በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን
Tuesday, December 31, 2013
መለከት ሲነፋ፣ ነጋሪትም ሲጎሰም ከሰማይ ተሰማ።
ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔርን አጥብቀው የሚሹት የአባቶቻችን ጸሎት፣ ምሕላ፣ ዝማሬ፣ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዚቅ፥ ማህሌት፣ ወረብ፣ ቅኔ፣ ቅዳሴ የት ደረሰ? ብርሃን በጨለማ ተከብባ ትቀራለችን? እውነት በኃሰት ተዳፍና ትቀራለችን? እነሆ የአባቶቻችን ጸሎት መሬት ላይ እንደሚቀር ትቢያ እንዳልሆነ ከዚህ በታች ይመልከቱና ይረዱ።
ከ ፪፲፻፩ ዓ.ም. ጀምሮ ከስማይ መለከት ሲነፋ፣ ነጋሪትም ሲጎሰም ከአፍሪካ በቀር በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በተለይ ከ፪፲፻፭ ዓ.ም. ወዲህ መለከቱና የነጋሪቱ ድምጽ በድግግሞሽ በበርካታ ስፍራዎች በመሰማት ላይ ይገኛል። በመቶ በሚቆጠሩ ሥፍራወች በሚሰማው በዚህ ደምጽ ብዙ የአውሮፓና የአሜሪካ ሰዎች ሲሸበሩ ይታያሉ። የሳይንስ ሰዎች ደግሞ ሳይንሳዊ ትንታኔ ለመስጠት እየተንገዳገዱ ነው።
ከ ፪፲፻፩ ዓ.ም. ጀምሮ ከስማይ መለከት ሲነፋ፣ ነጋሪትም ሲጎሰም ከአፍሪካ በቀር በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በተለይ ከ፪፲፻፭ ዓ.ም. ወዲህ መለከቱና የነጋሪቱ ድምጽ በድግግሞሽ በበርካታ ስፍራዎች በመሰማት ላይ ይገኛል። በመቶ በሚቆጠሩ ሥፍራወች በሚሰማው በዚህ ደምጽ ብዙ የአውሮፓና የአሜሪካ ሰዎች ሲሸበሩ ይታያሉ። የሳይንስ ሰዎች ደግሞ ሳይንሳዊ ትንታኔ ለመስጠት እየተንገዳገዱ ነው።
Sunday, December 29, 2013
Trumpets Heard Worldwide
Do you think the prayers of our forefathers faded into oblivion and that it was spent in vain? See below and think again!
Beginning from 2008 European Calendar, sounds of the trumpet along side periodic drum beats are being heard all around the world with the exception ofAfrica . The frequency of the sounds has been increasing steadily
peaking in 2012. The sound has an approaching and a receding and then an
approaching and a receding pattern. In some cases it ends with a bang. This
trumpet sound from the sky is heard from hundreds of places and many of those
who witnessed the events have recorded the sound.
Beginning from 2008 European Calendar, sounds of the trumpet along side periodic drum beats are being heard all around the world with the exception of
Wednesday, December 25, 2013
Tuesday, December 17, 2013
Friday, December 13, 2013
የሰይጣን ውጊያው እንደቀጠለ ነው!
ዋልድባ |
የሰይጣን ውጊያው እንደቀጠለ ነው!
- · ዘራቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩ ካሕናት ተብዪውች ዋልድባን የመታደግ ጥረትን ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው
- · በዋልድባ የቤተ ጣዕመ ክርስቶስ አባቶች ልማት አንቃወምም፥ ገዳሙንም አይነካም በማለት የአዞ እንባ እያነቡ ነው
- · አፍቃሪ መንግሥት (ካድሬዎች) ዋልድባን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት ለመቃወም በየመንደሩ አሉባልታ እየነዙ ይገኛሉ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪካዊውን እና
ጥንታዊውን የዋልድባ ገዳም አፍርሶ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደገዳማዊ ገዳማውያን የሚባሉ፣ ነገር ግን ዘራቸውን
እንደጣዖት የሚያመልኩ የበግ ለምድ ለብሰው በጠቦቶች መካከል የሚዘዋወሩ ተኩላዎች፥ ይህንን ታሪካዊ እና ጥንታዊ ገዳም ለመታደግ
የሚንቀሳቀሰውን ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በመባል
የሚታወቀውን ተቋም የተለያየ አሉባልታ በመንዛት ጥረቱን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል።
ይህ ተቋም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የዋልባ ገዳም
አባቶች ላይ የመንግሥት ካድሬዎች የሚያደርሱባቸውን እንግልት፣ በደል፣ እና ስደት አቅም በፈቀደ ለመርዳት ይህ ተቋም ብዙ ጥረቶችን
ሲያደርግ ቆይቷል። ከነዚህም ጥረቶች መካከል ለመጥቀስ ያህል
Monday, December 9, 2013
በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ
የቆራሪት ከተማ
(አንድ አድርገን ታህሳስ 01 2006 ዓ.ም)፡- በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡ ለተነሱ አርሶ አደሮቹ 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል፡፡ ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል ፡፡ ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ፤ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ ፤ የመኖሪያ ቤት ፤ ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት 127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል ፤ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት ከ13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
Thursday, December 5, 2013
ተወካዮች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን አነጋገሩ

ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለተወካዮች አባታዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ተወካዮቹ ቤተክርስቲያናችን በተመለከተ ለብፁዕነታቸው
ያቀረቡላቸውን ማሳሰቢያወች ብፁዕነታቸው ተቀብለው ጉዳዮቹን ከብፁአን የሲኖዶስ አባላት ጋር እንደሚመለከቷቸው ገልፀው ለተወካዮቹ
አባታዊ ቡራኬ አድርገውላቸዋል።
ዜና - ዋልድባ አብረንታንት
ዋልድባ
አብረንታንት ዉስጥ በሀይማኖት ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ተነስቶ አብዛኛዉ መነኮሳት እየተሰደዱ ነዉ። ባለፈዉ ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ዋልድባ በነበረ “መነኩሴ” የተጻፈ የኑፋቄ
መጽሐፉ ገብያ
ላይ እንዳይዉል - እንዳይሸጥ ተብሎ ቢታገድም ገዳሙ ዉስጥ ብጥብጡ እንደቀጠለ ነዉ:: በአሁኑ ሰአት
አብዛኛዉ መነኮሳት ወደ በርሀ እየፈለሱ ነዉ። በተለይ ለብዙ ዘመናት በገዳሙ የቆዩ አባቶች እየለቀቁ ነዉ። ያሉተም የቤተ ጣእማን መስቀል በግድ ተሳለሙ እየተባሉ ነዉ። የማይጸብሪ አስተዳደር በሀይማኖት ጣልቃ እየገባ ነዉ። ህዳር ፳፯
ቀን ፪፲፻፮ ዓ.ም. የማየጸብሪ አስተዳደር ማህበረ መነኮሳቱን ከገዳሙ በመሄድ ይሰበስባል የቤተ ጣዕማን መስቀል አልሳለምም ብሎ የሚበጠብጥ መነኩሴ ካለ ገዳመን መልቀቅ አለበት ብሎ መመሪያ ሰጥቷል።
ሌላዉ
በወልቃት ስኳር ፕሮጀክት (ዋልድባ) ምክንያት በሚቀጥለዉ አመት ቤቶችን ስለምናፈርስ በቅርብ ቀን ግምት እንገምታለን ብለዉ ባለስልጣኖቹ ያለፈው እሁድ እለት ለህዝቡ መህርገጽ ቅደስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ቁመዉ ተናግረዋል
Friday, November 22, 2013
ዜና ፥ ዋልድባና አበሳው
- ኅዳር ፰ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም. የአርባእቱ እንስሳን ባዕለ ክብር ለማክበር ወደ
ዋልድባ በመሄድ ላይ የነበሩትን ወጣቶች አሳደደ። ወጣቶቹም
ሸሽተው ሁመራ ገቡ።
- ኢሕአዴግ ኅዳር ፲፮ ቀን ፪፲፻፮ ዓ.ም. የራሱን መነኮሳትና የራሱን ሰዎች
ከትግራይና ከጎነደር በመጥራት ጎንደር ላይ ስብሰባ ለማድረግ እየተሰናዳ ለመሆኑ መረጃ ደርሶናል። ስብሰባው ሁለት ዓላማ አለው።
o
፩ኛ - “መነኮሳቱ” - “ዋልድባ
አልታረሰም፣ ባለፈው ታረሰ ብለን ስለተናገርን አጥፍተናል። ይቅርታ እንጠይቃለን; የልማቱ ተባባሪዎች ነን” የሚል መግለጫ አውጡ
በማለት በዜና አውታሮች ለማሰራጨት ሲሆን፥
o
፪ኛው ዓላማ ደግሞ “ተሰብሳቢዎቹ በፈቃዳቸው ራስ ዳሽንና አካባቢው በትግራይ ክልል
ሥር እንዲሆን ተስማሙ” የሚል መግለጫ ለማውጣት እንደሆነ ከደረሱን ምንጮች ለመረዳት ችለናል።
አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ የኢሕአዴግ አገልጋይ የሆኑ “መነኮሳት” ዓላማውን ለማሳካት መነኮሳትን ለማባበል በመንኮሳት
አካባቢ እያንዣበቡ መሆኑም ታውቋል።
ዝርዝሩን በቅርቡ እናቀርባለን።
ይቆየን።
Monday, November 18, 2013
ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።
ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።
ከኃይለሚካኤል፥
ኅዳር ፱ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም.
ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና
ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ
አስተዳደር የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።[1]
ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።[2]
ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ። ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር።
እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር
ግጥም መፎካከር የዐረቦች ባህል ነበር።[3]
እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም
የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።
Tuesday, November 12, 2013
ዜግነት ዋጋ ሲያጣ
Friday, November 8, 2013
(PDF):- ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ
እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በአረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት
ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል?
ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አንሶ ይሆን?ትናንት ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችባቸው
5 ዓመታት ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አድርሳለች። ከነዚህ መካከል
በግራዚያኒ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የደረሰው የየካቲት 12 ጭፍጨፋ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በግፍ
የተጨፈጨፉት የየካቲት 12 ሰማዕታት በሚዘከሩባቸው ቀናት አንድም ፈረንጅ በአዲስ አበባ መንገድ ዝር አይልም ነበር አሉ። ኢትዮጵያውያን
በቁጭት ስለሚወጡ። እንኳን ጣሊያን እና የጣሊያን ዝርያ ያለው ቀርቶ ሌላ ፈረንጅም ቢሆን ይፈራ ነበር። ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው
ጥቃት ይኼን ያህል ቁጭት ነበራቸው።
Wednesday, November 6, 2013
ዘመቻ ፀረ-ተሃድሶ በደብረ ብርሃን
- ‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ምዕመንም ሆነ ካህን በሀገረ ስብከቴ እንዲኖር አልፈቅድም››ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም
- ‹‹አምስት ዓመት ከጣልያን ጋር የተዋጋነው ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለሃይማኖታችን ጭምር ነው›› አባት አርበኛ
- ‹‹የዘርያቆብ ከተማ ኑፋቄ አይዘራባትም›› የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ካህናት
ኑፋቄ የተገኝበት መጽሐፍ ታገደ
ዳዊት ደስታ
- መጽሐፉ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ መነኩሴ የጻፉት ነው፡፡
(አንድ አድርገን ጥቅምት 26 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባደረገው ስብሰባ ‹‹ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት›› በመል ርዕስ በዋልድባ ገዳም በሚኖሩት በመ/ር አባ ገ/እግዚአብሔር አብርሃ የተዘጋጀውን ቅጽ አንድና ሁለት መጽሀፍ በሊቃውንት ጉባኤ አስመርምሮ የኑፋቄ ትምህርት ያለበት መሆኑን ስለተረጋገጠ እንዳይራጭና እንዳይሸጥ አገደ፡፡
Saturday, October 26, 2013
እዩና እመኑ፥ መልከ ጸዴቅ ገዳም
source: sodere.com
Thursday, October 17, 2013
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!
October 16, 2013
ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ሲከራከሩና በአንዳንድ ኹኔታዎችም ኤክስፐርቶቹን ሲገሥጹ ውለዋል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ÷ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ÷ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታና ከቀረበው ጽሑፍ እየተነሡ በመረጃ፣ በጥያቄና በትችት ስለ መቻቻል ጽሑፍ ያቀረቡ የሚኒስቴሩን ባለሥልጣናት ፈተና ላይ ጥለዋቸው አምሽተዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳቱ ምስክርነት‹‹የባዕድ እምነት አራማጆች በቤተ ክርስቲያንና በካህናት ላይ ልዩ ልዩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉና ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ታላቅ ድፍረት እንደሚፈጽሙ›› ቀደም ሲል ለአጠቃላይ ጉባኤው የቀረቡ ሪፖርቶችን በገሃድ የሚያጠናክሩና የሚያጸኑ ናቸው፡፡
የሚኒስቴሩ አማካሪዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ቅሬታዎቹ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተደግፈው በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤበኩል ቢቀርቡላቸው መፍትሔ እንደሚሰጧቸው፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተገለጹት በላይ ያልተነገሩ ቅሬታዎች ስለመኖራቸው በየወረዳው ተዘዋውረው መረጃዎችን አሰባስበው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ‹‹ሕግ የተያዙት ጉዳዮች በሕግ እንደተያዙ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ›› ለዚህም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንካሬ አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል፡፡
የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጥያቄ፣ አስተያየትና ትችት በከፍተኛ ጥሞና የተከታተለው የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊ የሞቀ ድጋፉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የውይይት አጀንዳ አጋጣሚውን እንደ ምቹ ኹኔታ ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉትና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የሚመስሉት አቡነ ሳዊሮስ ውይይቱን ሳይጨርሱ አቋርጠው ሲወጡ ታይተዋል፡፡
Sunday, October 13, 2013
Sunday, October 6, 2013
ዘመነ ጽጌ
+++ የዳሰሳ ጥናት +++
የሐመርና ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ ሕትመቶችን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሚዘጋጀው አውደ ጥናት መረጃ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ መጠይቅ ቅፅ ::ዘመነ ጽጌ |
|
|
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ክረምቱ አልፎ በጋ ሲተካ ተራውንም ለዘመነ መፀው ሲያስረክብ የመጀመሪያው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ
ይባላል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠራር በዘመነ ጽጌ ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ባለው
ጊዜ ውስጥ የሚደርሰው ስብሐተ እግዚአብሔር የሚቆመው ማኅሌቱ ደግሞ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይጠራል፡፡ በአባ ጽጌ ድንግል
የተደረሰው ማኅሌተ ጸጌ እየተባለ የሚጠራው መልክ መሰል ድርሰትም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ እየተቃኘ
አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜም ይኸው ዘመነ ጽጌ ነው፡፡ ባሉት ሰንበታትና እንዲሁ ወርኀ በማለት ይደርሳል፡፡
ማኅሌተ ጽጌ የተባለው የድርሰት ክፍል እመቤታችንን በጽጌ ማለት
በአበባ ልጇን መድኀኔዓለምን በፍሬ እንደገናም እሷንም ልጇንም በአበባና በፍሬ እየመሰለ ልብን በሚመስጥ ምሥጢራት
ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገር ድርሰት ሲሆን፤ በውስጡ ስለ ሥላሴ፣ ስለ
ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትና ስለ ቅዱሳን ጻድቃን
የሚናገርና ገድላቸውን ትሩፋታቸውን መከራቸውን ከብሉይ ከሐዲስ አስማምቶ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡
Friday, October 4, 2013
ግልጽ ደብዳቤ ለብፁዓን ወቅዱሳን አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ማትያስ፤
ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ/ም
ግልጽ ደብዳቤ
ለብፁዓን ወቅዱሳን አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ማትያስ፤
ግልባጭ፤
ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ፤ ለእግዚአብሔር፤
ለእመቤታችን፤ ለቅድስት ማርያም፤
ለሊቃነ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤልና ለቅዱስ ገብርኤል፤
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና
ምእመናን።
አቤቱታ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ለተጋረጡት ከባድ ችግሮች መፍትሔ አግኙልን!
“ዕርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ እነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ. ም5/9
ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች ሆይ!
በመጀመሪያ፤ ዝቅ ብዬ እጅ በመንሳት፤ መንፈሳዊ ሰላምታዬን
በከፍተኛ አክብሮትና ትሕትና አቀርባለሁ።
በመቀጠልም፤ ምንም እንኳ ኢምንት፤ ተራ ምእመን
ብሆንም፤ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው ለሚገኙት ከባድ ችግሮች መፍትሔ ሊገኝ የሚችለው፤
በፍጡራን ደረጃ፤ ከሁሉም በላይ፤ ሁለታችሁ ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች፤ በአምላክ በተጣለባችሁ ግዴታና ኃላፊነት፤ ተግባራችሁን ከናንተ
በሚጠበቅ ብርታት ስትወጡ መሆኑን ስለማምን ይህንን ግልጽ ደብዳቤ፤ ለሚመለከታቸው ሁሉ ግልባጭ በማድረግ በታላቅ ትሕትና አቅርቤላችኋለሁ።
መልሳችሁን በአክብሮት፤ በጥሞናና በጸሎት እጠብቃለሁ።
"ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም" ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
"ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም" ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዕንቁ መጽሔት መስከረም 2006 ዓ.ም እትም ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር ‹‹አንድ አድርገን›› ፍሬውን ከላይ ዝርዝሩን ከታች አድርጋ እንዲህ አቅባላችኋለች
· ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ አመኔታ ያለው የዕምነት ተቋም የለም፤ ጠንካራ እምነቶች ግን አሉ፡፡
· ማኅበረ ቅዱሳን እስከ አሁን ድረስ አክራሪ ሆኖ ያመጣው ነውጥ፣ ያስነሳው ነገር፣ የደበደበው፣ የገደለው ሰው፣ ያቃጠለው ቤተ እምነት የለም፡፡
· ማኅበረ ቅዱሳንን አክራሪ ለማሰኘት የሚያበቃ ምንም፣ አንድም መከራከሪያ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ ከሳቸውም በፊት የነበሩት ሌሎች ሰዎች እንደ እርሳቸው ብለዋል፡፡
· ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች ምንጫቸው መታየት አለበት፡፡ ‹‹ቂጣም ከኾነ ይጠፋል፤ ሽልም ከኾነ ይገፋል›› እንደሚባለው በተያዘው ሐቅ መቀጠል ነው
· ማኅበሩ አንድ የሚጎድለው ነገር ቢኖር ማስረዳት ነው፡፡ መልስ መስጠት እንጂ ቀድሞ የማስረዳት ነገር ውስጥ ብርቱ አይደለም፡፡
· ‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን ተጠብቃ፣ ሥርዐቷን ይዛ ወደሚቀጥለው ትውልድና ዘመን መሻገር አለባት›› የሚሉትን አካላት ነው አሁን ‹‹አክራሪ›› ማለትና ዝም ማሰኘት ነው የሚፈለገው
· በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አክራሪነትን ሊያበቅል የሚችል መሬት አይገኝም፡፡
Saturday, September 28, 2013
ነገረ ወልድ
ነገረ፡
ወልድ።
በቅዱስ
ኤፍሬም። ፫፻፶ ዓ. ም.
|
ቸሩ እግዚአብሔር
“አብራም” ብሎ ጠራው።
ከዘመዶችህ ተለይና
እኔ ወደማሳይህ ምድር
ተሰደድ አለው።
አብራም ከካራን ወጣ
በ፸፭ አመቱ ልክ
እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደከነዓን ወረደ።
ከዘመዶቹም ካገሩም ይልቅ
ልቡ እግዚአብሔርን
ወደደ።
ከካራን ሲወጣ
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
ሊጠብቅ
“ሀ” ብሎ ጀመረ።
እግዚአብሔርም አየ፡
ትእዛዝ ጨመረ።
አረጋዊው አብራም
በብርቱ ፈተናወች ታጠረ።
Wednesday, September 18, 2013
በምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት የተቃጠለው የዳገት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን
በዚሁ የምሥራቅ ጎጃም ዞን በርካቶች የመቃጠል አደጋ ደርሶባቸዋል ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው
፩ኛ/ የአንጋታ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓም ተቃጥሏል
፪ኛ/ የዳገት እየሱስ ሚያዚያ 11 ቀን 2005 ዓም
፫ኛ/ ደረባን ሕዳር 8 ቀን 2005 ዓም
፬ኛ/ የደማሞ ማርያም ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓም
፭ኛ/ የሰንደባ ሚካኤል ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓም
፮ኛ/ ጥንታዊው የአንበር ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ኅዳር 13 ቀን 2005 ዓም የቃጠሎ አደጋ ሲደርስባቸው ሃላፊነት የወሰደ ወይንም
ችግሩ ደግሞ እንዳይከሰት ለማድረግ የሞከረ የመንግሥት አካላትም የሉም። የአካባቢው ነዋሪም ቀን ቀን ሦስት ሰው ማታ ማታ አራት ሰው በመሆን ጥበቃ ያደርጋሉ ነገር ግን ይሄ በቂ ሊሆን አልቻለም።
ሰላም ባለበት፣ የሃገር ልዕልና ባለበት የዜጎች መብት በሚከበርት ሃገር እንዴት የእምነት ቦታዎች በተለያየ ጊዜ እንዲህ ቃጠሎ ሊደርስባቸው ይችላል ይህንን የክልልሉ መንግሥትም ጉዳዩን ከምንም አለመቁጠሩ፤ ነገሮች የበለጠ እንዲወሳሰቡ ሆነዋል
በሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ አድባራት፣ ገዳማት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶች ባለፉት 20 ዓመታት ሲቃጠሉ፣ ሲወድሙ ተመልክተናል ነገር ግን ቤተክህነቱ ምንም ሊያደርግ አልቻለም ወይንም የእምነቱ ተከታዮች ምንም ማድረግ አልቻሉም ወይንም አይመለከተንም ብለው ተቀምጠዋል። በጣም በእጅጉ የሚያስፈራው በቀጣይነት ክርስቲያኖች በየቦታቸው እየታደኒ አደጋ እንዳይደርስባቸው ስጋት አለን።
እምነታችንን እና ሃይማኖታችንን ነቅተን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን
እግዚአብሔር ይሁነን
Tuesday, September 17, 2013
በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
- መነኰሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው
- አስተዳደሩ ለመነኰሳቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም
- ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ብትውሉ አታድሩም!›› /ጥቃት ፈጻሚዎቹ/
በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል – ‹‹ቢፈነዳም እርሱ ከልሎናልና ጉዳት አላደረሰብንም፡፡››
Sunday, September 8, 2013
የአክራሪነት ውንጀላ የተሰነዘረበት ማኅበረ ቅዱሳን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ሪፖርት/ክሥ ማቅረቡ ተጠቆመ
- አክራሪነት ውንጀላው በ‹‹አገር አቀፍ የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ወቅት ማኅበሩንና አገልግሎቱን ከተቀበረ ፈንጂ ጋራ ያመሳሰለውና በአቶ ስብሓት ነጋ አጽንዖት የተሰጠው የአባ ዮናስ ጥቆማ ነው፤ ጥቆማው የተሰማው ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሑፍ ተከትሎ አቶ በረከት ስምዖን በመሩት የውይይት መድረክ ነው፡፡
- ከሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ተወክለው የመጡት አባ ዮናስ÷ ማኅበሩን በስም ለይተው ባይጠቅሱም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ለቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚሰጠው ሥልጠና ትውልዱን ‹አክራሪነትን ያደርጋል› በማለት፣ በእነርሱም በኩል የመንግሥትንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ይካሄዳል ያሉት እንቅስቃሴ ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረ ትልቁ የአክራሪነት ፈንጂ›› እንደኾነ ጠቅሰው ማኅበሩን ቅ/ሲኖዶስ አጽድቆ በሰጠው የአገልግሎት ድርሻው በመጠቆም በከፍተኛ ደረጃ ወንጅለዋል፡፡
- ለአባ ዮናስ በቂምና ጥላቻ የተሞላ ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ያላገኙ የውይይቱ ተሳታፊ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከስብሰባው በኋላ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ ሓላፊዎች በተለይ ከሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ጋራ ከፍተኛ ሙግት ገጥመው ታይተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና የሰጠችውና በመዋቅሯ የምትቆጣጠረው ማኅበርና አገልግሎቱ ከአክራሪነት ጋራ መያያዙና ትርጉሙ በቀላሉ እንደማይታይ ያመለከቱት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ሚኒስቴሩ ማኅበሩን ጠርቶ ለማነጋገርና ለመመካከር ሞክሮ እንደኾነ ጠይቀዋል፤ ጉዳዩንም መንበረ ፓትርያርኩ በጥብቅ ይዞ እንደሚነጋገርበት አሳስበዋቸዋል ተብሏል፡፡
ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም: በዋልድባ ገዳም እና በ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ የተፈጠሩ ዝንባሌዎችን ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ላሉት አክራሪነት/ጽንፈኝነት›› በጉልሕ ማሳያነት አቀረቡ
- ‹‹በስደተኛው ሲኖዶስ የተሸፈኑና በማኅበረ ቅዱሳን የመሸጉ የትምክህት ኀይሎች የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል››
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባዘጋጁትና ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በተካሄደው ‹‹አገር አቀፍ የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ውይይት ከተካሄደባቸው ጽሑፎች መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡
በሰባት ንኡሳን አርእስት ተከፋፍሎ በስፋት የቀረበው ጽሑፋቸው÷ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥት አንጻር እንዴት እንደሚታይ፣ በአገራችን ይታያሉ ያሏቸውን የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች፣ አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን የማስፋፊያ ስልቶችን፣ የአክራሪ/ጽንፈኛ ኃይሎች መነሻና መድረሻ ምስጢር፣ ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረጉ የአክራሪነት አደጋዎች እና አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ መሠራት ይገባቸዋል ያሏቸው ስድስት የመፍትሔ ሐሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡
በሚኒስትሩ ጽሑፍ አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቃል የተበየነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ ይኸውም አክራሪነት/ጽንፈኝነት÷ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፯ ንኡስ አንቀጽ ፫ ዜጎች የፈለጉትን እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው የተደነገገውን በመተላለፍ የሃይማኖትና እምነት ነጻነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፭ ስለ እኩልነት መብት በሚደነግጋቸው ንኡሳን አንቀጾች በሃይማኖቶች መካከል የማበላለጥ ጉዳይ እንደማይኖር የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጣስ የሃይማኖት እኩልነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ስለ መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመፃረር መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመሥረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡
አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖቶች ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ገጽታም ያለውና የሚመጋገብ እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም የሚል ሃይማኖትና አገር ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ እንደየአገሩ የሕዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪክ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት ተጋላጭነት የመላቀቅ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት የብዝሃነት አያያዝ ጥበቃ ዋስትና ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
Thursday, September 5, 2013
ስብሓት ነጋ ጥፋቷን ስለሚመኙላት ቤተ ክርስቲያንና መግደያ ብትር ሊያደርጉት ስለሞከሩት ማኅበረ ቅዱሳን ይወተውታሉ
- ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?
‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም››
/አቶ ስብሓት ነጋ/
(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
Tuesday, July 23, 2013
አቡነ ጢሞቴዎስ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊነት ተገለሉ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ኮሌጁን በጊዜያዊ ሓላፊነት እንዲመሩ ተመድበዋል
- አቡነ ጢሞቴዎስ ጉዳያቸው ከሚታይበት ስብሰባ ላለመውጣት ሲለመኑ ውለዋል
- ፓትርያሪኩ ስለ አቡነ ጢሞቴዎስ ብዙ ከመናገር ተጠንቅቀዋል፤ ተቆጥበዋል
- ደቀ መዛሙርቱና መምህራኑ ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር እየገለጹ ነው
- የቦርድ አባላቱ በሲኖዶሱ ፊት ያሰሙት ያልተጠበቀ ምስክርነት አስተዳደሩን አጋልጧል
- የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ቅ/ሲኖዶሱ መመሪያ ሰጥቷል
- የንቡረ እድ ኤልያስ ምደባ ከሚያስነሣው ግዙፍ ጥያቄ ጋራ የምረቃው ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል..
ላለፉት 14 ዓመታት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን በበላይ ሓላፊነት ሲመሩ የቆዩት ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ ከሥልጣናቸው እንዲገለሉ ቅዱስ ሲኖዶስ መስማማቱ ተገለጸ፡፡
Thursday, July 18, 2013
ዜና ብሥራት ዘሥላሴ! ሐኬተኛው እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ወሰነ!
- መ/ር ፍሥሐ ጽዮን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ
- የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው
- የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሌጁ አስተዳደርና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ላለፉት ስድስት ወራት እየተባባሰ የመጣውን ውዝግብ ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ከኮሌጁ መምህራንና የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች ጋራ ከመከረ በኋላ ነው፡፡
ትላንት እና ዛሬ ቋሚ ሲኖዶሱ በወቅታዊ የኮሌጁ ኹኔታ ላይ ሲያካሂድ በዋላቸው ተከታታይ ስብሰባዎች፣ አጣሪ ኮሚቴው የኮሌጁንአካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ይዞታ ለማሻሻል ከአጭር እና ረጅም ጊዜ አኳያ በመፍትሔነት ያቀረባቸውን የውሳኔ ሐሳቦች መርምሯል፡፡ በዚህም መሠረት በኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት ቅሬታ ከቀረበባቸው መካከል አንዱ የኾነውና ተደራራቢ ሓላፊነቶችን የያዘው ዘላለም ረድኤት ከሐላፊነቱ መነሣት እንዳለበት ተስማምቷል፡፡
በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ዘላለም ረድኤት ‹‹መምህር፣ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽንና የአስተዳደር ጉባኤ አባል›› ነበር፡፡ በሐኬተኛውና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ላይ የታዩበትን ጉድለቶችና ድክመቶች ኮሚቴው በሪፖርቱ ገጽ 14 ላይ እንደሚከተለው ዘርዝሮታል፡-
Tuesday, July 16, 2013
የቤተክርስቲያን ፈተናዎች
Let's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!
ዋልድባ በቪኦኤ July 2, 2012
Let's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!
ESAT RADIO Feb 14 2013
Let's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!
Monday, July 15, 2013
ሰበር ዜና - ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ
የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ምድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል
· ደቀ መዛሙርቱ በቀጣይ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው
በዘረኝነት እና በጎሰኝነት ታንቆ የተያዘው የቅ.ሥ.መ.ኮ. የመዘጋት ፍርድ ተበየነበት! ያሳዝናል! ! ! ! |
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡
ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ ፰ እስከነገ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ››ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
‹‹የቀኑ ትምህርት የተቋረጠ መኾኑን ስለማሳወቅ›› በሚል በቁጥር ል/ጽ/445/339/05 በቀን 8/11/05 ዓ.ምበፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ ተፈርሞ በአድራሻ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተላከው ይኸው ደብዳቤ፣የቀኑ መርሐ ግብር የተዘጋው ከኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከተመረመረ በኋላ መኾኑን አስታውቋል፡፡
ምእመኑ በቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲኾን ደቀ መዛሙርቱ ጠየቁ
- በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
- አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል
- የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው
ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡
የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት በዛሬው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል ላይ ለመጣው ምእመን ተቃውሟቸውን የገለጹባቸው ኀይለ ቃሎች
- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!
- የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!
- ልጆቹን የማይጠይቅ አባት አለን?
- ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!
- የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ!
- ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳)
- ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን!
- የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን!
- ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ!
- ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው ሊበረታታቱ እንጂ ሊባረሩ አይገባም!
- ከአየህጉረ ስብከቱ ቤተ ክርስቲያንን አምነን ወጥተን ለረኀብ ተጋለጥን፡፡
- ኮሌጁ በመዘጋቱ ከተመገብን ሰባተኛ ቀናችን ነው፡፡
- አቤቱ የኾነብንን አስብ፡፡
- ኮሌጁን የሚዘጋው የከፈተው ሲኖዶስ ነው፡፡
- ኮሌጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የግለሰቦች አይደለም!
- እውነትን ሙስና አይደለም መቃብር አያሸንፈውም!
- ጌታ ሆይ፣ ከመቅደሳችን ውስጥ የሙስናን እሾኽ ንቀል!
- እየሞትንና እየተራብን ሙስናንና ዘረኝነትን እንቃወማለን!
- ሙስና ከቤተ ክርስቲያናችን ይወገድ!
- ከሓላፊነት መሸሽ በራሱ ሙስና ነው!
Thursday, July 11, 2013
ፖሊስ ደቀ መዛሙርቱን ከኮሌጁ ግቢ እንዲያስወጣ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ጠየቀ፤ የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ውሳኔውን በጽኑ ተቃውመዋል
- ኮሌጁ እንዲዘጋ የውሳኔ መነሻ የሰጠው ከአቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ያልወጣው የኮሌጁ ቦርድ ነው
- የኮሌጁ ምግብ ቤት አገልግሎቱን እንዲያቆም በመታዘዙ ደቀ መዛሙርቱ ምሳና ራት ተከልክለው ውለዋል
- አቤቱታቸውን ለመንግሥት አካላት ያሰሙት ደቀ መዛሙርቱ ‹‹ቅ/ሲኖዶስ እና ምእመናን የከፈቱት ኮሌጁ የሚዘጋው በመቃብራችን ላይ ነው!›› በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል፤ በአስተዳደር ሕንጻው ዙሪያ የሚያደርጉትን ቁጥጥር አጠናክረዋል
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የፌዴራል ፖሊስ ኀይልን እገዛ መጠየቁ ተገለጸ፡፡
በልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ስም ተፈርሞ የወጣውና ለፌዴራል ፖሊስ እንደተጻፈ በተገለጸው ደብዳቤ÷ ልዩ ጽ/ቤቱ የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በሰላም ነሽነት በመወንጀል ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን ያስታወቀ ሲኾን በዚህም መሠረት ፖሊስ ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው የሚወጡበትን ርምጃ እንዲወስድ እገዛ መጠየቁ ታውቋል፡፡
የልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ የተጻፈው በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ የሚነገረውና በደቀ መዛሙርቱ የችግሩ አካል ተደርጎ የሚተቸው የኮሌጁ ቦርድ ኮሌጁ እንዲዘጋ በሰጠው የውሳኔ መነሻ መኾኑ ተነግሯል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በአቡነ ገሪማ የበላይ ሓላፊነት የሚመራው የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የቦርዱን መነሻ በመቀበል ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑንና ደቀ መዛሙርቱም ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መጠየቁን በጽኑ ተቃውመዋል፡፡
ፓትርያሪኩ ኮሌጁን የመዝጋት ሥልጣን እንደሌላቸው የገለጹት የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሓላፊው ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ‹‹በኮሌጁ ላይ ለመወሰን ሙሉ ሥልጣን ያለው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነው፤›› በማለት በመንበረ ፓትርያሪኩ ስምምነት በተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ተግባራዊ እንዲኾን ተሟግተዋል፡፡ ከኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ጋራ የሚስማማው ይኸው የብፁዕነታቸው አቋም ከፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጋራ በትይዩ እንዳቋማቸውና የከረረ ውዝግብ ውስጥ እንደከተታቸው ተዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ አኳኋን አምስት አባላት የሚገኙበትን አጣሪ ኮሚቴ በተወካዩ አማካይነት በሰብሳቢነት የመራው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ኮሌጁ እንዲዘጋ ያስተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ኮሚቴው አጣርቶ ያቀረበውና ፓትርያሪኩም እንደተስማሙበት የተመለከተው የመፍትሔ ሐሳብ ተፈጻሚ እንዲኾን መጠየቁ ተሰምቷል፡፡
Source: Hara ZetewahedoLet's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያርኩ ቅጽር የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው
- ፖሊስ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ አነጋግሯል
- ‹‹ከሣሾቼን እንዳታነጋግሩ›› ያሉት አቡነ ጢሞቴዎስ ቋሚ ሲኖዶሱ በጉዳዩ ላይ እንዳይወያይ ማከላከላቸው ተሰምቷል
- በተቃውሞው የተበሳጩት ሊቀ ጳጳሱ ራሳቸውን ስተው እንደነበር ተጠቁሟል
- ‹‹አልፈው በመቃብራቸው ላይ መሣቅ እንፈልጋለን›› – የጥላቻው ምሬት
- ‹‹በተራዘመው መርሐ ግብር ሳቢያ የተጨመረው በጀት ለብክነት እየተዳረገ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
ዛሬ ጠዋት ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያመሩት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር ላይ የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው፡፡
ጥቁር የአገልግሎት ቀሚሳቸውንና መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ በሰልፍ ያመሩት ደቀ መዛሙርቱ፣ ወደ ቅጽሩ እንዳይዘልቁ በጥበቃ ሓላፊው በታገዱበት ነው የተቃውሞ ትዕይንታቸውን በማካሄድ ላይ ያሉት፡፡
ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ለመግባት የተፈቀደላቸው የደቀ መዛሙርቱ መማክርት መሪዎች/ተወካዮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች ጋራ እየተነጋገሩ እንዳሉ የተመለከተ ሲኾን ቋሚ ሲኖዶሱም በጉዳዩ ላይ እየመከረበት ስለመኾኑ፣ ‹‹በግቢው ጥበቃ ሓላፊ አቶ ብርሃኔ ኀይሉ ተነግሮናል፤›› ብለዋል፡፡
Tuesday, July 9, 2013
በዋልድባ ገዳም ግፉ እና እንግልቱ እንደቀጠለ ነው፥ አረማውያን የግፍ በትራቸውን በገዳማውያን አባቶች ላይ እየሰነዘሩ ነው!
![]() |
ገዳማውያኑ ያለበደላቸው ለምን ይንገላቱ? |
ከትናንት በስቲያ በደረሰን ሪፖርት እንደሚያመለክተው ላለፉት ጥቂት ወራቶች ሲደረግ እንደነበረው ታጣቂዎች በመነኮሳቱ ላይ ድብደባ፣ እንግልት፣ ስድብ እና እስራት እየፈጸሙባቸው ይገኛሉ። መንግሥት በዋልድባ ገዳም ላይ የሥኳር ፋብሪካ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ፣ የፖርክ ይዞታን እከልላለው ብሎ በመነሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሏት በርካታ ገዳማት በጥንታዊነቱ እና በታሪካዊነቱ የሚታወቀውን የዋልድባ (ዋሊ) ገዳም ለማፍረስ እና ገዳማውያኑን ለማሰደድ አረማውያን ደፋ ቀና ማለት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በገዳማውያኑ ላይ ሲደርስ በሰዎች ዘንድ ምንም ጥያቄ እና የመከላከል እርምጃ ባይደረግም ነገር ግን የቤተክርስቲያኒቱ መስራች መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ተዓምራትን እያሳየ በርካታ እንቅፋቶችን ቢፈጥርባቸውም፥ ነገርግን በእምቢተኛነት ተግዳሮቱን እንደቀጠለ ነው፥ ነገር ግን የልብሳቸውን አዳፋነት፣ የሰውነታቸውን ክሳት አይቶ ሳይፈራ ስቃይንና መከራን ያበዛባቸውን አረማዊ እንዳይፈሩ በትንቢተ ኢሳያስ ፶፩ ፥ ፯ ላይ የሰፈረውን ቃል መመልከት በቂ ነው፤ እንዲህ ይላል “ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።” ኢሳ. ፶፩ ፥ ፯
Thursday, July 4, 2013
IUEOTCFF (ዋልድባን እንታደግ) በሰሜን አሜሪካ ስፖርትና ባሕል ፌዴሬሽን ፴ኛ ዓመት በዓል ላይ በመገኘት ዝጅቶችን እያቀረበ ነው
ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከያዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ
በርድ ስታዲዮም በሚደረገው የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባሕር ፌዴሬሽን 30ኛ ዓመት በዓል ላይ በመገኘት በዓሉ ላይ ለመገኘት ለሚመጡት
ኢትዮጵያውያን ግንዛቤት በማስጨበጥ እና ተቋሙን ለማጠናከር የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያውያን
ዘመን አቆጣጠር ከሰኔ ፳፭ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓም (June 30 – July 6,
2013) የሚቀጥል ሲሆን በበዓሉም ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከመላው ዓለም የሚገኙበት ሲሆን ምዕመናን፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ልጆች፣ የቤተክርስቲያኒቷ ወዳጆች በርካታ እርዳታዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል እያበረከቱም ነው ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ዘወትር የማያልቅበትን
በረከቱን ለምዕማናን እንዲያበዛልን እየተመኘን በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ዝግጅቱ ስለሚቀጥል በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን
በሙሉ በትብብራችሁ እንትበረቱ እና ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከጥፋት፣ ገዳማት አድባራቱን ከምዝበራ፣ ንጹሐን መነኮሳትና መነኮሳይትን
ከስደት፣ ዋልድባን ከመፈታት እንድንታደግ አደራ እንላለን።
በዚህ በዓል ላይ እጅግ በሚያኮራ እና በሚያስደስት ፍፁም የቤተክርስቲያን
ቅንዓት ጫማዎችን በመጥረግ (ሊስትሮ)
በማስጠረግ በርካታ ክርስቲያኖች ትብራቸውን እያደረጉ ነው በዚህም ቤተክርስያናቸውን ከጥፋት ለመታደግ፣ ዋልድባን እና የተለያዩ ገዳማትን ለመታደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ተባባሪነታቸው አሳይተዋል እና በመጨረሻው ዘመን አምላከ ቅዱሳን በክብር በሚገለጽበት ጊዜ “ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን” ተብለው ከሚጠሩት ከቅዱሳን ወገን እንዲደምርልን ለአምላካችን ዘወትር በጸሎት እናመለክታለን።
በመጨረሻ በበዓሉ መጨረሻ ላይ ማለትም አርብ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፭
ዓ.ም. (July
5, 2013) ከ
4:00 PM. ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እና የመንግሥት ተግዳሮት በሚል ርዕስ ዝግጅት ስለሚኖረን በድንኳን
ቁጥር 41
ፊትለፊት በመገኘት
የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)