስራቱ እና እንግልቱ ቀጥሏል


በዋልድባ ገዳም ዙሪያ እስሩ፣ እንግልቱ፣ እንዲሁም ማስፈራራቱ እንደቀጠለ ነው. . . የገዳማውያኑን የምዕመኑን ጩኽት
የሚሰማ ጠፋ. . . ቤተክርስቲያንም አባት አጥታለች፣ ኢትዮጵያም የሕዝቡን ጩኽት የሚሰማ መሪ አጥታለች ታዲያ ምን ይሻላል?

savewaldba@gmail.com

Wednesday, June 6, 2012

ዋልድናን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ደብዳቤዎችን ላከ


ባለፈው ሰኞ ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፬ ዓም ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ደብዳቤዎችን ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተሟቻቾች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለአሜሪካን የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ለተለያዩ ሴናተሮች፣ ኮንግረስ ተወካዮች በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ሎስ አንጀለስ፣ ለኢትዮጵያ ዮናይትድ ኔሽንስ አምባሳደር ደብዳቤዎችን አስገብቷል። ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑት ድርጅቶች መልሶችን በቅርቡ ይጠበቃሉ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥትም መልሶችን እንደሚጠበቁ ተነግሮናል እንደደረሰን እንዘግባለን

ለተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተላከውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተላከውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Tuesday, June 5, 2012

ታሪክ ራሱን ይደግማል


ያልተጻፈ የማይጻፍ ያልታየ ያልተዘገበ
          ምን አለና ነው ያልተነበበ
                   ገና ድሮ ጥንት በዘፍጥረት  በህገ ልቦናው
                   አዳም ከገነት የወጣ የተባረረው
                   የሞት ሞትን ሞቶ ከመቃብር የወረደው
                   ሄዋን ከክብር ወደ ጥልቅ የወረደችው
                   የአምላክን ትእዛዝ መርሳት መዘንጋቱዋ ነው
                   ያልተገባውን ስራ መፈጸሙዋ ነው
ታሪክ እራሱን እየደገመ ታሪክ ሆኖ ቢያልፍም
ያማይልፍ መስሎ በጊዜው ህዝብን ቢያስጨንቅም
ማለፍ ግን አይቀርም ይሄዳል
ጠባሳውን ጥሎ ባአዲስ ዘመን ይተካል
ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል

ዓለም አቀፍ የሰላማዊ ሰልፍ በትላንትናው ዕለት ተካሂዶ ውሏል


 • ዋልድባ የጸሎት ቦታ እንጂ የኢንቨስተሮች አይሆንም!
 • መንግሥት እጆቹን ከቤተክርስቲያን ላይ በአስቸኳይ ያንሳ!
 • የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!
 • መንግሥት የቤተክርስቲያኗን መብት መጋፋት በአስቸኳይ ያቁም! 

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ስለ ዋልድባ ብዙ ነገሮችን ከአንባቢያን ጆሮ ማድረሳችን ይታወሳል፥ አሁንም በዋልድባ ዙሪያ በመንግሥት ሃይሎች ዋልድባ ገዳምን እና አካባቢውን በማናለብኝነት እያረሰ እና አጽመ ቅዱሳኑን በማፍለስ የስኳር ፋብሪካውን ግንባታ እናደርጋለን በማለት ሥራውን በከፍተኛ ፍጥነት እያካሄዱ እንደሆነ ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፥ ዋልድና ገዳም ውስጥ ያሉትም አባቶችን መንግሥት በተለያየ ዘዴ ተጠቅሞ ከአካባቢው ለማስወገድ ጥረት ማድረጉን ቀጥሏል። እናንተ ለተቃዋሚዎች የምትሰሩ ጸረ ልማት እና ጸረ ሰላሞች ናችሁ፣ ስኳር ስለተወደደ ስኳር ቢለማ ምናችሁ ይነካል በማለት ማዋከቡን ቀጥሏል፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ጊዜያዊ ኮሚቴ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጠራው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጥሩ ምላሽ ማግኘቱን ከተለያዩ ከተሞች በቦታው የተከታተሉት ዘግበውልናል፣ ትላንት ጠዋት ከጠዋቱ 8:00 am. ጀምሮ በሁናይትድ ስቴትስ ሕህ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ለፊት የተሰባሰቡት የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች ከተለያየ የአሜሪካን ግዛቶች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ተደርጓል፣ ከነዚህም ግዛቶች መካከል ዋነኛዎቹ ቦስተን፣ ሻርለት ኖርዝ ካሮላይና፣ ቺካጎ፣ ሜኖሶታ፣ አትላንታ፣ ፊላደልፊያ፣ እንዲሁም የኒው ዮርክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ተገኝተው መንግሥት እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ የታሪክ እና የሃይማኖት ማጥፋት ዘመቻ በጥብቅ ተቃውመዋል።
  በዚህ ገዳም ላይ ደረሱ ከተባሉት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ለስኳር ፋብሪካ ፕሮዤክትና ለሸንኮራ-አገዳ ልማት ቦታው እየታረሰ ነው፤ የአበው መካነኩሳት አረፈ አጽማቸው እየተቆፈረ እና እየፈለሰ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰደ ይገኛል፣ አያሌ አብያተ-ክርስቲያናት ሊፈርሱ በዕቅድ ተይዘዋል፣ የገዳሙ ንብረት የሆነ በርካታ ገንዘብ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተዘረፈ፣ ብዙ ኲንታል የእጣን ምርት ባልታወቁ ሰዎች ተቃጠለ፤ እናም ይህን አባቶች «በደል» ያሉትን በዝርዝር ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚገልጹ መነኮሳት አደን፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው የሚሉ ይገኙባቸዋል።
VOA interview June 4, 2012

Washington DC June 4, 2012

New York City June 4, 2012

Los Angeles, CA June 4, 2012


የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል

Sunday, June 3, 2012

የESAT ቃለ ምልልስ

ዋልድን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ከላስ ቬጋስ እና ካናዳ ተወካዮች ጋር ያደረገው የሬዲዮ ቃለ ምልልስ ተከታተሉት። 

የVOA ሁለት ቀን ቃለ ምልልስ ከዋልድባ

የVOA June 1, 2012 ቃለ ምልልስ 
በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው መንግሥት፣ ማናለብኝ በማለት ሥራውን እየሰራ እንደሆነ ይነገራል። የቤተክርስቲያኗ የበላይ አካላትም እስከ አሁን ምንም ድምጽ ሊያሰሙ ፈቃደኞች አይደሉም እስከመቼ ይሆን?
ቸር ወሬ ያሰማን።

የVOA June 2, 2012 ቃለ ምልልስ 
በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው መንግሥት፣ ማናለብኝ በማለት ሥራውን እየሰራ እንደሆነ ይነገራል። የቤተክርስቲያኗ የበላይ አካላትም እስከ አሁን ምንም ድምጽ ሊያሰሙ ፈቃደኞች አይደሉም እስከመቼ ይሆን?
ቸር ወሬ ያሰማን።

Friday, June 1, 2012

የVOA May 31, 2012 interview


ልብ ያለው ልብ ይበል

ማስታወቂያ June 4, 2012

በመጪው ሰኞ ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (June 4, 2012) የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሰሜን አሜሪካ

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰኞ ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. 

በዋሽንግተን ዲሲ
Capitol Hill እስከ State Department (22 & C Street NW.) Washington DC የእግር ጉዞ ይደረጋል።
አስተባባሪዎቹን በሚከተለው ስልክ ማግኘት ይቻላል
703-956-0513 ወይም 571-224-2869 


በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል •   
  ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
 • “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
 •    ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃትሏል
  (አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ  በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡