Tuesday, July 3, 2012

በዋልድባ አባቶች ላይ ፈተናው ጨምሯል ከጸሎት በመሣሪያ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው


በዋልድባ ሰቋር ኪዳነምሕረት የሴቶች አንድነት ገዳም አባቶች እና እናቶች በሱባኤ ባሉበት ወቅት የመንግሥት ታጣቂ ወታደሮች ወደ ገዳሙ ክልል በመግባት 5 አረጋውያን መነኩሳትን ለእስር ዳርገዋቸዋል ምክንያታቸውም ሕዝቡን የምታነሳሱት እናንተ ናችሁ ለዓመጽ እና ለጦርነት አነሳሳችሁት በሚል ሰበብ ነው። እውነታው ግን እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ለሃይማኖቱ እና ለቤተክርስቲያኑ ክብር መቆም ያለበት መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። እነዚህ አባቶች ለሀገር፣ ለወገን፣ ለመሪዎችን እንዲሁም ለአለም በጸለዩ የአባቶቻችንን ርስት አንሰጥም ባሉ እስር መዳረጋቸው ትልቅ ቁጣ አስተስቷል በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ዝም አንበል የአባቶቻችን ደም ይጠራናል የበኩላችንን እናድርግ ስለ እመብርሃን የጭንቅ አማላጇ ብላችሁ ቤተክርስቲያንን እንጠብቅ
"እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን" ራዕይ 10:3
ቸር ወሬ ያሰማን

1 comment:

  1. መናፍቃን በኢ\ኦ\ተ\ቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጠሩ ያለውን ችግር ለመረዳት http://emenetsion.blogspot.com (እምነ ጽዮን) የተባለውን ጦማር ቢያነቡ ጥሩ ግንዛቤ ያገኛሉ::

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤