Monday, January 28, 2013

አቶ ሲሣይ ለአቤቱታ በወጡት አባቶች ላይ ማስፈራራቱን ቀጥሏል

የገዳማውያኑ በረከት ይደርብን


·         ዋልድባ ከምትመለሱ እናታችሁ ሆድ ብትገቡ ይቀላችኋል (አቶ ሲሣይ መሬሳ)
·         የሽሬ እና እንደስላሴ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የአቶ ሲሣይን አካሄድ መቃወም አለባቸው
·         የባሕር ዳር ሕዝበ ክርስቲያን እና የጎንደር ሕዝበ ክርስቲያን ሊመሰገኑ ይገባል
በፒዲፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ      

ባለፈው ሳምንት ከ30 - 40 የሚጠጉ መነኮሳት እና መነኮሳይት ከዋልድባ ገዳም በረሃ አቋርጠው ለሚመለከተው ክፍል አቤት ለማለት፣ በእነ አቶ ሲሣይ እየደረሰባቸው ያለውን ግፍ ለማሳወቅ፣ ቤተክርስቲያናችንን ይተውልን በማለት አቤት ለማለት ወደ ጎንደር ከዛም ወደ ባሕር ዳር የተጓዘው የመነኮሳቱ እና የመነኮሳይቱ ቡድን አቤቱታቸውን ለሚመለከተው የመንግሥት አካላት እንዲሁም ለቤተክርስቲያኒቱ ለቀረቡት ሁሉ ብሶታቸውን ገዳማቸው (ገዳማችን) በጥቂት ጽንፈኞች በግፍ መነጠቁን ሲያሳውቁ ቆይተዋል፤ አሁንም በዚው ሥራቸው ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Wednesday, January 23, 2013

የዋልድባ ውዝግብ እንደቀጠለ ነው


ሙሉውን ቃል በ PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
·         አማርኛ ተናጋሪ መነኮሳት ከገዳማቸው በግፍ ተባረዋል
·         መነኮሳቱ ለሁለት ቀናት ተጉዘው ጎንደር ገብተዋል
·         የትግራይ ተወላጅ አበሜኔት እና እቃ ቤት በአቶ ሲሣይ መሬሳ ተሹመዋል
·         በባሕር ዳር ከተማ ተገኝተው ለክልሉ ፕሬዘዳንት አቤቱታ በማሰማት ላይ ናቸው
አቶ ሲሣይ መሬሳ

ባለፈው ሳምንት እንደዘገብነው በአቶ ሲሣይ መሬሳ መሪነት ገዳማውያን መነኮሳት በግፍ አማርኛ ተናጋሪዎች ናችሁ የተባሉት ተባረዋል፣ አቅም ያላቸው በረሃ አቋርጠው ሸሽተዋል፣ ደካሞቹ አረጋውያን አባቶች እጅግ በሚያዝን ሁኔታ ጺማቸውን እየተነጩ፣ ቆባቸውን እያቀለቁ ገረፋቸው፣ ደበደቧቸው፣ ጭንቅላታቸውን በሰደፍ ደበደቧቸው . . . እውን የሰው ዘር ቀርቶ ለዚያውም ከአንድ አፈር ኢትዮጵያ ምድር የበቀለ ሰው ይፈጽመዋል ለማለት እጅግ ይከብዳል። ነገር ግን የራሳችን ሰዎች ከኢትዮጵያ አብራክ ክፋዮች ነገር ግን እራሳቸውን የአንድ ጎጥ እና ወንዝ ሰዎች ነን ብለው የለዩ፣ በዚያች ምድር ላይ ፈልገው ያልተወለዱ፣ ሰው ሊፈጽመው የማይችለውን ፍጹም ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ አረጋውያን አባቶችን ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ክርስተት ሆኗል። ለተቀሩትም የማስፈራሪያ መዓት እየደረሳችው ነው “ገዳሙን ለቃችሁ ባትሄዱ፥ ማን እንደገደላችሁ ሳይታወቅ ትሞታላችሁ” “ይሄ ምድር ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነው፥ እናንተ ልትኖሩበት ቀርቶ ልትረግጡት አትችሉም” እና የመሳሰሉትን የማስፈራሪያ ቃላት በታጣቂዎች አማካኝነት እየተነገራቸው ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ያለ ጸሎት መጽሐፍ እና መቋሚያ የሌላቸው መነኮሳት እቤታቸውን “መሣሪያ ታጥቃችኋል” በሚል ሰበብ ዘወትር ብርበራው እና ማንገላታቱ በወጡ በገቡ ቁጥር በርግጫ እና በጡጫ መሰቃየታቸውን ቀጥለውበታል። 

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ


·       የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤
·       ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው” ነው፤
  •       መነኮሳት ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፤
  • ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።
የክልሉ መንግሥት የመናንያኑን አቤቱታ ይቀበል ይሆን? የምናየው ይሆናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

Tuesday, January 15, 2013

በዋልድባ አበረንታት አዲስ የትግራይ ተወላጅ አበሜኔት ለማስመረጥ ለጥር ፲፫ ቀጠሮ ተይዟል

በዋልድባ አባቶች ላይ ግፉ እና ድብደባው እንደቀጠለ ነው

  • በዋልድባ አበረንታት የትግራይ ተወላጅ አበሜኔት መመረጥ አለበት (አቶ ሲሣይ መሬሳ)
  • አማሪኛ ተናጋሪ እና የአማራ ተወላጆችን በግድ ማስወጣት አለብን (አቶ ሲሣይ መሬሳ)
"ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።" የሐሪያት ሥራ ፲፱ ፥ ፲፮

በእነ አቶ ሲሣይ መሬሳ የሚመራው ግፈኛው፣ ጽንፈኛው እና ርህራሄ ቢስ የሆኑት የመንግሥት ታጣቂዎች ዛሬም ኢ-ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ አባቶችን እየደበደቡ፣ እያዳፉ፣ ወደ እስር አለያም ለሞት እያዳረጉ እንዳሉ ሁኔታውን የሚከታተሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እያመለከቱ ነው። ዛሬም በዋልድባ በቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር ተቀምጠው፣ ወደ አምላካቸው ዘወትር ጠዋት ማታ ባለቀሱ፣ ሰላሙን አንድነቱን ስጠን ብለው በጸለዩ በግራኝ መሐመድ እና በዮዲት ጉዲት ጊዜ ይደርስ ከነበረው ግፍ ባልተናነሰ ሁኔታ በገዛ ወገኖቻቸው ወንድሞቻቸው የግፉን ጽዋ እየተጎነጩት ባሉበት ባሁኑ ሰዓት . . . መነኮሳቱ ኸረ የሰው ያለህ . . .ኸረ የቤተክርስቲያን አምላክ ያለህ . . . በማለት ጩኸታቸውን እየሰሙ ነው። የአካባቢውም ባለሥልጣናት የጭቃ ጅራፋቸውን በስግደት፣ በጸሎት፣ በቋርፍ በደከመው ገላ ላይ ያለ ርህራሄ ያወርዱት ጀምረዋል። 

Monday, January 14, 2013

የድረሱልን ጥሪ ከዋልድባ ገዳም ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን


የዋልድባ ገዳም አባቶች በድጋሚ የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው፣ አባቶች እየተደበደቡ ነው፣ እየታሰሩ ነው፣ ያለ በደላቸው በመከላከያ ሰራዊት ሃይሎች በደል እየደረሰባቸው ነው። የድረሱልን ጥሪያቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ እንዲደርስ በESAT RADIO አማካኝነት አስተላልፈዋል።
ልብ ያለው ልብ ይበል እንላለን

Sunday, January 13, 2013

የስልክ ጉባኤ ጥሪ ጥር ፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (Jan. 13, 2013)


ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን ምዕመናንና ምዕመናት በሙሉ
የጸሎትና የውይይት መርሐግብር:-
ሐዋርያዊት ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት ስለሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት : በልጆቿ መካከል ሊፈጠር ስለሚገባው ሰላም: ፍቅርና ሕብረት የተዘጋጀ የጸሎት መርሐግብር ይምጡና ስለ ሰላምና አንድነት በጋራ እንጸልይ :: እንመካከር::
የኮንፈረንስ ቁጥር 1-559-726-1200      መግቢያ ኮድ 24-81-12
እሑድ  ጥር 5 ቀን 2005 ዓ/ም (JANUARY 13, 2013 )
ሰዓት፦     8:00 PM - 10:00 PM በዲሲ ሰዓት (EST) /
            5:00 PM - 7:00 PM ካሊፎርኒያ ሰዓት (PST)

ጉባኤ ካህናት ወምዕመናን ለቤተክርስቲያን ሰላም

Friday, January 11, 2013

በዋልድባ ዛሬም እስራቱና እንግልቱ እንደቀጠለ ነው

ዘረኛው አቶ ሲሣይ መሪሳ

በትላንትናው እለት እንደዘገብነው በማይጸብሪና ጸለምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መሪሳ ትእዛዝ ሰጪነት ሦስት የአካባቢው ነዋሪዎች በገዳሙ ክልል ውስጥ በመግባት በእስራት ወደ ማይጸብሪ ከተማ በመውሰት እዚያው በእስራት መቆየታቸውን እና በርካታዎች ሸሽተው ማምለጣቸውን ዘግበን ነበር። አሁንም ጽንፈኛው የአውራጃው አስተዳዳሪ ታጣቂዎቻቸውን በመላክ ወደ ገዳሙ ክልል ውስጥ በመግባት መነኮሳቱን ሲያንገላቱ፣ ሲያዳፉ፣ ሲደበድቡ ቆይተው በትላንት ምሽት ላይ ሁለት መነኮሳትን ማይለበጣ ላይ አንስተው እየደበደቡ እና እያሰቃቁ ወደ እስራት ወስደዋቸዋል፣ በመቀጠል በዛሬው ረፋዱ ላይ እነዚሁ ታጣቂዎች ተመልሰው በመምጣት ዶንዶሮቃ ላይ ሁለት ተጨማሪ መነኮሳትን እየደበደቡ ለእውራት እና ለእንግልት መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሱን ምንጮች ገልጸውልናል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን የተማኅጽኖ ደብዳቤሙሉውን የደብዳቤውን ይዞታ ለመመልከት ይዚህ ይጫኑ 

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለዉ «ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል።»

Thursday, January 10, 2013

"የገበያ ግርግር፥ ለሌባ ይመቻል" የምርጫው ግርግር ለአጥፍዎች ተመቻችቶ ተገኝቷል

ገዳመ ዋልድባ ዛሬም እንደትላንቱ ያለተቆርቋሪ፣ ያለከልካይ፣ ያለባለቤት እየታረሰ ነው፥ የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የወረዳ እና የአውራጃ ባላባቶች በመንግሥት የተሾሙ እንደመሆናቸው ታሪካዊነቱን ጥንታዊነቱን እንዲሁም ቅድስናውን በአንደበታቸው ቢመሰክሩም ገዳሙን ከጥፋት እና ከመፍታት የታቀቡበት ጊዜ የለም። ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ውስጥ እስከ ዛሬ በርካታ ነገሥታት እና መሪዎች ቢያልፉባትም እንደዛሬው አይነት መንግሥት ታሪኳን ለመቀየር እና ትውፊቷን ለማጥፋት የተነሳበት ጊዜ የለም ብንል ማጋነን ሊሆንብን አይችልም። እውን ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሰዎች እንደሚፈልጉት የክርስትያን ደሴት መሆኗ ቀርቶ የአረማውያን ደሴት ትሆን ይሆን? እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እንኳን ልጇን እና ወዳጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ያዛ በምድረ ኢትዮጵያ ይልቁንም ዋልድባን በረገጡት እግሮቿ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የገባላት ምድር እውን ይሆን ይሆን? አዎ ዛሬ ዛሬ ብዙ ነገሮች መለወጣቸው የለመነውን ልመና ያልሰማን ሲመስለን፣ ይልቁንም የሃይማኖት አባቶቻችን ዝምታቸውን ሲያበዙ፣ መምህራን እና ዘማሪያን ድምጻውን ቢያጠፉ ይህች ርትዕይት ሃይማኖታችን አለሁ ባይ ብጣም በወጀብ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ በዙፋኑ አለ ብለን ለምናምነው ችግር እና መከራ ቢበዛም በመጨረሻ እኛ የምናምነው መድኃኒዓለም ክርስቶስ ቤተክርስቲያናችንን ገዳሞቻችንን ለአረማውያን አሳልፎ እንደማይሰጥ በጽኑ እናምናለን።

የዛሬ ሁለት ሳምንት ይሆናል የማይጸብሪ ወረዳ እና አውራጃ ነዋሪዎች እንዲሁም የወልቃይት አካባቢ ገበሬ ማኅበራት ገዳማችንን ዝም ብለን ሲጠፋ መመልከት የለብንም ከአባቶቻችን ጋር ሆነን እንጸልያለን አለያም እንሰዋለን በማለት ወደ ገዳመ ዋልድባ ለመሄድ የአካባቢውን የመንግሥት ባለ ሥልጣናት የጠየቁን፥ የማይጸብሪ እና ጸለምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መሪሳ ማንም ወደ ገዳሙ መሄድ አይችልም እንዲያውም እኛ እናስተካክላቸዋለን በማለት በትዕቢት ለአካባቢው ነዋሪዎች አቶ ሲሣይ ተናግሮ ነበር፥ ገዳመ ዋልድባ የአባቶች ብቻ አይደለም የዋልድባ ገዳም አባቶች ከእኛ በተሻለ ፍቅረ ክርስቶስን መርጠው ከአለም ተለይተው ለፈጣሪ ያደሩ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሁላችንም ሃላፊነት ናቸው በኃይልም ሆነ በእልህ የሚሰራ ሥራ የለም በማለት ነዋሪዎቹ ቢናገሩም አቶ ሲሣይ ግን