Monday, December 31, 2012

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት "ከፖትርያሪክ ምርጫው በፊት እርቀ ሰላም ይቅደም" በሚል መግለጫ አወጣታሕሳሥ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
ቁጥር: ኢኦተቤእተ00182005/
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“በትሕትና ዅሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችኹ በፍቅር ታገሡ፤
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” ኤፌ 4:2-3

ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ
ዋሽንግተን ዲሲ
ለብጹዕ አቡነ ናትናኤል
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እና የአርሲ  ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስ  እና ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል
ቡራኬያችሁ ይድረሰን !
ጉዳዩ :  እርቀ ሰላምን፣ የቤተክርስቲያን አንድነትና የምዕመናንን መንፈሳዊ ደህንነት ከስልጣንና ከሹመት ማስበለጥን ይመለከታል ፦

Friday, December 28, 2012

“ዘይሁብ መርሐ ርቱዓ ለቤተክርስቲያን”

 በጸሎተ ኪዳን ዘሠርክ ላይ እንደተነገረው፥ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ለምትሆን፥ ጸጋን ኃይልን ለምታድል፥ አምነው ለሚቀርቡት ምስጋና አንድም በሃይማኖት ለሚገኝ ክብር ማረፊያ ማሳረፊያ ላደረጋት ለቤተክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። የተገረፈላት፥ሥጋውን የቆረሰላት፥ ደሙን ያፈሰሰላት፦ ነፍሱንም አሣልፎ የሰጠላት እርሱ ነውና። የሐዋ ፳፥፳፰።                                             
          ጥንት ሙሴን እና አሮንን ልጆቹንም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የመረጠ እግዚአብሔር ነው። ዘጸ ፫፥፩-፳፪፣ ፳፰፥፩-፲፬ ይህንን ምርጫ ለመቃወም ወይም በምርጫው ጣልቃ ለመግባት የሞከሩ ዳታን፥ ቆሬንና አቤሮን ፍጻሜያቸው አላማረም።እናንተ የሌዊ ልጆች ስሙኝ፤ የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን የእግዚአብሔርን ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ እንድታገለግሏቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱ ታላችሁን?” ብሎ የመከራቸውን ሙሴን አልሰሙትምና ዘኁ ፲፮፥፩-፶። ከቤተ መንግስቱም ሰዎች እነ ዖዝያን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ገፍተው ቤተ መቅደሱን ደፍረው ነበር።ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፥ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ፥ ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተቀደሱት ለአሮን ልጆች ለካህናቱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ አይገባህም፥ ከእግዚአብሔር ርቀሃልና ከመቅደሱ ውጣ፥ ይህ በአም ላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ክብር አይሆንህም፥አሉት፤ይላል። የንጉሡም መጨረሻ አላማረም። ፪ኛ ዜና ፳፮፥፲፮-፳፫               
                     

Thursday, December 27, 2012

መግለጫ ከጉባኤ ካህናት ወምዕመናን ለቤተክርስቲያን ሰላም


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ግልጽ ደብዳቤ
ታኅሳስ ፲፯ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ዋሽንግተን ዲሲ
ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እና የአርሲ  ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ
ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት - የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
በያላችሁበት
ጉዳዩ: የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ከፍጻሜ ስለማድረስ:
ሀገራችን ኢትዮጵያ በሶስቱ ሕግጋት ማለትም በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትናበሕገ ወንጌል ሀልዎተ እግዚአብሔርን በማመንና ለሥርዓቱ በመገዛት ኖራለች:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንኑና ክርስትናን በቀደምትነት ከተቀበሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት::  ቤተ ክርስቲያኒቱ በሳለፈችው ሶስት ሺህ ዘመናት ጊዜ ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ያለውን ኅብረተሰብ አስተሳስራ የፍቅርና የአንድነት ሰንሰለት ሆና ቆይታለች:: እንደዚሁም ለመላው ዓለም ይልቁንም ለአፍሪካውያን ሁሉ መኩሪያ የሆኑትን ኮኖዊ : መንፈሳዊና ማበራዊ ሀብታትን አበርክታለች::  እያበረከተችም ትገኛለች:: 

Tuesday, December 25, 2012

የዋልድባ አካባቢ ዛሬም እየታረሰ ነው
(አንድ አድርገን ታህሳስ 16 2004 ዓ.ም)፡- የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ የዋልድባን ጉዳይ ወደ ኋላ እንዲል አድርጎታል ፤ ምዕመኑ “እርቀ ሰላሙ ካልቀደመ ፓትርያርክ ምርጫው መደረግ የለበትም” ሲል አባቶች ደግሞ የአራት ቁጥርና የስድስት ቁጥር ነገር አስጨንቋቸዋል ፡፡  ከቀናት በፊት ከስኳር ኮርፖሬሽን ያገኝንው የፎቶ መረጃ ቦታው ላይ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥሩ አመላካች ሆኖ አግኝተነዋል ፤ ይህ የምታዩት ፎቶ ከስሩ ይህ ጽሁፍ ሰፍሮበት ይገኛል  The Gorge of Zarema River where the MayDay Dam will be in place at Wolkayite ይላል ፡፡ ይህ ፎቶ በአካባቢው ላይ በገዳሙ የሚገኙ አባቶች ከሚናገሩት በተጨማሪ በቦታው ላይ የሚሰራው ስራ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡  በርካታ ዶዘሮች መሬቱን ሲያርሱ  በርካታ ገልባጭ መኪኖች ደግሞ እየተርመሰመሱ የሚጫንላቸውን አፈር ወደ ሌላ ቦታ በማዞር ላይ እንዳሉ ፎቶ ያሳያል፡፡ እስከ አሁን ድረስ በአካባቢው የሚሰራውን ስራ በግለሰብ ደረጃ በግልጽ በቪዲዮም ሆነ በፎቶ ማስቀረት በጣም የተከለከለ መሆኑ ይታወቃል ፤ ሰዎች ወደ ቦታው ለጸሎትም ሆነ ክብረ በአል ለማክበር ሲሄዱ ካሜራ እና ቪዲዮ ይዘው እንዲዘልቁ አይፈቀድላቸውም ፡፡ መንግሥት ግን ቦታው ከማረስ ወደ ኋላአላለም ፤ ዋልድባ አካባቢው እንደምትመለከቱት መልክአምድሩ እየተቀየረ ይገኛል ፤ መንግስት እየሰራ ባለው ስራ ገዳማውያን የአመት ቀለባቸውን ማግኝት እየተሳናቸው ነው፡፡ እንደ ጾሙና ጸሎቱ ሁሉ ሥራን የጽድቅመሠረት አድርገው በማኅበር የሚኖሩት ከሦስት መቶ ኀምሳ በላይ ማኅበረ ደናግሉ፤ በአሁኑ ሰዓት በሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት እና ተያያዥነት ባለቸው ጉዳዮች  ከፍተኛ ሙቀትናበሌሎችም የአካባቢ ለውጦች ሳቢያ ራሳቸውን የሚረዱባቸው የዳጉሳና የማሽላ ሰብሎቻቸው ፍሬሊሰጧቸው ስላልቻሉ አስቸኳይ የምግብ እና የአልባሳት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ማስታወቃቸው ይታወቃል፡፡ 

Friday, December 14, 2012

ስቃዩ እና እንግልቱ በዋልድባ እንደቀጠለ እንደሆነ ይነገራል


በዛሬው ታሕሳሥ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በESAT Radio ዘገባ መሰረት በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግሥት የተለያየ ሙከራዎችን እያደረገ እንደሚገኝ እና በገዳማውያኑ ላይ ስቃዩን እንደቀጠለ ይነገራል። ባለው ወር ላይ የገዳሙን አባቶች ጥቂት የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰብስበው እንዳነጋገሯቸው እና ለጥር ፬ ቀን ቀጠሮ ሰጥተዋቸው እንደተበተነ ይታወሳል። በመጪው ጥር ፬ ቀን ምን ሊመጣ እንደሚችል በገዳማውያኑ ላይ ሊደርስባቸው የሚችሉትን፣ እንደ መንግሥት ባለሥልጣኖች አባባል በጥር ፬ ቀን በሚደረገው ስብሰባ ላይ የመንግሥት ተወካዮች ለገዳሙ አባቶች "ለቦታው ካሳ ተቀበሉ አለበለዚያ ሌላ ነገር ይመጣል" በማለት ገዳማውያኑን ለማስፈራራት ቢሞክሩም፥ ገዳማውያኑም "ሞትም ቢመጣ እኛ የአባቶቻችንን ርስት አሳልፈን አንሰጥም፣ እኛን ገላችሁ ሥራችሁን መስራት ትችላላችሁ" በሚል ሁኔውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት የገዳሙን ይዞታ የቋርፍ (የገዳማውያኑ ምግብ) የሚመረትበትን ቦታ ወስዶ ስላረሰው ገዳማውያኑ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል፥ ከዚህ በተጨማሪ የገዳማውያኑ የሳር ቤት ክዳን ባለው ቤት ላይ ተባይ በማፍራቱ ገዳማውያኑን ለተጨማሪ አደጋ ተዳርገዋል። ከዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት የአንድነት ገዳም ሦስት የመነኮሳይት ቡድን ወደ አዲስ አበባ ተልኮ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለመጠየቅ መጥተው እንደነበር እና ነገር ግን ከቤተክህነቱም ምንም ዓይነት ድጋፍ ሳይደረግላቸው መነኮሳይቱ ወደ ባዕታቸው ለመመለስ ችለዋል። 
ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው ኮሚቴ በወቅቱ ለነበረው ችግር በጊዚያዊነት ለገዳማውያኑ መጠነኛ የገንዘብ እርዳታ እና የመነኮሳይቱን ቡድን ወደ ባዕታቸው የሚመለሱበትንም የትራንስፖርት ሁኔታ አመቻችቶ ወደ ባዕታቸው ለመመለስ ችለዋል።
እግዚአብሔር አምላክ መናንያኑን በገዳም ያጸና፥ እኛንም በሃይማኖት ያጽናን አሜን

ራዲዮን ፕሮግራሙን ለማዳመጥ ይጫኑ 

በቀጥታ ከESAT ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ 

Monday, December 10, 2012

ዕርቀ ሰላሙ በሚቀጥለው ጥር ወር በሎስ አንጀለስ በድጋሚ ይካሄዳል


(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 1/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 10/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ከኅዳር 26 እስከ 30 (ዲሴምበር 5-9/2012) በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት የተደረገው ሦስተኛ ዙር የዕርቅ ድርድር ትናንት እሑድ መግለጫ በማውጣት እና ለሌላ ጉባዔ ቀነ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቋል። በመግባባት፣ በመከባበር እና በመደማመጥ ተደርጓል በተባለው በዚህ በአባቶች ውይይት ከቀደሙት ሁለት ጉባዔያት በተሻለ “ተስፋ ሰጪ” የአንድነት ምልክቶች የታዩበት መሆኑን ብዙዎች እየመሰከሩ ነው። ሙሉ መግለጫው በዳላስ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በምዕመናን ፊት በተነበበበት ወቅት ከሁለቱ ወገን የመጡ ልዑካን ኮፒውን በእጃቸው ይዘው ታይቷል።
በዕለቱ የተነበበው መግለጫ በዋነኝነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ ሰጥቶ ያለፈ ሲሆን እኛም እንደሚከተለው ጨምቀን እኛም አቅርበነዋል።

Thursday, December 6, 2012

ሰለ ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬ ባያመልጠንስ?


በጀርመን ሃገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባት ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ በአሁን ሰዓት ስለ አለው የቤተክርስቲያን ሰላም ጉዳይ ካሳሰባቸው በርካታ የኢ/ኦ/ተ/ቤ አማኞች መካከል አንደኛው እንደመሆናቸው መጠን እንደ ቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ፣ እንደቤተክርስቲያኒቱ ልጅነት ይህ ጊዜ ሊያመልጠን አይገባም እግዚአብሔር ባወቀው ያመጣልን እድል ለቤተክርስቲያን ሰላም እና ለምዕመናቷ አንድነት ሲባል ሁለቱም ተደራዳሪዎች እና መላው የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ስለመጪው ትውልድ በማሰብ እድሉን እንጠቀምበት በማለት አበክረው በጽሑፋቸው ገልጸውታል እኛም ጽሁፋቸውን እንዳለ ለአንባቢያን ለማቅረብ ወደድን መልካም ንባብ እንመኛለን። 
ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ቅድስት እና ርትዕይት ሃይማኖታችንን በጸጋና ረደኤት ይጠብቅልን 
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

Wednesday, December 5, 2012

“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

አባቶች በጋራ ከጉባኤው በፊት በተገናኙበት ወቅት

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ካህናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ ምዕመናን እና ምዕመናት በጉጉት ሲጠብቁት የነበሩት የቅድስት ቤተክርስቲያን አባቶች የእርቀ ሰላም ጉባኤ ዛሬ ረፋዱ ላይ በዳላስ ቴክሳስ በሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጸሎት ተጀምሮ በመቀጠል በአካባቢው በሚገኘው ሆቴል የድርድሩ እና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምን ለማምጣት በአባቶቻችን እና በምዕመናን ጸሎት እና ልመና የተሳካ እንደሚሆን የሁሉም ወገኖች እምነት ነው።


Saturday, December 1, 2012

ማስታወቂያ

መንፈሳዊ ጉባኤ በዲሲ እና ቨርጂኒያ


ታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ
December  15 & 16, 2012

ትላንት ዋልድባ ታረሰ፣ ዛሬ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው፣ ነገስ . . . በተመሳሳይ ርዕሶችና በእርቀ ሰላሙ ዙሪያ ውይይቶች ተዘጋጅተዋል እንዳያመልጦት!

ዓለምዓቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አንድነት፣ ቀድሞ ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው ኮሜቴ ለአራተኛ ጊዜ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ባለሙያዎችን ጋብዞ ለመነጋገር የሁለት ቀናት ተከታታይ ጉባኤ አዘጋጅቷል። የእርሶ ተሳትፎ እየት ድረስ ነው? ለቤተክርስቲያንዎ ሊያበረክቱ የሚችሉትን ለመጠቆም ተዘጋጅተናል፣ ኑ! እንምከር ቤተክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ከነሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍ አብረን እንስራ!
እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን በረደኤት ይጠብቅልን አሜን

 ቅዳሜ Dec. 15, 2012                   እሑድ DEC. 16, 2012
 St. Andrew UMC                        ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅ/ማርያም ቤ/ክርስቲያን
845 N. Haward Street                                            1360 Buchanan Street, NW.
Alexandria, VA 22304                                                Washington, DC 20018
2:00 – 6:30 pm.                                                                4:00 – 8:00 pm

ለተጨማሪ መረጃዎች በስልክ ቁጥር  571-299-0975 or  571-224-2869.
savewaldba@gmail.com | www.savewaldba.blogspot.com | PO box 56145 Washington, DC 20040

ለቤተክርስቲያን እርቀ ሰላም የበኩልዎን ያበርክቱ

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከያዮች አንድነት (ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው ኮሚቴ) እርቀ ሰላሙን ለመራዳት ከምዕመናን እና ከካህናት ተውጣጥተው የተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከቤተክርስቲያን አንድነት በሚደረገው አለም አቀፍ ርብርብ ላይ ሁሉም ወገን የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግ እና ከዚህ ጋር የተያያዘውን petition በየቤተክርስቲያኑ በማስፈረም ስካን በማድረግ በቀጥታ savewaldba@gmail.com በመላክ ከዓለም ዙሪያ የተሰበሰቡትን እነዚህን የቤተክርስቲያን አንድነት ለማምጣት የሚደረገውን ትግል ለመተባበር በየአካባቢያችን ቤተክርስቲያን እንዲሁም የጉባኤ ቦታዎች በመውሰድ ምዕመናንን በማስፈረም ትብብራችሁን እንድታደርጉ እና የበኩላችንን እንድንወጣ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን መሄድ የማንችል በሚከተለው አድራሻ petitionኑን እንዲፈርሙልን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን፡
ፒቲሽኑን ለመፈረም እዚህ ይጫኑ 

የተጻፉትን ፒቲሽን ፕሪንት በማድረግ በየአጥቢያ በመውሰድ ለሚተባበሩ በሙሉ እዚህ ይጫኑ
ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት የበኩልዎን ያበርክቱ!