Tuesday, November 27, 2012

ዛሬ ረፋዱ ላይ የመንግሥት ተወካዮች ከዋልድባ መነኮሳት ጋር በማይጋባ ተነጋገሩ


የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት ይደርብን
ዛሬ ረፋዱ ላይ አንድ ማንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ባለሥልጣን፣ የሥኳር ፋብሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አማናይ መስፍን የሥኳር ፋብሪካው ፕሮጀክት የበላይ ተቆጣጣሪ እንዲሁም ጥቂት የአካባቢው የመንግሥት ሹማምንት በተገኙበት በወልቃይት ወረዳ ማይገባ ከተማ ላይ ወደ ሃያ የሚጠጉ መነኮሳት ጋር ስብሰባው ተካሂዶ ነበር። በስብሰባውም ላይ የተሳተፉት ከአበረንታንት መድኅኒዓለም ዋልድባ የአንድነት ገዳም የቤተ - ሚናስ እና የቤተ - ጣዕመ ማኅበራት ቢኖሩም በዛሬው ስብሰባ ላይ ከተገኙት መነኮሳት መካከል አንድም ከቤተ - ጣዕመ የመጣ መነኮሴ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል። በስብሰባው ላይ የተገኙት መነኮሳት ቁጥር ወደ ሃያ የሚጠጉ ሲሆን በሙሉ የመጡት ከቤተ - ሚናስ ዋልድባ የሆኑና ከዚህ በፊት ቆራጥ ውሳኔያቸውን ያሳዩና በወሳኔያቸውም ምንም ለውጥ እንደሌለ ያሳወቁት የመነኮሳቱ ቡድን በቀጣይነት በቀጠሮ የስብሰባ ጊዜ ቢሰጣቸውም ወሳኔያቸው ምንም ለውጥ እንደማይኖረው አስቀድመው ለመግለጽ ሞክረዋል።

Monday, November 26, 2012

ነገ ማይገባ ላይ የመንግሥት ተወካዮች እና የአበረንታንት መነኮሳት ስብሰባ ያደርጋሉ


በነገው እለት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች እና ወደ 30 የሚጠጉ የዋልድባ አበረንታት ገዳማውያን ለስብሰባ ማይገባ ላይ ስብሰባ እንደሚደረግ ከአካባቢው ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ ስብሰባው በተለየ መልኩ የዋልድባ አበረንታት ገዳማውያንን ብቻ የተጠራበት ምክንያት በተለይ መንገሥት ገዳማውያኑን ለመለያየት እና ለየብቻ በማነጋገር ይልቁንም እጆችን በመጠምዘዝ ሥራዎችን ለማቃናት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ጠቋሚ ነው ብለዋል። እንደሚታወቀው ዋልድባ በሰቋር የአንድነት ገዳም፣ የዳልሻሕ የአንድነት ገዳም እና የአበረንታት አንድነት ገዳም በሦስቱ ማኅበራት በጋራ በአንድነት በተመሳሳይ ህግና ሥርዓት ለለፉት በርካታ ዓመታት አንድነታቸውን ጠብቀው የኖሩ ማኅበራት ናቸው፥ ምንጮቻችን እንደገለጹት በነገው እለት ለሚደረገው ስብሰባ የአበረንታትን ገዳማውያብ ብቻ ለይቶ መጥራት ያስፈለገውም በገዳማውያኑ መካከል ልዩነቶችን ለመፍጠር ብሎም ለመለያየት እና መንግሥት ያሰበውን ገዳሙን የማፍረስ እና ታሪክን የመበረዝ ሥራዎችን ለመሥራት የዘየደው እቅድ እንደሆነ ይገመታል።

የዋልድባ ኮሜቴ ከአላስካ ሴናተር ማርክ ቢጊች አማካሪ ጋር በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው ተነጋገሩ


ከግራ ወደቀኝ
ቀሲስ ሶሎሞን፣ ቴዎድሮስ፣ ማቲው፣ የአብስራ፣ ሴናተር ማርክ፣ ሳምሶን
ባለፈው ሳምንት ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው የዋሽንግተን ዲሲ ኮሜቴ በዋልድባ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአላስካ ግዛት ሴናተር ማርክ ቢጊች የስራ አስኪያጃቸው ከሆኑት ሚስተር ማት ፔይን በጽፈት ቤታቸው ተቀብው አነጋግረውታል።  ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት ሴናተር ማርክ በዚሁ ቀን እለት ከቀትር በኃላ ከኢትዮጵያው የአሜሪካን አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ ጋር በጽ/ቤታቸው እንደሚነጋገሩ ገልጸው በግንኙነታቸውም ወቅት ሊያነሷቸው ካሰቡት ነጥቦች የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የሰብዓዊ መብጥ ጥበቃ እና ክብካቤ በተጫማሪ የዋልድባ ገዳም እና በገዳሙ ክልል ዙሪያ ለመስራት ብዙ ጥረት እየተደረገ ባለው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ እንደሆነ አስረድተዋል።

የዋልድባ መነኰሳት “ኳሬዳ” በተሰኘ ትልና ምስጥ ተቸግረዋል


  • ለመነኰሳቱ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብና የአልባሳት እርዳታ ጥሪ ቀርቧል
(አንድ አድርገን ህዳር 10 2005 ዓ.ም)- በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የሚገኘውየጥንታዊው ዋልድባ ደልሽሐ ኪዳነ ምሕረት ማኅበረ ደናግል ገዳም ሴት መነኰሳት ኳሬዳ በተሰኘ ትልናበአካባቢው በብዛት በሚፈላው ምስጥ መቸገራቸውን ለገዳሙ የራስ አገዝ ልማት ርዳታ ለማሰባሰብየተቋቋመው ኮሚቴ ገለጸ፡፡ ትሉ መነኰሳቱ ለዘመናት የኖሩባቸውን ጎጆ ቤቶች /የሣር መክደኛምቹመራቢያ እንዳደረገው የተገለጸ ሲሆን ትሉን በምትገበው ኩቱ የተባለች ወፍ በሚራገፍበት ወቅትበመነኰሳቱ ቆዳ ላይ እያረፈ ሰውነታቸውን ያሳብጣል፤ ዕብጠቱ ከሚፈጥረው ሥቃይ ለመዳን መነኰሳቱሰውነታቸውን በምላጭ ስለሚበጡት ተጨማሪ ጉዳት እያስከተለባቸው ነው፡፡ በአካባቢው በብዛትየሚፈላው ምስጥ ሌላው የማኅበረ ደናግሉ ፈተና መኾኑ ሲሆን አረጋውያትና ሕሙማን መነኰሳትየሚረዱባቸውን የአልጋ ቆጦችና የቤት ቋሚዎች እየቦረቦረ በመጣል ለጉዳት እየዳረጋቸው መኾኑ ታውቋል፡፡

Thursday, November 8, 2012

ለቤተክርስቲን ሰላም፣ ስለ እርቀ ሰላሙ፣ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናንና ምዕመናት የስልክ ውይይት ምድረክ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ተለያይተው የነበሩ አባቶቻችን የቤተክርስቲያን መሥራቿ እና የማዕዘን ራስ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ባወቀው መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል በመሆኑም እስከዛሬ አባቶች ተለያይተው፣ ከዛም አልፎ ምዕመናን ተለያይተው የቆዩበትን የመለያየት ዘመን እንደነበረ ሁላችንም እናስተውሰዋለን ፣ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ካጋጠሟት በርካታ ፈተናዎቹ መካከል ዋነኛው እንደሆነ ሁላችንም የምንገነዘበው እውነታ ነው። በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምዕመናን እና ካህናት አስተባባሪ ኮሚቴዎች ለቤተክርስቲያን አንድነት ባላቸው ትጋት በምዕመናን እና በካህናት ተዋቅረው ሕዝበ ክርስቲያኑ ሲናፍቀው የነበረውን ሰላም የእርቀ ሰላሙን ኮሚቴ በማገዝ ሰላሙን ለማምጣት ከምዕመናን እስከ ሊቃነ ጳጳሳት ባሉት የቤተክርስቲያኒቱ አካላት ዘንድ ከባድ ርብርብ እየተደረገ በሚገኝበት በዚህ በአሁኑ ሰዓት ይልቁንም፣ በመጪው ሕዳር ወር በዳላስ ቴክሳስ የሚደረገውን የእርቀ ሰላም ጉባኤ ያግዙ ዘንድ የተመረጡት የምዕመናን እና የካህናት ተዋካዮች ጋር የስልክ ጉባኤ በመጪው እሑድ ስለሚደረግ እያንዳንዱ ሰላም ወዳድ ሕብረተሰብ ለዚህ ሰላም የበኩሉት ጥረት እንዲያደርግ የምዕናናን እና የካህናት ተወካዮች በአክብሮት ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ሀገራችንን እና ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን በረደኤት ይጠብቅልን
ለቤተክርስቲያን ሰላም የበኩልዎን ያበርክቱ!


“ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ”  ሐዋ 13፥15
“ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን።” መዝ 122:6
“በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” ኤፌ 4:3
ሙሉ ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ