Monday, November 26, 2012

የዋልድባ ኮሜቴ ከአላስካ ሴናተር ማርክ ቢጊች አማካሪ ጋር በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው ተነጋገሩ


ከግራ ወደቀኝ
ቀሲስ ሶሎሞን፣ ቴዎድሮስ፣ ማቲው፣ የአብስራ፣ ሴናተር ማርክ፣ ሳምሶን
ባለፈው ሳምንት ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው የዋሽንግተን ዲሲ ኮሜቴ በዋልድባ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአላስካ ግዛት ሴናተር ማርክ ቢጊች የስራ አስኪያጃቸው ከሆኑት ሚስተር ማት ፔይን በጽፈት ቤታቸው ተቀብው አነጋግረውታል።  ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት ሴናተር ማርክ በዚሁ ቀን እለት ከቀትር በኃላ ከኢትዮጵያው የአሜሪካን አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ ጋር በጽ/ቤታቸው እንደሚነጋገሩ ገልጸው በግንኙነታቸውም ወቅት ሊያነሷቸው ካሰቡት ነጥቦች የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የሰብዓዊ መብጥ ጥበቃ እና ክብካቤ በተጫማሪ የዋልድባ ገዳም እና በገዳሙ ክልል ዙሪያ ለመስራት ብዙ ጥረት እየተደረገ ባለው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ እንደሆነ አስረድተዋል።


የአሜሪካን መንግሥት በዋልድባ ገዳም አካባቢ በገዳማዊያኑ አባቶች እና እናቶች ላይ እየተደረገ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ከፋብሪካው ምሥረታ በኃላ ሊመጣ የሚችለውን የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃን፣ የተለያዩ የፋብሪካው የኬሚካል ውጥቶች ሊያደርሱ የሚችሉትን ብክለት እና የአየር ንብረት መዛባትን፣ ከዚህም በተጨማሪ የሌላ እምነት ተከታዮች ከፋብሪካው ምስረታ ጋር መጥተው ሊያደርሱ የሚችሉትን እና ሊመጣ የሚችለውን ውዝግብ ከወዲሁ ለመነጋገር ነበር ከአምባሳደር ግርማ ጋር የሴናተሩ ውይይት፥ ብሎም ዘለቄታዊ መፍትሄ እና የጸጥታውም ጉዳይ የአሜሪካን መንግሥት የመጀመሪያ ወይም ግንባር ቀደም ጥያቄ እንደሚሆን ነበር የሚጠበቀው።
እንደ ስራ አስኪያጁ አገላለጽም በመቀጠል በዋልድባ ገዳም አካባቢ ስለተጀመረው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ እና በገዳሙ ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው አደጋ ከአቻዎቻቸው የሪፖብሊካን ሴናተሮች ጋር ለመነጋገር እንዳቀዱ እና የአሜሪካንን መንግሥት አቋም በዋልድባ ገዳም አካባቢ በሚሰራው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ያስከተለውን ስጋት እና ወደፊት ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ የኦርቶዶክሳውያኑን ጥያቄ ይበልጥ እንደሚመረምሩት እና አንድ ነጥብ ላይ እንደሚደርሱ ቃል ገብተዋል።
እንደሚታወቀው እስከ ዛሬ ድረስ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጀምሮ አሁን በድርድር ላይ እስካለው የሕንድ የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ጨምሮ ሦስት ኮንስትራክሽን ካምፖኒዎች ሥራውን ለመስራት ኮንትራት ፈርመው መግባታቸው ይታወሳል፥ ነገር ግን የእስካሁኑቹ ሁለት ካምፖኒዎች በእግዚአብሔር ሃይል እና በአባቶቻችን ጸሎት ኮንትራት አፍርሰው ጥለው እንደወጡ ይታወቃል። በመጀመሪያ የሱር ኮንስትራክሽን (የአቶ ስዩም መስፍን ኮንስትራክሽን ካምፖኒ) ሥራውን ለመስራት ኮንትራት ፈርሞ ሥራውን ጀምሮ እንደነበረ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፥ ነገር ግን ሥራውን ከጀመረ ጀምሮ በዋልድባ አካባቢ በርካታ ፈተናዎች አጋጥመውት ነበር ከነዚህም ለአብነት ያህል ለግድብ የተቆፈረው ጉድጓድ መሽቶ እስኪነጋ ወሃ እና አፈር በተከታታይ ቀናት ሲመለሱ እና በዚህም ግራ በመጋባታቸው፣ የኮንስትራክሽን ካምፖኒው ዲዛይን ኢንጂነር በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው፣ ጥቂት የፕሮጀክቱ ሰራተኞች በአውሬ መበላታቸው በመጨረሻም ፈቃደኛ የሆነ ቀጥረው ሊያሰሩት የሚችል ሰራተኛ ከአካባቢው ፈቃደኛ የሆነ ሰው በመጥፋቱ ምክንያት ፕሮጀክቱን በታቀደው ጊዜና የገንዘብ መጠን ጨርሰው ማስረከብ እንደማይችሉ ከወዲሁ በመገንዘባቸው ኮንትራታቸውን አፍርሰው ወጥተዋል።
በመቀጠልም የቻይናው የሥኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን አዲስ ኮንትራት ፈርሞ ስራውን ሰርቶ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደሚያስረክብ ቃል ገብቶ ሥራውን በመስራት የመጀመሪያውን ፌዝ ለመጨረስ ችሎ ነበር፥ እስሩም የመጀመሪያ በዛሬማ ወንዝ ላይ ለሎጂስቲክ ማግቢያ እና መስወጫ የሚሆን ድልድይ እንዲሁም በእስያ ወንዝ አካባቢ ለሸንኮራ ችግኝ ማፍያ የሚሆን መጠነኛ ግድብ ገንብተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞች ለማፍላት ተችሎ እንደነበረ ከስፍራው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ችለናል። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ሥራዎች በአድን ምሽት የቅዱስ ሩፋኤል እለት በመጣ ዝናም ግድቡንም፣ ድልድዩንም፣ ከዛ በተጨማሪ በንብረት እና የሰውን ሕይወት ጨምሮ አደጋ በማድረሱ የተደናገጠው የቻይናው የስኳር ኮርፖሬሽን ሥራውን ለመስራት አቅሙም ጉልበቱም እንደማይኖረው በማወቁ ይመስላል ለኢትዮጵያ መንግሥት ኮንትራቱን አፍርሶ ሥራውን ጥሎ ለመውጣት የተገደደው። በአሁኑ ሰዓት እንደ ሸገር ሬዴዮ ዘገባ ከሆነ የሕንድ ስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን አዲስ ኮንትራት ፈርሞ ሥራውን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ችለናል። እንደ እስካሁኑ ሁለት ኮንስትራክሽን ካምፖኒዎች እግዚአብሔር ተዓምራቱን አሳይቷቸው በሰው ላይ ጉዳት ሳይደርስ የአምላክን ታላቅነት፣ የቅዱሱን የዋልድባን ገዳም ቅድስናን አምነው እና ተመልክተው እንደሚመለሱ በፍጹም እመነታች ነው።
 ዛሬም እንደ ትላንቱ ሰማያዊት እየሩሳሌምን፣ የመንግሥተ ሰማያትን መውረሻ ቅዱሱን ቦታ ለማፍረስ፣ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙትን ቅዱሳን አባቶቻችንን በማንገላታት፣ በማሰር፣ በመደብደብ በእግዚአብሔር መንግሥት ተግዳሮት ያሳዩት እጆች ተቆርጠዋል አሁንም ይቆረጣሉ ትላንት በክፋት እና በትዕቢት ተሞልቶ ሕዝበ እግዚአብሔርን በሰቆቃ ያሰቃየው ፈርዖንን በቀይ ባሕር እንደሳጠማቸው ዛሬም የእኛዎቹ የክፋት እና የጥፋት መልዕክተኞች ተግዳሮታቸውን ካልገቱ ከክፋት ሥራቸው ካልታቀቡ የፈርዖንና የሰራዊቱ ዕጣ ፈንታ እንደሚደርሳቸው ሊያውቁት እና ሊረዱት የሚገባ እውነት መሆን እንዳለበት እንገምታለን።
በመጠረሻ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ከኢትዮጵያዊው በላይ ተቆርቁረው እና ተሰምቷቸው ስለ ቅዱስ ዋልድባ ገዳም ሰዓት ጊዜያቸውን አጥፍተው ስለዚህ ቅዱስ ገዳም ያነጋገሩንን ሚስተር ማቲው ከልብ እያመሰግንን ለስራቸው መሳካት ስለ ቅን ተግባራቸውም እግዚአብሔር አምላክ የልባቸውን ሃሳብ ሁሉ እንዲሞላላቸው እንመኛለን።
ቸር ይግጠመን

2 comments:

  1. ሕገ ቤተክርስቲያን ይከበር!!
    ቀኖና ይከበር!!
    ስለዚህም በህይዎት የሚገኙት ፓትርያርክ ወደመንበራቸው ይመለሱ::

    ReplyDelete
  2. that is great. other stupid political leadersof our country will, most hopefully, follow bloody Melese......

    ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤