Tuesday, June 5, 2012

ዓለም አቀፍ የሰላማዊ ሰልፍ በትላንትናው ዕለት ተካሂዶ ውሏል


  • ዋልድባ የጸሎት ቦታ እንጂ የኢንቨስተሮች አይሆንም!
  • መንግሥት እጆቹን ከቤተክርስቲያን ላይ በአስቸኳይ ያንሳ!
  • የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!
  • መንግሥት የቤተክርስቲያኗን መብት መጋፋት በአስቸኳይ ያቁም! 

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ስለ ዋልድባ ብዙ ነገሮችን ከአንባቢያን ጆሮ ማድረሳችን ይታወሳል፥ አሁንም በዋልድባ ዙሪያ በመንግሥት ሃይሎች ዋልድባ ገዳምን እና አካባቢውን በማናለብኝነት እያረሰ እና አጽመ ቅዱሳኑን በማፍለስ የስኳር ፋብሪካውን ግንባታ እናደርጋለን በማለት ሥራውን በከፍተኛ ፍጥነት እያካሄዱ እንደሆነ ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፥ ዋልድና ገዳም ውስጥ ያሉትም አባቶችን መንግሥት በተለያየ ዘዴ ተጠቅሞ ከአካባቢው ለማስወገድ ጥረት ማድረጉን ቀጥሏል። እናንተ ለተቃዋሚዎች የምትሰሩ ጸረ ልማት እና ጸረ ሰላሞች ናችሁ፣ ስኳር ስለተወደደ ስኳር ቢለማ ምናችሁ ይነካል በማለት ማዋከቡን ቀጥሏል፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ጊዜያዊ ኮሚቴ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጠራው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጥሩ ምላሽ ማግኘቱን ከተለያዩ ከተሞች በቦታው የተከታተሉት ዘግበውልናል፣ ትላንት ጠዋት ከጠዋቱ 8:00 am. ጀምሮ በሁናይትድ ስቴትስ ሕህ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ለፊት የተሰባሰቡት የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች ከተለያየ የአሜሪካን ግዛቶች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ተደርጓል፣ ከነዚህም ግዛቶች መካከል ዋነኛዎቹ ቦስተን፣ ሻርለት ኖርዝ ካሮላይና፣ ቺካጎ፣ ሜኖሶታ፣ አትላንታ፣ ፊላደልፊያ፣ እንዲሁም የኒው ዮርክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ተገኝተው መንግሥት እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ የታሪክ እና የሃይማኖት ማጥፋት ዘመቻ በጥብቅ ተቃውመዋል።
  በዚህ ገዳም ላይ ደረሱ ከተባሉት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ለስኳር ፋብሪካ ፕሮዤክትና ለሸንኮራ-አገዳ ልማት ቦታው እየታረሰ ነው፤ የአበው መካነኩሳት አረፈ አጽማቸው እየተቆፈረ እና እየፈለሰ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰደ ይገኛል፣ አያሌ አብያተ-ክርስቲያናት ሊፈርሱ በዕቅድ ተይዘዋል፣ የገዳሙ ንብረት የሆነ በርካታ ገንዘብ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተዘረፈ፣ ብዙ ኲንታል የእጣን ምርት ባልታወቁ ሰዎች ተቃጠለ፤ እናም ይህን አባቶች «በደል» ያሉትን በዝርዝር ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚገልጹ መነኮሳት አደን፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው የሚሉ ይገኙባቸዋል።
VOA interview June 4, 2012

Washington DC June 4, 2012

New York City June 4, 2012

Los Angeles, CA June 4, 2012
የተባለው ልማት በእርግጥም በዕቅድ ላይ መሆኑን መንግትም ሆነ ጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ ያምናሉ። መንግሥት፣ «ልማቱ ከገዳሙ ብዙ እርቅት ላይ ስለሆነ አይነካውም» ሲል፣ ወደ ስፍራው የተላኩት የጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ የዐይን ምስክሮችም ይህንኑ አረጋግጠው፣ «ቤተ-ክህነት የመንግስቱን የልማት ዕቅድ ትደግፋለች" ብለዋል።

Toronto Canada June 4, 2012 by www.esat.com 
የገዳሙ ይዞታ እንዳይነካ ጥያቄ የሚያቀርበው ሕዝብ በአካባቢው ብቻ አልተወሰነም። «ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመ ዓለማቀፍ ኰሚቴ» የተሰኘው ስብስብ የየአካባቢው ተጠሪዎች ለቪኦኤ እንደገለጹት፣ ዛሬ አንድ ዓለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄደ ላይ ነው። ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ቶሮንቶ-ካናዳ፣ ሎስ-አንጀለስ-ላኪፎርኒያ፣ ኒው-ዮርክና ዋሽንግተን ዲሲ። አውሮፓ ደግሞ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ብራስልስና አውስትሬሊያ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

በትላንትናው ዕለት በዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛው ምክር ቤት Capitol Hill ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት የተጀመረው መረኅግብር በጸሎት በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ መሪነት ከተከፈተ ጀምሮ በኃላም በፔንሲልባኒያ ጎዳና ላይ በእግር ተጉዞ በአሜሪካው የstate department ላይ በብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳን እና ጸሎት ተጠናቋል። በዚህም ትዕይንት ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከቦስተን፣ ከኒው ዮርክ፣ ፊላደልፊያ፣ ቺካጎ፣ ሜኖሶታ፣ አትላንታ ከሰሜን ካሮላይና ሻርለት፣ እንዲሁም ከቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ የዲሲ ነዋሪዎችን ጨምሮ የተገኙበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር ተመልክተናል። ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር።
በዚህ ሰልፍ ላይ የክርስትና እምነት ተከታይ ብቻ አይደለም የተገኙት። ሌሎችም በኢትዮጵያውነታቸው ተገኝተዋል።
ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተወከሉት ባለሥጣን Ms Lora, ሙሉ ስማቸውን ማግኘት አልተቻለም፤ የሰልፈኛውን ደብዳቤ ተቀብለው ጉዳዩን እንደሚያጤኑትና ተገቢ ነው የሚሉትን ምላሽ በጽሑፍ እንደሚሰጡ ለሕዝቡ ገልጸዋል።
በተለይም ባለፈው ሐሙስ ሰቋር ውስጥ፣ በማግስቱ ዐርብ ደግሞ ገሪማ ላይ ስብሰባ ተካሂዷል። የሐሙሱ፣ እራሱ ሕዝቡ ተጠራርቶ የተሰባሰበበት ሲሆን የዐርቡ ደግሞ ባለሥልጣናት የገዳሙን አሥር ያህል መነኮሳት ጠርተው የሰበሰቡት እንደነበር ተገልጾልናል። 
በተለያየ ከተማት የተደረገውን የቪዲዮ ዝርዝር በቅርቡ እናቀርባለን።
እግዚአብሔር አምላክ ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ቤተክርስቲያንን በቸርነቱ ይጠብቅልን አሜን

1 comment:

  1. አሜን አሜን አሜን! እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ሃገራችንን ይጠብቅልን! የተዋህዶ አርበኞች በርቱልን፣ እየተደረገብን ያለውን ግፍ ማስቆም ካልቻልን ዛሬ ዋልድባን ያረሱ ነገ ሌላውን እንዳይነጥቁን ዋስትና የለንም ሁላችን በያለንበት በመጮህ ውሳኔ አምጪዎች መሆን አለብን ለዚህም የአምላክ ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤