Tuesday, September 25, 2012

በዋልድባ አምላከ ቅዱሳን ተዓምራቱን እያሳየ ነው

የገዳማውያኑ የጸሎታቸው በረከት ይደርብን

 • ቅዱስ ሩፋኤል በእለተ ቀኑ በዋልድባ ዛሬማ ወንዝ ላይ የተሰራውን ድልድይ በመብረቅ ተመቶ ጠራርጎ ወስዶታል
 • በአቲካ ወንዝ ላይ የተሰራው የሸንኮራ ማልማያ ግድብ እንዲሁ በዚሁ ቀን ፈራርሷል
 • የገዳማውያኑ እንግልት እንደቀጠለ ነው
 • ቤተክሕነት በዋልድባ ገዳም ለሚፈርሱት ቤተክርስቲያኖች ካሳ ጠይቋል ይባላል (የተረጋገጠ መልስ ማግኘት አልቻልንም)
(PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ )
እንደሚታወቀው ጳጉሜ ወር የበረከት ጊዜ ናት ይበልጡኑ ደግሞ በእለተ ቅዱስ ሩፋኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በወርሃ ጳጉሜ በውጪ በመውጣት በመጠመቅ እና የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ይደርብን በማለት አሮጌውን ዓመት አሳልፈን
አዲሱን ዓመት በምንቀበልበት ጊዜ ዝናብ ሲመጣ መቼም ሕፃን አዋቂው በውጪ ወጥቶ ይጠመቃል ረደኤት በረከቱን ደግሞ ይጠብቃል፤ ነገር ግን ኢ -አማናውያን ደግሞ ይቀሰፉበታል በእግዚአብሔር ቤት የተዘባበቱን በሃይላቸው እና በክንዳቸው የሚመኩትን ቀሳፊ መላዕክት ተልከው የሰው ልጆችን በፈጣሪ ስራ የተሳለቁትን ይቀስፋሉ ስለዚህ ወርሃ ጳጉሜን ላመነ ረደኤት በረከት የሚያገኝበት ላላመነው ደግሞ የሚቀሰፍበት እና የሰይጣን እና የሠራዊቱ ምሽግ ሁሉ የሚፈርስበት እና የአምላካችን ተዓምራቱ የሚነገርበት ጊዜ ነው ማለት ነው።

ባለፉት ጥቂት ሳምትታት ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ በሚሰራው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሥራውን ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ እንደነበረ ከአካባቢው በደረሱን መረጃዎች ለመገንዘብ ችለናል። እንደሚታወቀው ከጥቂት ወራት በፊት በዋልድባ ገዳም አካባቢ ሊሰራ የታሰበውን ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱን ወስዶ ሥራዎቹን ጀምሮ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን በተለያየ ጊዜ በአካባቢው በደረሰው ተአምራት ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የዲሳይን ኢንጂነሩ በአጋጣሚ በመሞቱ፣ ጥቂት ሰራተኞች በአውሬ በመበላታቸው፣ የግድቡ ሥራ በጣም አዳጋች በሆነ መልኩ መስራት ባለመቻላቸው (ለግድብ ሥራ ጉድጓድ ቆፍረው በነጋታው ሲመለሱ ውሃ ሞልቶት ወይንም አፈር ተንዶ በመሞላቱ) ተደጋጋሚ ክስተቶች በመፈጸማቸው የሱር ኮንስትራክሽን ኮንትራቱን አፍርሶ መውጣቱ ይታወሳል። ኮንትራት አፍርሶ መውጣት (breach of contract) በብዙ ሚሊዮን ብር ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም ሱር ኮንስትራክሽን ባለቤቶቹም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት በዓይናቸው በማየታቸው ቅጣቱን ተቀጥተው ትተው ወጥተው ነበር።

ሱር ኮንስትራክሽን ጥሎ እንደወጣ ኢ-አማናውናኑን ጣዖት አምላኪዎቹን የቻይና ኮንስትራክሽን ካምፖኒዎችን በማስመጣት ሥራዎቹን እንዲቀጥሉ ማድረግ ተችሎ ነበር፤ በመጀመሪያው አካባቢ የአካባቢው ሰው በማንኛውም የቀን ሥራ ተቀጥሮ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመገኘቱ፣ የአካባቢውም ነዋሪዎች በገዳሙ ላይ እንዲህ አይነት ሥራዎችን ሲሰሩ ከማየት ሞታችንን እንመርጣለን በማለት ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ፍጥጫ መፈጠሩ የሚታወስ ነው፤ የመንግሥትም አካላት ምንም ዓይነት ግብግብ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር እንዲፈጠር ባለመፈለግ፣ ቢፈጠር ሊመጣ የሚችለውን የከፋ አደጋ አስቀድሞ በመገመት በወቅቱ ሥራው ትንሽ ጋብ ለማድረግ ተችሎ ነበር። የአካባቢው ገበሬ መሐበራት ሥራቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ወጥተው ስለነበር ለብዙ ጊዜ ያለሥራ መቆየት ባለመቻላቸው በመቀጠል የቻይናው ኮንስትራክሽን ሥራውን ላለፉት ጥቂት ወራት ሲሰራ ቆይቷል በዚህም በዛሬማ ወንዝ ላይ ትልቅ ድልድይ ወደ ገዳሙ ውስጥ logistics ሊያስገቡበት የሚችሉበት ድልድይ ተሰርቶ ነበር ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአቲካ ወንዝ አካባቢ መጠነኛ ግድብ ገድበው ለሸንኮራ ልማት ችግኝ ማፍያ የሚሆን ግድብ ተገድቦ ነበር በነዚህ ጥቂት ወራቶች ውስጥ ነገር ግን የፈጣሪ የአለም መድኃኒት ውጊያው ከባድ ነው ከፍጡራን ጋር ሰዎች ወይም መንግሥታት ጦርነት ገጥመው ወይንም ጎበዛዝት እርስ በርስ በጦር ገጎራዴ ሊጋጠሙ ይችላሉ በዚህም ጎበዝ የሆነው መንግሥት ወይም የጎበዝ አለቃ ያሸንፋል ተሸናፊውም መሸነፉን በጸጋ ተቀብሎ ይሄዳል። ነገር ግን የሀገራችን የኢትዮጵያ መንግሥት ወይንም የስኳር ልማት ሚኒስቴር በጉልበት ሰውን እንደሚያሸንፉ፣ በመሳሪያ ሃይል ሰውን እንደሚያስገድዱ፣ በወገናቸው ብዛት ወይም የስልጣናቸው መጠን እንደሚያሸንፉበት ሳይሆን ተግዳሮቱ ሰማይና ምድርን ከዘረጋው ከፈጣሪ ጋር መሆኑ እጅግ ከባድ ሊያደርገው እንደሚችል የተገነዘቡት አይመስለንም። በመጽሐፍ እንደተገለጸው ፈርዖን ልቡ ደንድኖ የፈጣሪን ትዕዛዝ ባለመቀበሉ 10 ተዓመራትን በግብጽ ምድር ላይ ሊታይ ችሏል ጓጉንቸር ከሰማይ ዘንቧል፣ ቅማል ምድሪቱን ወርሷታል፣ የደም ዶፍ ወርዶባቸዋል ያም አልበቃ ብሎ የግብጽን የበኩር ልጆች በመቅሰፍት ተመተዋል በመጨረሻ ግን የእግዚአብሔር ሃይል በልጦ እስራኤላውያን ወደ ተሰፋይቱ ምድር ለመሄድ በመሪያቸው በሙሴ አማካኝነት ከግብጽ 400 ዘመን ባርነት ወጥተው ነበር። ዛሬ በኛ ሀገር እንዴት እነዚህ በቅዱሳን መጽሐፍት የተጻፉ ታሪኮች እና የእግዚአብሔርን ሃያልነት የሚያስገነዝቡ ትምህርቶች ለመማር አለመቻላችን እስከ አሁን የሀገር መዋዕለ ንዋያት እና ሃብት ዝም ተብሎ ለጎርፍ እና ለመቅሰፍት መዳረጋቸው ያሳዝነናል።

ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው በጳጉሜ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ. ም. መብረቅ ቀላቅሎ የወረደው ዝናብ በዋልድባ ገዳም በቻይና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ላለፉት ወራት ሲገነቡ የነበሩ ግንባታዎች በሙሉ ለታሪክ እንኳን ምንም ሳይቀር በመብረቅ እና የዝናም መዓት ተመተው ድራሻቸው መጥፋታቸው ለአምላከ ቅዱሳን መድኅኒዓለም ክርስቶስ ምን ይሳንሃል ያሰኘ ክስተት ነበር፤ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ እንደተናገረው " . . .ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን የሰጣል ይላል . . ." ስለዚህ ዛሬም እግዚአብሔር ለተገፉት፣ ለተገረፉት፣ ለተደበደቡት ገዳማውያን አባቶቻችን ሃይሉን ሰጥቷቸው በጸሎታቸው ሃይል እንኪሁም በአምላካችን ቸርነት በዛሬማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በመብረቅ ለወሬ እንዳይመች ሆኖ በጥፋቱ በአቲካ ወንዝ ለሸንኮራ ማፍያ የተገደበው ግድብ እንዲሁ በጎርፍ ሙላት ሙሉ ለሙሉ ከነሸንኮራ ችግኝ ማፍሊያ እና የተለያዩ ከባድ እና ቀላል machinery በአንድነት በአንድ ጀምበር ድምጥማቱ መጥፋቱ "የአምላክ ሥራ መርቀቁ" የሚያስብል ሆኖ አልፏል ከዚህም ጊዜ ጀምሮ በምንም መልኩ የቻይናው የኢ-አማናውያኑ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሊያንሰራራ ባለመቻሉ እስከ አሁኗ ቀን ድረስ ሥራው ሊጀመር አልቻለም ቢጀምሩም እንደገና ከዜሮ መጀመራቸው የማይቀር በመሆኑ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ይልቁንም አቶ አባይ ጸሐዬ በሚመሩት የሥኳር ልማት መስሪያ ቤት ውስጥ የተለያዩ ሃሳቦች እየተነሱና በዚህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችም ሃሳባቸው እየተከፋፈለ መምጣኑን ሰምተናል። 
የዚህ ዝግጅት ክፍል እንደሚያምነው "ተግዳሮቱ ከፈጣሪ ጋር በመሆኑ ይቅር ባይ ነን፤ የፈርዖንን ልብ የያዘ ደግሞ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል በዓይናችን የምናየውን ማየት ከተሳነን" ምከረው ምከረው፤ አልመለስ ካለ መከራ ይምከረው የሚለውን የአባቶቻችንን አባባል እኛም ለመድገም እንገደዳለን።

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ በዚሁ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እግዚአብሔር መዓቱን አውርዶ እነዚህ ግድብ እና ድልድይ ከፈረሱ በኃላ የአካባቢው ጸጥታ ሰዎች በገዳሙ ውስጥ በመግባት አባቶችን ማወክ እና መደብደብ ጀምረው "የእናንተ መተት ነው" በማለት ሲያውኩ አንድ ስማቸው ክንፈ ገብርኤል የተባሉ መናኝ "የግድቡ እና የድልድዩ አይግረማችሁ፣ ይህንን ገዳም ለማፍረስ የተነሳ ሥራው ብቻ ሳይሆን እራሱ ይፈርሳል" በማለት በሃለቃል ለታጣቂዎቹ ነግሯቸው፣ ታጣቂዎቹም በአጸፋው መናኙን ክፉኛ ደብድበዋቸው ክፉኛ በመቁሰላቸው ማይገባ በሚባል ከገዳሙ የሰባት ሰዓት መንገድ የሆነ ጤና ጣቢያ ተወስደው በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን እና በአሁን ሰዓት በማገገም ላይ እንደሚገኙ ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

ባለፈው አቶ አባይ ጸሐዬ ከመነኮሳቱ ጋር ንግግር ባደረጉበት ጊዜ አንድ ነገር ነግረዋቸው ነበር እስሱም እናንተ ለምንድነው እንዲህ የምትሉት "ቤተክህነቱ እኮ ካሳ ለፈረሱት እና ለሚፈርሱት 18 ቤተክርስቲያኖች ጠይቀዋል" በመለት ለመነኮሳቱ ነግረዋቸው ነበር፥
ነገር ግን ይህንን ዜና በትክክል ቤተክህነቱ እንዳደረገው የተጨበጠ መረጃ የለንም፣  ነገር ግን እንደመላምት መንግሥት በማንኛውም መንገድ ቤተክህነቱን እና መነኮሳቱን ለማለያየት እርስ በእርሳቸው ለማጣላት የሚያደርገው ሴራ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፤ ነገሩም በእውነት በቤተክህነቱ በኩል ከመንግሥት ለሚፈርሱት 18 ቤተክርስቲያኖች ካሣ ተጠይቆ እንደሆነ ሊሆን የሚችለው በሁለት በኩል እንደሚሆን ይገመታል ይህም:
፩ኛ/ በቅዱስ ፖትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኩል በዚህም ደግሞ (ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ወይም ብጹዕ አቡነ ገሪማ) በቀጥተኛ ይመለከታቸዋል፤
፪ኛ/ በቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ በኩል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል
በእውነት ጉዳዩ ተፈጽሞ ከሆን ከሁለቱ የቤተክህነቱ ጽ/ቤቶች በስተቀር በማንኛውም የቤተክህነቱ አካል ከመንግሥት ጋር እንዲህ አይነት ሊደረግ እንደማይችል እናምናለን፥ እነዚህን ያሉትን መላምቶች ለማረጋገጥ ወደ ቤተክህነቱም በመደውል ለማረጋገጥ ሞክረናል፥ በዚህም ያገኘናቸው ሰዎች እንደነገሩን በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በኩል እንዲህ አይነት ነገር እንደማያደርጉ እንደማይሞክሩ በእርግጠኝነት ሊያረጋግጡልን ችለዋል። የቀረነ ቢኖር ቅዱስ ፖትርያሪኩን አፈሩ ይቅለልላቸው እና መረጋገጥ ባንችልም ብጹዕ አቡነ ገሪማ ጋር ተደጋጋሚ ሞክረን ነበር ነገር ግን አልተሳካልንም። 

ዋልድባ ገዳም በመድኅኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የድንጋይ ቆብ ቀርጾ ባመነኮሳቸው መነኮሳት የተገደመ ገዳም እንደመሆኑ መጠን ችግሩ ምን ቢጸና፣ ምን ያህል አባቶቻችን መነኮሳት እና እናቶቻችን መነኮሳይት ቢንገላቱ እና ቢሰደዱ፣ በገዳሙ ውስጥ የሰው ዘር እንኳ ቢጠፋ በፍጹም ልንገነዘበው የሚገባን የገዳሙ መስራች እና የቤተክርስቲያናችን ጉልላቷ ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ሊተዋት አይችልም መንግሥታት፣ ጎበዛዝት፣ ሃይለኞች ፣ በለጊዜዎች እና ባለመሣሪዎች በሙሉ ሰማይና ምድርም ሳይቀሩ ያልፋሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እና የፈጣሪያችን ቃሉ ለዘልዓለም ህያው ሆነው እስከ ዓርያም ይኖራሉ። ዋልድባም ከነሙሉ ክብሩ በመድኅኒታችን ጠባቂነት እና ረደኤት ከትውልድ ትውልድ መተላለፉ ጥርጥር የሌለው እውነታ ነው።
መድኅኒዓለም ክርስቶስ ዘወትር በተዓምራቱ እና በቸርነቱ ያልተለየን የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን

ቸር እንሰንብት 

3 comments:

 1. I strongly believe that the non-believer Melese Zenawi died because of Waldiba. Next will be Abay Tsehaye. You infidels be better believe in Almighty EGZIABHER. or else go to hell like Melese for eternity. Our GOD is GREAT!!!

  ReplyDelete
 2. Amen! YeEwinetegnoch Abatoch tselot ena m'lja ay'leyen!
  Its cristal clear that True Ethiopia & Ethiopians are safegarded by Almighty God's Mercy n Power as long as Holy Covenants b/n God n Humanity are Observed by we z human being.
  4mr info, we can cosult a book entitled "Ethiopia: the Classic Case." or z Amharic version- "ItiyoPya: yeAlemu Mefareja!"

  ReplyDelete
 3. የገዳም አባቶችና ሕዝበ ክርስትያን በሙሉ አይዞችሁ በአንድነት በርትተን ከጸለይን “እግዝአብሔር ታላቅና ሐያል ዓምላክ ነው” አቶ አባይ ፀሐየን በዋልድባ ያስቀራቸዋል:: ተወደደም ተጠላ የዘንድሮው ተረኛ እሳቸው ናቸው:: የሜያሳዝነው ልባቸው ሳያምንበት ለመኖር ብለው አብረው የሜሮጡት ያለ እንደነበረከት ስሙኦን አይነቱ ነው:: አንድ ነገር ልናገር ይህ የዋልድባ መናንያን ስቃይና ግፍ የህዝበ ክርስትያን ሃጥያት ያመጣው መዘዝ ሰለሆነ ግድ ይላል :: እኛ መእመን በቀን ሶስት ግዜ አገርንና በተክርስትያንን በተመለከተ እጃችንን በአንድ ልብ ብናነሳና ብንፀልይ ፀጥ ረጭ ማድረግ የሜያውቀው አምላክ በፊታችን ይቆማል:: እባካችሁ ህልናችሁን ሰብሰብ አርጋችሁ ልትሰሙኝ ሞክሩ:: አሜን

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤