Monday, September 17, 2012

አቶ አባይ ጸሀይ በአባ ወልደ ማርያም አማካኝነት ከዋልድባ መነኮሳት ጋር ተነጋገሩ

የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት አይለየን
 • አቶ አባይ ፀሐይ በአባ ወልደ ማርያም (የጻድቃኔ ማርያም መነኮስ) አማይኝነት ከዋልድባ መነኮሳት ተገናኝተው ነበር
 • የዋልድባ መነኩሳት በቤተክርስቲያናችን ድርድር የለንም፣ ሕይወታችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን
 • እኛ ገዳሙ እንዲነካ አንፈልግም፣ ገዳሙ እንዲታረስ ልንፈቅድ አንችልም
 • መነኮሳቱ ግን እየተሰደዱብን ነው

ከትላንት በስቲያ በአባ ወልደ ማርያም (የጻድቃኔ መነኮስ) አማካኝነት አራት የዋልድባ መነኮሳት፣ አባ ወልደ ማርያም፣ እና አቶ አባይ ጸሐዬ ተሰብስበው እንደነበር ከታመኑ ምንጮቻችን ዘገባ ደርሶን ነበር።
በስብሰባውም ላይ አገናኙ አባት እኔ መነኮሳቱን አውቃለሁ የልማቱን ሥራ እንዲቀጥል መደረግ ይኖርበታል በማለት የዋልድባ መነኮሳት የቅዱስ ፖትርያርኩን ሞት ተከትሎ ለሥርዓተ ቀብሩ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ያወቁት እኝሁ አባት ከአቶ አባይ ጸሀይ ጋር መነኮሳቱን ለማገናኘት እላይ ታች በማለት ለማገናኘት ችለዋል።
በስብሰባውም ላይ ከዋልድባ የመጡት መነኮሳት በአሁን ሰዓት በርካታ መነኮሳት እየተሰደዱብን ነው፣ የአካባቢው ፖሊሶች እያስፈራሩን ነው፣ እየደበደቡን ነው፣ እኛ ገዳሙ እንዲነካብን አንፈልግም፣ ገዳሙንም ለማረስ ሳንፈቅድ ፈቀዳችሁ በማለት አሰወርታችኃል፣  በቤተክርስቲያናችን ህልውና ምንም ድርድር ልናደርግ አንችልም ሃሳባችን ይህው ነው በማለት እቅጩን ተናግረው ነበር።

አቶ አባይ ጸሐይም በበኩላችው የተሰደዱትንም መነኮሳት ወደ ገዳማችሁ ተመለሱ በሏቸው፣ ማንም ሊያሳድዳቸው አይችልም ወደ ገዳሙ ተመለሱ ብላችሁ ንገሯቸው እዛ ያሉትም የወረዳው አስተዳዳሪውም እስራቱን ማስፈራራቱን እንዲያቆም እናናግራቸዋለን፣ ነገር ግን በወጪ ሬድዮ የሚናገሩት አባቶችን በሙሉ በአደባባይ ይቅርታ የኢትዮጵያን መንግሥት ይቅርታ ይጠይቁ አለበለዚያ ግን ለእነሱ ይቅርታ እስካልጠየቁ ድረስ ወደ ገዳሙ መግባት እንደማይችሉ ነበር የተናገሩት።

በተለያየ ጊዜ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ስለዋልድባ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ሲያስረዱ የቆዩትም አባት እንደሚያስረዱት: በመጀመሪያ ይቅርታ የምንጠይቀው ማንን ነው? ማን ይቅርታ ተጠያቂ? ማን ጠያቂ ሊሆን ነው? እንዴት ነገር የተገላቢጦሽ ይሆናል ነበር ያሉት። የሆነስ ሆነና ይቅርታስ የምንጠይቀው ምን ብለን ነው፣ ገዳማችንን አትንኩብን፣ የሃይማኖት መሰረታችን የሆነውን የቅዱሳን አጽም እንደ አሸዋ የፈሰሰበትን ቦታ አትረሱ ስላልን ነው ወይ ይቅርታ የምንጠይቀው። በመቀጠልም ገዳሙ አይነካብን ማለት የመነኮሳቱ ብቻ ጥያቄ መሆን እንደሌለበት አስረግጠው ነግረውናል፥ ይህ ታሪካዊ ገዳም የሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ የጳጳሳት፣ የመምህራን፣ የመነኮሳት፣ የዘማሪያን እንዲሁም የመላው ምዕመን ጥያቄ መሆን ነበረበት፣ ይህ ገዳም የሃይማኖታችን መገለጫ፣ የማንነታችን መኩሪያና ማሳያ፣ የታሪካችን አሻራ እንዲሁም የተለያዩ ቅዱሳን ገድል ያለባቸው በርካታ መጽሐፍት እና የተለያዩ የኢትዮጵያ ሀገራችን ቅርሶች ያሉበት ገዳም በመሆኑ ማንኛውንም የሃይማኖቱ ሰው ብቻ ሳይሆን ሃገር ወዳዱን ሕብረተሰብ ይመለከታል፤ በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ እና ቅዱስ ቦታ የመጠበቅ ጠብቆም ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ ያማድረግ ሃላፊነት የሁሉም ሃላፊነት መሆን እንዳለበት ነግረውናል።

እንደ እውነቱ ከሆነ የኛው አባቶች እሾም እሸለም ባዮች ወደ መንግሥት ነገሮችን እየወሰዱ የሚያመላልሱ ሰዎች እምኑ ላይ ይሆን የነሱ ለፈጣሪ ተገዥነታቸው? እውን እነዚህ ሰዎች ናቸው የወደፊቱ የቤተክርስቲያኒቱ ተረካቢዎች? መልሱን ለእነሱው እንተወው እና የኛ የምዕመናን ሃላፊነት እስከምን ድረስ ነው? እነዚህ እውነተኛ አባቶቻችን ለቤተክርስቲያናቸው ሕይወታቸን የተሰውላት፣ በፍጹም ቀናዒነት እና ተቆርቋሪነት ዱር ለዱር ፍርክታ ለፍርክታ ሲሳደዱ ማን ነው አለንላችሁ ሊላቸው የሚገባ፣ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ማንስ ነበር እንደነኚህ እውነተኛ አባቶች ባይሆን ኖሮ ዛሬ ዋልድባ ላይ የስኳር ፋብሪካው የገዳሙን ህልውና ሙሉለሙሉ በተቆጣጠረው ነበር። የገዛ ወገኖቻችን የቤተክርስቲያን ሰዎች ይልቁንም መነኩሳት እነኚህን አባቶች ለራሳቸው ተወዳጅነት ለማግኘት እንደ ማስያዣ ሲጫወቱባቸው፣ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ የስልጣን እርከን ላይ ያሉት አባቶች ዝምታ፣ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚገኙ ካህናት እና መነኮሳት እኛን አይመለከትንም ብለው ፊታቸውን ሲያዞሩ ታዲያ ለነኝህ አባቶቻችን ተጠያቂው ማነው ስለሚደርስባቸውስ ድብደባ እና እንግልት ተጠያቂው ማነው? ስለምንስ ሁላችን በዝምታ ማየት መረጥን?

ነገ ታሪክን እና እውነተኛው ፈራጅ መድኅኒዓለም ክርስቶስ ፍርዱን ይሰጣል እውነተኛ አባቶቻችንን ሃይማኖታቸውን በመጠበቅ በፍጹም ተጋድሎአቸው ታሪክ ለዘለዓለም አይረሳቸውም፣ ነገር ግን መስሎ አዳሪዎችን፣ ታሪክ እና ትውልድ በማንነታቸው ያስታውሳቸዋል ብለን እናምናለን።
እግዚአብሔር አምላክ የእውነተኛ አባቶችን ጸሎት እና ልመና ሰምቶ ገዳመ ዋልድባን ከኢ-ዓማንዊያን ይታደግልን
ቅድስት ቤተክርስቲያንን በረደኤት ይጠብቅልን

8 comments:

 1. It is really indeed. God give his judge for all who betray our church. You know all are dead. Please learn from recent dead of Meles and Patriaric. Stop abuse of monks.

  ReplyDelete
 2. ጊዜ በገፋ ቁጥር የዋልድባ ጉዳይ በበርካታ ክርስቲያኖች ዘንድ እየተረሳ ሊመጣ አይገባውም፡፡ እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ ስለቤተክርስቲያን ልንቆረቆር ነፍሳችንንም እስከመስጠት ልንንቀሳቀስ ይገባል፤ በጸሎት እንትጋ፤ እግዚአብሔር ያጽናን!

  ReplyDelete
 3. please change the font color of the address title. It isn't visible.

  ReplyDelete
 4. bertu bertu egziabher kenante gar yihun

  ReplyDelete
 5. One, who is committed enough should go to waldiba and prove the reality.
  What exactly is the reality? I don't trust EPRDF and its Government, but I don't believe they would involve in such a destructive action knowing that this could cause massive opposition. if you have the real courage and commitment, please try to get the fact yourself with open mind and try to disseminate the fact. We shouldn't trust the Monks only because they are Monks. Any one, who is willing and ready to see the situation from different point of view, must take responsibility to find out the reality. Will really the plan of the Government affect the "Gedam" in any way? I doubt!

  ReplyDelete
 6. በመጀመሪያ ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፥ አስተያየትዎ እንደማንኛውም ሰው ምንም ይሁን ምን ለአስተያየትዎ ታላቅ አክብሮት አለን ነገር ግን በእርሶ አስተያየት ከመሬት ተነስተን እንደምንናገር በማሰብዎ በጣም እናዝናለን፣ እርሶም እንደሚያውቁት በተለየ ከሀገሩ ወጥቶ ጥሮ ግሮ የሚኖር ሰው ጊዜ እና ሰዓት ተርፎት ጊዜውን በእርሶ እይታ ያለትክክለኛ መረጃ ጊዜውን ያጠፋል ብለው በመሰቦ ምናልባት እርሶ ትንሽ ከሪያሊቲው የራቁ ይመስለናል። የሆነ ሆኖ እኛ ትክክለኛ መረጃ እንኳ ባይኖረን እንደእርሶ አባባል we should our facts straight ለነገሩ እስቲ እነዚህን ነጥቦች እንመልከት ለእርሶ መልስ ከመስጠታችብ በፊት፤ እርሶም እንደሚያውቁት አለምም በደንብ እንደሚረዳው ይህ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ስንት መቅለጫዎችን አወጣ ስንት የማስተባበያ interview ተደረገ? ሊያገናዝቡ ቢችሉ መልካም ይመስለናል በተጨማሪ ደግሞ በአቶ አባይ ጸሐዬ አንደበት የተነገሩትስ?
  * "ቅዱሱን ቦታ አልነካንም እንጂ 27 አጽሞችን አውጥተን በክብር አሳርፈናቸዋል"
  * "ለስኳር ፋብሪካው ቅድሚያ ግንባታ እንዲሆን 4 አብያተ ክርስቲያናትን አንስተናል"
  * "ግድቡ ገዳሙን ሊነካው አይችልም ነገር ግን የተወሰነ ደረጃ ውሃው የሚያቁተው በገዳሙ ክልል ነው ለዚህም ከገዳማውያኑ ጋር ንግግር ጀምረናል" ለመሆኑ ሥራ ተጀምሮ ነው ንግግር የሚጀመረው ወይንስ ሳይጀመር ነው? መልሱን ለእርሶ እንተወው
  ከዚህ በተጨማሪ በአቶ ሲሣይ መሬሳ የተሰጠውን የራዲዮ መግለጫ ሰምተዋል?

  * "የተፈነቀሉት አስከሬኖች በሀገር ደንብ በክብር ተቀብረዋል"
  * "መንግሥት ለልማት ቦታውን እስከፈለገው ድረስ፣ የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለበትም"
  * "ከገዳሙ ውጪ ያሉ የሚነሱ ቤተክርስቲያኖች ግምታቸው ተሰጥቷቸው ተነስተዋል"

  እርሶም እንደሚያውቁት ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው ዋልድባ ለመደፈሩ ኢ-አማናውያን የቅዱሱን ቦታ ህልውና እንደደፈሩ የታወቀ ነው የእርሶ ማደናገሪያ ግን ለምን እንደሆነ ሊገባን አልቻለም በምን background እንደሚያወሩም አናውቅም ስለዚህ የእራስዎን አነሳስ ቢመረምሩ ጥሩ ነው እንላለን
  ለማንኛውም ግን በዓሁን ሰዓት በዋልድባ ገዳም አካባቢ ለሚደርሰው ጥፋትና እንግልት የገዳማውያኑ መደብደብ፣ መታሰር፣ ስብእናን መንካት እና ማሰደድ ከምን የመጣ እንደሚሆን ወደፊት ታሪክ እና ትውልድ በታሪክ ይመዘግበዋል የእያንዳንዳችንንም ታሪካችንን የመጠበቅ እና ተቆርቋሪ መሆንን ባጠቃላይ ስለእንቅስቃሴው ያበረከነው አስተዋጽዖ በሙሉ ታሪክ ሲያነሳው ይኖራል እኛንም ታሪክ እና ትውልድ ሊመዝነው በሚችል መልኩ እየሰራን ስለሆነ ለፍርዱ ሳንደርስበት ባንቸኩል መልካም ነው እንላለን
  ለአስተያየትዎ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 7. this is so sad ethiopia has a big land why they want waldeba.this is devil we need to pray .ofcourse GOD going to give them what they desirve.

  ReplyDelete
 8. ትልቁ ችግር እንዴት ይህን ጉዳይ ምእመናን ይወቁት? ሁኔታውን ህብረተሰቡ ቢሰማ መልካም ነበር ነገር ግን ህዝቡ የሚከታተላቸው ሜዲያዎች በሙሉ የመንግስት ደላላዎች ናቸው፡፡

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤