Tuesday, November 27, 2012

ዛሬ ረፋዱ ላይ የመንግሥት ተወካዮች ከዋልድባ መነኮሳት ጋር በማይጋባ ተነጋገሩ


የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት ይደርብን
ዛሬ ረፋዱ ላይ አንድ ማንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ባለሥልጣን፣ የሥኳር ፋብሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አማናይ መስፍን የሥኳር ፋብሪካው ፕሮጀክት የበላይ ተቆጣጣሪ እንዲሁም ጥቂት የአካባቢው የመንግሥት ሹማምንት በተገኙበት በወልቃይት ወረዳ ማይገባ ከተማ ላይ ወደ ሃያ የሚጠጉ መነኮሳት ጋር ስብሰባው ተካሂዶ ነበር። በስብሰባውም ላይ የተሳተፉት ከአበረንታንት መድኅኒዓለም ዋልድባ የአንድነት ገዳም የቤተ - ሚናስ እና የቤተ - ጣዕመ ማኅበራት ቢኖሩም በዛሬው ስብሰባ ላይ ከተገኙት መነኮሳት መካከል አንድም ከቤተ - ጣዕመ የመጣ መነኮሴ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል። በስብሰባው ላይ የተገኙት መነኮሳት ቁጥር ወደ ሃያ የሚጠጉ ሲሆን በሙሉ የመጡት ከቤተ - ሚናስ ዋልድባ የሆኑና ከዚህ በፊት ቆራጥ ውሳኔያቸውን ያሳዩና በወሳኔያቸውም ምንም ለውጥ እንደሌለ ያሳወቁት የመነኮሳቱ ቡድን በቀጣይነት በቀጠሮ የስብሰባ ጊዜ ቢሰጣቸውም ወሳኔያቸው ምንም ለውጥ እንደማይኖረው አስቀድመው ለመግለጽ ሞክረዋል።

በዛሬው ስብሰባ ከመንግሥት ተወክለው የመጡት ሰዎች አቶ አማናይ መስፍንን ጨምሮ መነኮሳቱን ሥራውን አሁን ልንጀምር ስለሆነ በሥራው ወቅት ለሚነሱት ቤተክርስቲያኖች መንግሥት ካሳ ለመክፈል ፈቃደኛ እንደሆነ እና ማንኛውንም ቦታ በምትኩ ሊሰጥ እንደሚችል ለመጡትም አባቶች አስፈላጊውን እንክብካቤ ሊያደርግላቸው እንደሚችል ለማሳመን በተለያየ መንገድ የሞከሩት የመንግሥት ተወካዮች እንደ እስካሁኑ በግድ ወይም በጉልበት በማንገላታት፣ በድብደባ፣ በእስር በማስፈራራት የሞከሩት መንገድ  ሊያስኬዳቸው እንዳልቻለ በመገንዘብ ይመስላል በተለያየ መንገድ ቢሞክርም ገዳማውያኑ አባቶቻችን “የአባቶቼን ርስት እሰጥ ዘንድ እግዚአብሔር ከኔ ያርቅ” መጽ. ነገ. ቀዳ. ፳ ፥ ፫ በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት ለእናንተን ካሳ፣ ወይም ማንኛውንም መደለያ የምንቀበል አይደለንም ለዚህም ነው በገዳም ተወስነን የምንኖረው በማለት ይመስላል ስጦታቸውንም ሆነ ማስፈራሪያቸውን ለመቀበል ፈቃደኞች ሳይሆኑ በመገኘታቸው የተለየ ተጽዕኖ እና ማስፈራራት በቀጣይነት እንደሚደርስባቸው ይታወቃል፤ "አቋማችን ቤተክርስቲያናችንን ማስከበር፣ ገዳማችንን መጠበቅ" ነው በማለት ቆራጥ የሆነ አቋማቸውን ገልጸውላቸዋል።
ሌላው አስገራሚው ነገር በዛሬው ስብሰባ ላይ የቤተ ጣዕመ መነኮሳት አባቶች አለመገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሟል፥ ምክንያቱም በተለያየ ጊዜ የቤተ ጣዕመ መነኮሳት እንደተናገሩት የልማት ተቃውሞ የለንም፣ መንግሥት ልማቱን ያልማ ችግር የለውም፣ ልማትን የሚቃወሙት ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ሃይሎች እንዲሁም የፖለቲካ ሰዎች ናቸው በማለት መነኮሳቱን ከመንግሥት ጋር በመወገን ሲኮንኑ እንደነበረ  ይታወቃል፣ ከዚህ በተጨማሪ የቤተ ጣዕመ እና የቤተ ሚናስ መነኮሳት ከዚህ በላይ እራሱን የቻለ ሌላ ችግር እንዳለ እና ቤተክህነቱም ሁለቱን ማኅበራት ለማስማማት የተለያዩ ጥረቶችን ማድረጋቸው እና አገልግሎቱንም በየተራ እንዲያገለግሉ የተወሰነውም ከዚህ ችግር በኃላ ነው። የቤተ - ሚናስ እና የቤተ-ጣዕመ ማኅበራት አመሠራረቱ ከቅዱሳን አባቶቻችን ስም ይዘው ይመስረቱ ትንጂ፣ የኃላ ኃላ ከዘር ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለ ለመገመት አያዳግትም፣ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎችች ለረጅም ዘመናት የቆየ ችግር እንዳለ መረዳት ይቻላል፣ (ወደፊት ስለ ጻድቁ አባት አባ ጣዕመ ክርስቶስ እና ስለ ጻድቁ አባት አባ ሚናስ ዝርዝር ጽሁፎችን እናቀርባለን ተጠባበቁ) በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ ከሦስት ሺህ በላይ የሚሆኑ መነኮሳት ሲኖሩ በሰቋር፣ በዳልሻሕ፣ በአበረንታንት ከሚኖሩ መነኮሳት የቤተ ጣዕመ መነኮሳት ብቻ ዋልድባ ይታረስ ልማት ነው፣ እህል አይግባብሽ፣ ሐጢያት አይሻገርብሽ የተባለችውን ምድር ለኢ-አማናውያን ለመስጠት እና ለማስረከብ መሯሯጥ ምን የሚሉት ይሆን? ነገሩ ከዚህ ሁሉ የበለጠ ችግር እንዳለ ማንም ሊረዳው የሚችለው እውነታ ነው።
በመጨረሻ ከስብሰባው ማጠቃለያ ላይ በስብሰባው የተገኙትን አባቶች ካሳውን ተቀብለው እንዲሄዱ ይልቁንም የቀሩትን አባቶች እንዲያሳምኑ የመንግሥት ተወካዮቹ ቢወተውቱም፣ የመነኮሳቱ ቡድን ግን እኛ ተወካዮች ነን ውሳኔ ልንወስን አንችልም የማኅበራቱ አቋምም ዋልድባ ገዳምን ቅንጣት እንኳን አፈሯ እንዲነካ የማናቸውም መነኮሳት እና መነኮሳይት ፈቃድ እንዳልሆነ እና እነሱም አፈር ጠባቂዎች እንጂ ውሳኔ ሰጪ ወይም ተዳራዳሪ መሆን እንደማይችሉ እቁጩን ገልጸው ለስብሰባ መሪዎቹ ገልጸው ነበር፥ በስብስባው መጨረሻ የመንግሥት ተወካዮቹ በጥር ፬ ለተከታይ ስብሰባ መጥራታቸውን እና በዚህም ጊዜ ውሳኔያቸውን ብቻ እንደሚጠብቁ በማስፈራራት ጭምር ገልጸውላቸው የስብሰባው ፍጻሜ ሆኗል።
አባቶቻችንን በኃይማኖት እና በውሳኔያቸው ያጽናልን
ዝርዝር ዘገባውን እንደደረሰን እንዘግባለን ተከታተሉን   

6 comments:

 1. |Amlake teklehaymanot yifredbachew!!!

  ReplyDelete
 2. Egziabher hoy,Ebakih tadegen.Band bekul yebetekristian mekefafel band bekul betekristian mefres,abatoch mesekayet..egzioo meharene kiristos...hatiyatachin beza eko...ABETU AMLAKACIN HOY TADEGEN...ATITALEN...AMEN

  ReplyDelete
  Replies
  1. WE ARE TOGETHER TO DIFENED OUR IDENTITY AND OUR COUNTRY STARTING THE BIGGING IN OUR FATHERS. SO OUR FATHERE KEEP STRONG IN THE NAME OF GOD. GOD BLESS OUR COUNTRY AND CHURCH FATHERS!!!

   Delete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤