Friday, August 31, 2012

በዋልድባ ገዳም እንግልቱ እንደቀጠለ ነው ESAT


በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Wednesday, August 29, 2012

የፓትርያርክ ምርጫ ታሪክና አፈጻጸም በኮፕት ቤተ ክርስቲያን”


ወልደ ማርያም
 የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማ በትምህርተ ሃይማኖትና ከሞላ ጎደል በሥርዓተ እምነት ከሚመስሉን አኀት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ የሆነችው የኮፕት ቤተ ክርስቲያን በ2000 ዘመን ታሪኳ የሚመሯትን ፓትርያርኮች እየመረጠች የሄደችበትን ቀኖና ታሪክና ሥልት ጠቅለል ባለ መልኩ ማቅረብ ነው፡፡ ከሌሎቹ አኀት አብያተ ክርስቲያናት የኮፕት ቤተ ክርስቲያንን የምርጫ ቀኖናና ሂደት ዳስሰን ለማቅረብ የፈለግንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፕትርክና ለ1600 ዘመናት የቤተ ክርስያናችንም መንበረ ፕትርክና ሆኖ የቆየ ከመሆኑ አንጻር በጽሑፉ የሚወሳው ታሪክ የሚቀርበን በመሆኑ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፕትርክናዋ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ወንጌላዊው ማርቆስ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በድምሩ 117 ፓትርያርኮችን እየመረጠች አስቀምጣለች፡፡ 
ፓትርያርኮቹም የተቀበሉትን ሰማያዊ ሓላፊነት በመያዝ ቤተ ክርስቲያኗ ክፉውንና ደጉን ዘመን አልፋ ዛሬ ካለችበት ደረጃ እንድትደርስ አድርገዋታል፡፡ አሁን ባለችበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኗ በግብጽና በመላው ዓለም ከ15 እስከ 18 ሚልዮን የሚደርሱ ምእመናን ያሏት ሲሆን እነዚህንም ምእመናን በእረኝነት የሚጠብቁ ከ150 በላይ ሊቃነ ጳጳሳት አሏት፡፡ እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፕትርክናው ማእከላዊ አስተዳደር በሚመሩ 54 ያኽል አኅጉረ ስብከት በሊቃነ ጳጳስነት ተመድበው ያገለግላሉ፡፡ ከእነዚህ አኅጉረ ስብከት 15 የሚሆኑት ከግብጽ ውጪ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ተቋቁመው በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

Monday, August 27, 2012

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል  • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
  • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።

 (ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡

የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Friday, August 24, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

“ከመቃብር ላይ ሆነን የምንናገረው ስለ ትንሣኤ እሙታን ነው” ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቢ መንበረ ፓትርያርክ
ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኩኖ አምላክ
abune paulos funeral1 ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌሎችም የተወከሉ የእምነት አባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡

የአቡነ ጳውሎስ ሽኝት በፎቶ

Tuesday, August 21, 2012

የቤተክርስቲያን ፈተናዎች


ባለፈው እሑድ ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም.  ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ የመወያያ መርኃግብር አዘጋጅቶ በነበረበት ጊዜ በመጋቢ ጥበብ በእምነት ምትኩ የተሰጠው ጥናታዊ ጽሑፍ በወቅቱ በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ውቅታዊ ፈተናዎች እና ከእያንዳንዱ ክርስቲያን ምን እንደሚጠበቅ በግልጽ ውይይት የተደረገበት ነበር። በወቅቱ በርካታ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ከህናት፣ ዲያቆናት ተገኝተው የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑበት እለት ነበር። 
በመጨረሻ በጉባኤው ላይ ከተነሱት በርካታ ችግሮች ከነ መፍትሔ ሃሳቦች ጋር ውይይት ከተደረገ በኃላ በቀጣይ OCTOBER 7, 2012 በተመሳሳይ ቦታ ለመገናኘት ቀጠሮ በመያዝ ተለያይቷል።
 በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ሃገራችን የሃዘን ዜና በቅዱስ ፖትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ከልባችን እያዘንን  እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እየተመኘን ለሃገራችን ለቤተክርስቲያናችን ደግሞ ትጉህ፣ ታማኝ፣ ቅን መሪ እግዚአብሔር እንዲሰጠን ለልባችን እንመኛለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን በረደኤት ይጠብቅልን

Thursday, August 16, 2012

(ሰበር ዜና) ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን የተዘገበ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ደጀ ሰላም ዜናውን እየተከታተለች ማቅረቧን ትቀጥላለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

Tuesday, August 14, 2012

አንዳንድ ወገኖቻችን ዋልድባ አልታረሰም በማለት ሊያስተባብሉ ይሞክራሉ፥ እስቲ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ እና ይፍረዱ


የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም የቤተክህነቱ ተወካዮች ዋልድባ እንዳልታረሰ ምንም እንዳልተነካ በተለያየ ጊዜ ሲነገር ይሰማል ነገር ግን፣ መንግሥት ወይም እነዚህ የተለየ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ ወገኖች የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ እውነቱ ግን በዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው ዋልድባ ገዳምን የመንግሥት ሃይሎች በማናለብኝነት የተቀደሰውን ምድር ሲያርሱ እና የቅዱሳንን አጽም ሲያፈልሱ ቆይተዋል። በዚህም በርካታ የተዋሕዶ ልጆች ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሃዘን እና በቁጭት አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል አሁንም ይቀጥላሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የገዢው መደብ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን አቁሞ ወደ ሌላ ቦታ እስካልሄደ ድረስ የተጀመረው እንቅስቃሴ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይቀጥላል። ዓላማችን እረጅም ነው መንገዱም ጎርባጣ እና እሾህ አሜኬላ የበዛበት ሊሆን እንደሚችል እንገምታለን ነገር ግን ተስፋችን እግዚአብሔር ግባችን ሰማይተ ኢየሩሳሌም መንግሥተ ሰማያት ስለሆነ ሊያቆሙን አይችሉም ይልቁንም ከአምላካቸው የተጣሉት ይወድቃሉ ይዋረዳሉ፣ ከክብር ወንበራቸው ወደ ታች መውረዳቸው የማይቀር ነው።
ቸር ይግጠመን
አሜን

እግዚአብሔር የዋልድባ ገዳም አባቶቻችንን እንዲህ ይሰማቸዋል

(አንድ አድርገን ሐምሌ 3 ፤ 2004 ዓ.ም)፡, በዋልድባ ገዳም በዘመናት በርካታ ተዓምራት ተፈጽመዋል ፤ በጽሁፍ ሰፍረው ለትውልድ የተላለፉ እንዳሉ ሆነው ያልተጻፉ ተዓምራ በርካታ ናቸው ፤ የዋልድባ ገዳምን ታሪክን መሰረት አድርጎ ከተጻፈ አንድ መጽሃፍ ላይ ያገኝነውን ተዓምር በአሁኑ ሰዓት ገዳሙ ላይ እጃቸውን ላነሱ ሰዎችና ተባባሪዎቻቸው መማሪያ ይሆን ዘንድ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
ከዓመታ በፊት በዚህ ቦታ የተፈጸመ አንድ ተዓምር አለ ፤ ይህ ገዳም በተመሰረተበት ጊዜ ጌታ እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይሁንላችሁ ብሎ ባርኮ የሰጣቸው ውሃ አለ ፤ ይህ የዮርዳኖስ ውሃ ተባርኮ እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይሁንላችሁ ተብሎ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 1959 ዓ.ም ድረስ አንድም ቀን ደርቆ አያውቅም ፤ በገዳሙ አካባቢ የሚገኝ ህዝብና እንዲሁም ራቅ ካለው አገር የሚኖረው ምዕመናን በየዓመቱ በዓለ መስቀልን ለማክበር በመጋቢት 27 ቀን ከገዳሙ እየተገኝ በዓሉን ማክበር ከብዙ ጊዜ ጀምሮ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ወደዚሁ በዓል በየዓመቱ የሚመጡት ምዕመናን በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው ፤ በዓሉን ለማክበር የመጣው ህዝብ ከዚሁ ከዮርዳኖስ ውሃ ስምረትን በተቀበሉ መነኮሳት እየተቀዳ ይታጠባል ፤ ይጠጣል ወደ ቤቱ ይዞ ይሄዳል ፤ ውሃው የፈለቀው አለት ከሆነ ቦታ ላይ ሆኖ ከአንድ ከተደላደለ ቦታ ላይ ነው ፤ አለቱን እንደ እህል አውድማ ክብ አድርጎ በመሃንዲስ እንደተሰራ ጉድጓድ አድርጎ ነው ያፈለቀው ፤ ታዲያ በበዓሉ ቀን ይህን ሁሉ ህዝብ ሲቀዳው አይጎልም ፤ በአዘቦት ቀንም ተርፎ አይፈስም ፤ ሁል ጊዜ ከከንፈሩ እንደሞላ ይታያል ፡፡

የዋልድባ ጉዳይ ዋና መነጋገሪያው ነበር


  • ዋልድናን ለመታደግ ምን እንርዳ?
  • ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የቤተክርስቲያን ህልውና ለማስከበር መተባበር ግድ ይለናል
  • የዋሽንግተን ዲሲ ካህናት ለምን አይተባበሩም
  • ጥቂት ካህናት ዋልድባ ምንም እንዳልተነካ የሃሰት መረጃዎችን ለሰው እያስተላለፉ ይገኛሉ
ትላንት ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው የዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል የጠራው ስብሰባ ላይ ዋልድና እና በዋልድባ አካባቢ በሚደረጉት ሥራዎች ዙሪያ በርካታ ውይይቶች ተደረጉ። በዚህ ጉባኤ ላይ ካህናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከደረሰን ሪፖርት ለማረጋገጥ ችለናል።