Wednesday, October 24, 2012

ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ እርቀ ሰላሙ እንዲቀጥል ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ደብዳቤ ላከ


ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ጊዜያዊ ኮሚቴ የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲመጣ፣ የአባቶች አንድነት እና የሕዝበ ክርስቲያኑ በአንድነት መቆምን በመማፀን በሀገራችን ኢትዮጵያ ለሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዲሁም በውጪው ዓለም ለሚኖሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፬ኛ ፖትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው የተማጽኖ ደብዳቤዎችን ከጥቂት ቀናት በፊት ልኳል፡፡


 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ለኢትዮጵያ ኦርቶኦክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ጉዳዩ፤ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንና የአባቶቻችንን አንድነት ይመለከታል

Tuesday, October 23, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ


  • የሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ:: 

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የ2005 ዓ.ም ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ትናንት ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ አምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም የሚጀምረው ምልአተ ጉባኤው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት አስቸኳይ ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ኹኔታ፣ በፓትርያርክ አመራረጥ ሕግ ረቂቅ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ካለፈው ምልአተ ጉባኤ በተላለፉ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ 31ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለስድስት ቀናት በቆየበትና በአጠቃላይ ጉባኤው ታሪክ የተለየ ገጽታ በታየበት የስብሰባ ዝግጅት የተመከረባቸው የመዋቅር፣ የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ ውሳኔ ሐሳቦች ላይም እንደሚመክር ተመልክቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤ እንዲያጸድቀውና የሥራ መመሪያ አድርጎ እንዲያስተላልፈው አጠቃላይ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳቡንና የአቋም መግለጫውን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያቀረበበት ቃለ ጉባኤ 33 ነጥቦችን እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Monday, October 8, 2012

ዋልድባን ለመታደግ በዋሽንግተን ዲሲ ትላንት ጉባኤ ተደረገ፣ ይበል የሚያሰኙ እንቅስቃሴዎችም ተደርገዋል

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

በትላንትናው ዕለት መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች አንድነት (ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል) አስተባባሪነት የተጠራው ጉባኤ ተካሂዶ ውሏል። በጉባኤውም ላይ ካህናት አባቶች፣ ሰባኬ ወንጌል፣ እንዲሁም በርካታ ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው በመጡ የጉባኤው ታዳሚዎች በተገኙበት በርካታ ቁም ነገሮችን ተነጋግሮ እና ጉባኤው ተጠቃሏል። በቀጣይነትም ሥራዎችን በእቅድ ይዞ ለመሥራት ብሎም በአባባቢው የሚገኙትንም መዕመናን እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን በማስተባበር ለሥራ የተነሳሱ ካህናትን፣ መምህራንን፣ ዘማሪያን፣ በትውልድ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በምዕራቡ አለም በተለያየ ሀላፊነት ላይ ያሉትን ምሁራንን እንዲሁም አጠቃላይ የኢት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በማስተባበር የዋልድባ ገዳም መፍረስ ሳይሆን አፈሯ እንኳን እንዳትነካ (ሳትነካ) ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ቁርጠኝነት ያሳዩበት እና በብዙ ሃዘንም እየደረሰ ያለውን እንግልት በተለያየ መልኩ ለማሳየት ተሞክሯል።


Saturday, October 6, 2012

የአዲስ ድምጽ ራዴዮ ስለ ዋልድባ ገዳም ያደረገው ቃለ ምልልስ


መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓም በአዲስ ድምጽ ራሬዮ ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው የዋልድባው ገዳም አባት "እኛ ያልነው ገዳማችሁን ጠብቁ፣ ቅርሳችሁን ጠብቁ ፣ ታሪካችሁን ጠብቁ ነው" ያልነው ለሃይማኖታችን መቆም እንዴት ፖለቲከኛ ያስብለናል ነበር ያሉት። በሀገር ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ታሪካቸውን እና ገዳማቸውን የመጠበቅ ብሎም ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት እንዳለባቸውም አበክረው ገልጸዋል።
ልብ ያለው ልብ ይበል ነበር ያሉት
የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት ከእኛ ጋር ይሁን

Wednesday, October 3, 2012

ቱባ ባለሥልጣናት ወደ ዋልድባ ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተነገረየገዳማውያኑ የጸሎታቸው በረከት ይደርብን

·         አቶ አባይ ፀሐዬ የጀመሩትን እጅ የመጠምዘዝ ስራ እንደሚቀጥሉ ይገመታል
·         ባለፈው ከአቶ አባይ ፀሐዬ ጋር የተገናኙት መነኮሳት ተቃውሞ ገጠማቸው
·         ክንፈ ገብርኤል የተባሉት መናኝ ታስረው ወደ ማይ ጸብሪ መወሰዳቸው ተዘገበ
·         ቤተክህነቱ በዝምታው እንደቀጠለ ነው
PDF ለማንበብ ይጫኑ
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በርካታ የመንግሥት ባለ-ሥልጣናት ወደ ዋልድባ በመሄድ የሦስቱንም ማኅበራት አባቶች እንደሚያነጋግሩ ተነግሯል። የዋልድባ መነኮሳት እና ማኅበራቱ በጠቅላላው ምንም ዓይነት በገዳሙ ስም ድርድር ማድረግ እንደማይፈልጉ እና እንደማይችሉ ቢገልጹም ነገር ግን አቶ አባይ ጸሐዬ፣ አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት ወደ ቦታው በመሄድ ቢቻልም እጅ ጠምዝዞ ለማሳመን እና የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በቀጣይነት ስራውን እንዲቀጥል ለማግባባት ወደ ቦታው ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። የገዳሙ አባቶች የሰቋር ኪዳነ ምሕረት የአንድነት ገዳም፣ የዳልሻህ ኪዳነምሕረት ገዳም፣ እንዲሁም የአበረንታት ገዳም ተጠሪዎች በጉዳዩ የተነጋገሩበት ሲሆን እነሱም ውሳኔው የእነሱ ማለትም የገዳማውያኑ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በሙሉ ውሳኔ እንደሆነ እና በእነሱ በኩል ሊመጣ የሚችለውንም ፈተና በሰማዕትነት እንደሚቀበሉት እና በዚህ ቅዱስ ቦታ ምንም ዓይነት ድርድር ሊገባም እንደማይገባ እና መነኮሳቱ ብቻቸውን ለመወሰን መብት እንደሌላቸውም ተናግረዋል።