Monday, November 26, 2012

ነገ ማይገባ ላይ የመንግሥት ተወካዮች እና የአበረንታንት መነኮሳት ስብሰባ ያደርጋሉ


በነገው እለት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች እና ወደ 30 የሚጠጉ የዋልድባ አበረንታት ገዳማውያን ለስብሰባ ማይገባ ላይ ስብሰባ እንደሚደረግ ከአካባቢው ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ ስብሰባው በተለየ መልኩ የዋልድባ አበረንታት ገዳማውያንን ብቻ የተጠራበት ምክንያት በተለይ መንገሥት ገዳማውያኑን ለመለያየት እና ለየብቻ በማነጋገር ይልቁንም እጆችን በመጠምዘዝ ሥራዎችን ለማቃናት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ጠቋሚ ነው ብለዋል። እንደሚታወቀው ዋልድባ በሰቋር የአንድነት ገዳም፣ የዳልሻሕ የአንድነት ገዳም እና የአበረንታት አንድነት ገዳም በሦስቱ ማኅበራት በጋራ በአንድነት በተመሳሳይ ህግና ሥርዓት ለለፉት በርካታ ዓመታት አንድነታቸውን ጠብቀው የኖሩ ማኅበራት ናቸው፥ ምንጮቻችን እንደገለጹት በነገው እለት ለሚደረገው ስብሰባ የአበረንታትን ገዳማውያብ ብቻ ለይቶ መጥራት ያስፈለገውም በገዳማውያኑ መካከል ልዩነቶችን ለመፍጠር ብሎም ለመለያየት እና መንግሥት ያሰበውን ገዳሙን የማፍረስ እና ታሪክን የመበረዝ ሥራዎችን ለመሥራት የዘየደው እቅድ እንደሆነ ይገመታል።


የአበረንታት የአንድነት ገዳም 30 የሚሆኑ መነኮሳትን መርጠው እንዲልኩ የተጠየቁትም ለዚሁ ለያይተህ ግዛው በሚለው መርህ በሰረት እንደሆነ የሚያምኖቱ የመነኮሳቱ ቡድንም ለስብሰባው ሰላሳ የሚሆኑት ሳይሆኑ ሃያ የሚጠጉ መነኮሳት በስብሰባው ለመገኘት ወደ ማይገባ እንደሚሄዱ ተነግሯል፤ የአበረንታት ተወካይ መነኮሳት ከዚህ በፊት በአባ ነፃ ላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ የገለጹት አቋማቸች ዛሬም ተመሳሳይ እንደሆነ እየገለጹ ነው፤ በገዳሙ የተወከሉት የመነኮሳት ቡድንም እኛ መሬት ጠባቂዎች ነን፣ ቦታው የመድኅኒዓለም ነው እኛ መሬቱን ለልማትም ሆነ ለማንኛውም ነገር መስጠትም መፍቀድም አንችልም የሚል አቋም ነው የያዙት። የሆነ ሆኖ ስብሰባው በተጠቀሰው ቦታ እና ጊዜ እንደሚካሄድ ይጠብቃል።
በሰቋር እና ዳልሻሕ የአንድነት ገዳሞች አካባቢው የስብሰባው ጥሩ ያልሆነ ስሜትን እንዳሳደረ ለመረዳት ችለናል፣ ይበልጥ ደግሞ በሰቋር ዋልድባ ገዳም የሚገኙት አባቶች እና እናቶች ጠንካራ የሆነ አቋም ስላላቸው፣ ገዳማችንን ከምታርሱ እና ለሌላ ከምታውሉት እኛን ቀድማችሁ ገላችሁ ላልሆነ በሚል ቁርጥ የሆነ አቋም በመያዛቸው የመንግሥት ተወካዮች ነገሮችን በማዞር “እነሱ የአማራው አቀንቃኞች” ናቸው በማለት በተደጋጋሚ ሲነገር ተሰምቷል። ሰቋር ዋልድባ የሚገኙ እናቶች ከጥቂት ወራት በፊት በዓዲር ቃይ ስብሰባ በተገኙበት ወቅት ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕን ጨምሮ ለመታዘዝ ፈቃደኝነታቸውን ያልገለጹበት እና አቡነ ኤልሣዕም እገዝታችኃለሁ ብለው እንደነበር እና ከዛ ጊዜ ጀምሮ የሰቋር ገዳም መነኮሳትን ጉዳዩ እናንተን አይመለከትም፣ የናንተ ገዳም አልተነካም በማለት በተለያየ ጊዜ ሲያገሏቸው እና ሊለያዩዋቸው እንደሞከሩ በተለያየ ጊዜ ተሞክሯል፤ ዛሬም በዚህ የውሳኔ ሰጪ ስብሰባ ላይ የሰቋር እና የዳልሻሕ መነኮሳት አባቶች ለስብሰባው አለመጠራታቸው ይበልጡኑ ጉዳዩን እንዳያከረው እየተፈራ ነው።
በተያያዘ ዜና መንግሥት እጣኖ ማርያም አካባቢ የሚገኘውን የገዳሙ ይዞታ የሆነውን የእርሻ መሬት እየረሰ በማበላሸቱ እና ይልቁንም የተባለው የሥኳር ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሮ እስኪያልቅ እንኳ ግልጋሎት እንዳይሰጥ እና ገዳማውያኑ እንዳይጠቀሙበት ከአገልግሎት ውጪ አድርገውታል በዚህም ገዳምውያኑ ትልቅ የሆነ የምግብ እጥረት እና አቅርቦት እጥረት እንደሚያጋጥማቸው እየተፈራ ነው፣ እንደሚታወቀው የገዳሙ ይዞታ የሆነው የዕጣኖ ማርያም የእርሻ መሬት ለገዳሙ አይነተኛ የሆነው የቋርፍ (የሙዝ ተክል) የሚመረትበት ይሄ ቦታ እንደነበር ገዳማውያኑ በሃዘኔታ ይናገራሉ፥ ይሄንን ቦታ ቀድሞውን ምርት እንዳይሰጥ ገዳማውያኑ እንዲራቡ ለማድረግ የተሞከረው በአንድም በሌላም ምክንያት ገዳሙን ለመፍታት በመንግሥት እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት መመልከቻ እንደሆነ ለመጠቆም እንወዳለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቆላ ወገራ አካባቢ የሚገኙ ገበሬዎች በእጣኖ ማርያም የደረሰውን በመመልከት በአካባቢው ከሚገኝ ሰራተኞች ጋር በተለያየ ጊዜ ብዙ አምባ ጓሮ ተነስቶ እንደነበር እና የአካባቢው ገበሬ ማኅበራት ከአካባቢው ለቀው እስካልሄዱ ድረስ እኛ እዚህ እያለን እንዲህ ዓይነት ሥራ ሲሰሩ እየየን መኖር አንችልም በመለት እንደሚዝቱ እማኞች ጨምረው ገልጸዋል።
ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በረደኤት ይጠብቅልን 

2 comments:

  1. you evil TPLF should learn from Melese's death!!!!!!

    ReplyDelete
  2. Ebakachiwu astadadariwochachin sila egziabiher bilachiwu atigidalun.

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤