Tuesday, January 15, 2013

በዋልድባ አበረንታት አዲስ የትግራይ ተወላጅ አበሜኔት ለማስመረጥ ለጥር ፲፫ ቀጠሮ ተይዟል

በዋልድባ አባቶች ላይ ግፉ እና ድብደባው እንደቀጠለ ነው

 • በዋልድባ አበረንታት የትግራይ ተወላጅ አበሜኔት መመረጥ አለበት (አቶ ሲሣይ መሬሳ)
 • አማሪኛ ተናጋሪ እና የአማራ ተወላጆችን በግድ ማስወጣት አለብን (አቶ ሲሣይ መሬሳ)
"ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።" የሐሪያት ሥራ ፲፱ ፥ ፲፮

በእነ አቶ ሲሣይ መሬሳ የሚመራው ግፈኛው፣ ጽንፈኛው እና ርህራሄ ቢስ የሆኑት የመንግሥት ታጣቂዎች ዛሬም ኢ-ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ አባቶችን እየደበደቡ፣ እያዳፉ፣ ወደ እስር አለያም ለሞት እያዳረጉ እንዳሉ ሁኔታውን የሚከታተሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እያመለከቱ ነው። ዛሬም በዋልድባ በቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር ተቀምጠው፣ ወደ አምላካቸው ዘወትር ጠዋት ማታ ባለቀሱ፣ ሰላሙን አንድነቱን ስጠን ብለው በጸለዩ በግራኝ መሐመድ እና በዮዲት ጉዲት ጊዜ ይደርስ ከነበረው ግፍ ባልተናነሰ ሁኔታ በገዛ ወገኖቻቸው ወንድሞቻቸው የግፉን ጽዋ እየተጎነጩት ባሉበት ባሁኑ ሰዓት . . . መነኮሳቱ ኸረ የሰው ያለህ . . .ኸረ የቤተክርስቲያን አምላክ ያለህ . . . በማለት ጩኸታቸውን እየሰሙ ነው። የአካባቢውም ባለሥልጣናት የጭቃ ጅራፋቸውን በስግደት፣ በጸሎት፣ በቋርፍ በደከመው ገላ ላይ ያለ ርህራሄ ያወርዱት ጀምረዋል። 

እውን ይሄ ለልማት ታስቦ ነው? ወይስ ሌላ ለኅብረሰቡ ያላሳወቁት ድብቅ ዓላማ አላቸው እነዚህ ሰዎች፥ መነኮሳቱ ላለፉት ዘመናት በኅብረት እግዚአብሔርን እያመለኩ፣ ዘወትር ፍቅረ ክርስቶስ ይዟቸው በበረሃ ለወደቁ አባቶቻችን እኮ ወንዝ፣ ጎጥ፣ ዘር፣ ተራራ የመሳሰሉት ነገሮች ምናቸውም አይደለም፥ ነገር ግን እነ አቶ ሲሣይ መሬሳ እና መሰሎቻቸው በአካባው ላይ ተሹመው መጥተው እንዲህ አይነት ርህራሄ የጎደለው ጭካኔ ስለምን ሲባል ይልቁንም ተነስተው ጥቃታቸውን ለመመለስ በማይችሉ ለእግዚአብሔር ባደሩ ሽማግሌ እና አዛውንት ላይ እስከ ዛሬ ታሪክ ዘላለም የማይረሳቸው እነ ግራዚያኒ፣ ሞሶሎኒ፣ ሂትለር፣ እና ስታሊን ሲያደርሱ የነበረውን ሰቆቃ እንዴት በገዛ ወገናቸው ላይ የግፍ በትራቸውን ለማነጣጠር አስፈለገ፥ እውን እነሱ እንደፈለጉት ደብድበው፣ ስቃይ አብዝተውባቸው አባቶችን ካስወጡ በኃላ ሸንኮራ ሊተከል፣ ወርቅ ሊወጣ፣ ወይንስ የእምነ በረድ ፋብሪካ ሊቋቋም እውን መድኃኒዓለም ክርስቶስ ዝም ብሎ ይመለከታል ብሎ ማሰቡስ፤ እርግጥ ነው እነዚህ ሰዎች ከነ አለቆቻቸው ኮሚኒስቶች ናቸው "ሰውን ሰው ያሰኘው ሥራው ነው" ይላሉ የአንድ ቀን እስትንፋሳቸውን በቸርነቱ የሰጠ አምላከ ቅዱሳን፣ የሰማዕታት አምላክ መሆኑን የተገነዘቡት ዛሬም በንፁሐን አባቶቻችን ላይ የግፍ ግፍ እየፈጽሙባቸው ውሎው አድረዋል።

የአሁኑ ይባስ እንዲሉ አቶ ሲሣይ መሬሳ እና መሰሎቹ በዚሁ በተቀደሰው ስፍራ በአባቶች ላይ የሚያደርሱት በደል ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ሌላ አጀንዳ ይዘው ብቅ ብለዋል። እናስተውል የገዳማት አበሜኔት በወረዳ አስተዳዳሪ ሲመረጥ እንዴት አይነት ዘመን ላይ እንደደረስን መመክከት የሚያዳግት አይመስለንም። አዎ ከአካባቢው በደረሰን መረጃ መሰረት በመጪው ሰኞ ጥር ፲፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. እነዚሁ እናውቅላችኃለን ባዮች የገዳሙን አበሜኔት "የትግራይ ተወላጅ" መሆን ይኖርበታል "መርጠን የምናስቀምጠውም እኛው ነን" በማለት በትዕቢት በተለመደው ባልተገረዘው አፋቸው ሲናገሩ መስማት ይበልጥ ያሳዝናል። ይሄ ቦታ የሰዎች ሊሆን አይችልም "እኛ አፈር ጠባቂዎች ነን" የመድኃኒዓለም ቦታ ነው በማለት በተደጋጋሚ ለማስረዳት ቢሞክሩም የደረሰባቸው በደል ይህ ነው ለማለት እስከሚያዳግት ድረስ በድብደባ እና በማሳደድ በርካታዎች ከገዳሙ እየኮበለሉ ወደ ሌሎች ገዳማት እየሄዱ ነው በመሄድም ላይ ናቸው። ግማሹም ከአባቶቻቸው እንደተማሩት ሰማዕትነት እየተቀበሉ ያለፉም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም ታዲያ ዛሬ ላይ ቆመን እነዚህን አጋር የለሽ አባቶቻችንን አረማውያን ያለርህራሄ ሲደበድቧቸው ዝም ብለን ማየት ወይስ ለምን ብለን መጠየቅ? ገዳማውያኑ ድረሱልን በማለት በተለያየ ጊዜ ጥሪያቸውን እያቀረቡ ነው ሰሚ ያገኙ ግን አይመስለንም፥ ግማሹ "ይሄ የጳጳሳት ሥራ ነው እንዴት ዝም ይላሉ" ይላል፣ ሌላው ደግሞ "ይሄማ የማኅበረ እገሌ ጉዳይ ነው" ይላል ሌላው "እኔ አገሬ ቤት እየሰራሁ ስለሆነ እንዚህ ውስጥ መግባል አልፈልግም" ይላል፣ ሌላኛው ደግሞ "የአካባቢው ነዋሪ እንዴት ዝም ብሎ ይመለከታል" ትላለች፣ ሌሎችም "እኛ በጸሎት እናግዛቸዋልን" በማለት ያፌዛሉ።

እውን ይህች ቤተክርስቲያን የማን ነች? የጳጳሳት፣ የመከኮሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ የሰባኪያነ ወንጌል፣ የዘማሪያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት ወይንስ የምዕመናን፥ በገዳም ተወስነው ሲጸልዩ ጉልበተኞች መጥተው በጥፊ፣ በርግጫ፣ በቡጢ ብለው የሰውን ጥርስ ማውለቅ እና ጉንጭ መቅደድ ይቻላቸዋልስ ወይ? ቤተክርስቲያኒቱ ከልካይ፣ ተው ባይ፣ ተቆጪ፣ ወይስ መስዋዕት ሊሆን የተዘጋጀስ የለም እንዴ? ስለእውነት ጳጳሳት ካልተናገሩ ታሪካዊ እና ቅዱስ የሆሁ ገዳማት ሲፈቱ ዝም ብሎ መመልከት ከመነኮሳቱ፣ ከካህናቱ፣ ከመምህራኑና ከሰንበት ተማሪውስ ይጠበቃል? ወይንስ እዛ ያለው እሳት እኛ ጋር የማይመጣበት ሁኔታ ይታየናል?
እኔ ምን አገባኝ በማለት አጠገቧ ካለው ኩሬ ዘላ ገባች ይባላል፥ እሳቱ ሲባባስ ሰፈርተኛው ኸረ ውሃ አምጡ ሲባል ጎረቤቱ ቡሉ በሉ ባሊ ይዛችሁ ከኩሬው ውሃ በማምጣት እሳቱን አጥፉ ሲባል፣ እትዬ እንቁራሪት በኩሪው ነበረች እና ከውሃው ጋር ቀላቅለው ወደ እሳቱ ከተቷት ይባላል" እና አሁንም እኛ፤ ወልድባ ገዳም ሲፈታ የእኛ አልተነካም፣ የእኛ ደብር፣ አጥቢያ ወይንም ቦታ አልተነካም ብንል ወደድንም ጠላንም ነገ ወደእኛ መምጣቱ አይቀሬ ነውና "ሳይርቅ በቅርቡ፥ ሳይደርቅ በርጥቡ" እንደሚባለው ታሪካዊውን እና ጥንታዊውን ገዳም ከአረማውያን ልንታደግ ይገባናል እንላለን።

በመጨረሻ ለግፈኞቹ ዛሬ ጊዜው የእናንተ ቢሆንም፣ እንደምታስቡት ደካማ አባቶቻችንን ደብድባችሁ ስቃይ አብዝታችሁባቸው ገዳሙን ለቀው ቢወጡም፣ የምትፈልጉትን "የትግራይ ተወላጅ" አበሜኔት ብትሾሙም፣ ጊዜው የናንተ ቢመስላችሁም፣ ሰማይ ዝቅ፣ ምድርም ከፍ ብትል እምነታችን የጸና ነው በዓለም ብርቱ እና ፈርጣማ የተባሉ ነገሥታት አልፈዋል ከአፈር በታች ዝቅ ብለዋል ነገር ግን እናንተም ጊዜ በእናንተ መመለሱ የማይቀር ነውና የእግዚአብሔርን ቤት ለማፍረስ፣ ቅርስ ለማጥፋት፣ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የምታደርጉት ትግል ሁሉ ሊሰራ እንደማይችል ልትገነዘቡት በተገባ ነበር፥ ነገር ግን አልሆነም አሁንም ጊዜው አልመሸም ይህን አብሮ የኖረን ሕዝብ ይልቁንም ገዳማውያኑን አትለያዩዋቸው ነገር ግን አሻፈረን ብትሉ ውርድ ከራስ ነውና ነገ በታሪክ ተወቃሽ፣ በትውልድ የተጠላችሁ፣ በእግዚአብሔርም የተረገማችሁ እንደምትሆኑ ልብ ልትሉ ይገባል እንላለን። የሰሞኑን ውሎ እንደደረሰን እናቀርባለን።
መልካም ወሬ ያሰማን አሜን

7 comments:

 1. እንዘ መጠነዝ ይበዝኅ ህላዌ ግፍዕ ላዕለ አበዊነ፤ ይትከሀለነኑ አርምሞ?
  ባባቶቻችን ላይ ይኽን ያኽል ግዙፍ ግፍ ሲደራረብባቸው፤ ዝም ማለት ይቻለናልን?
  ወንክልኑ ንትኌለቊ ውሉደ ዚኣሆሙ?
  የነርሱ ልጆች ተብለን ልንቆጠርስ እንችላለንን?
  ወብነኑ ኣፍ በዘንቤ ብነ ሃይማኖት?
  ሀይማኖት አለን በምንል ገንዘብ ሃይማኖት አለን የምንልበት አፍስ ይኖረናል?
  ጥቀኑ ይትከሀል ብሂል ሀሎነ?
  ረ አለን ማለት ይቻላልን?
  እምልሂቅ እስከ ደቂቅ!
  ዐምስት ኪሎ ከተዘረፈጡት ሽማግሎች በየኳስ ሜዳው እስከምንራወጠው ጩጬዎች!

  ReplyDelete
 2. After Megabit 27,2005 E.C you will see what will happen!

  ReplyDelete
 3. አዎ መረጃዎችን በወቅቱ እንዲደርሰን ማድረጋችሁ እግዚአብሄር ይስጣችሁ ነገር ግን ሁሉም በመረጃ መረብ ውስጥ ተሸሽጎ ለምን ዝም ብለን እናያለን ለምን በእራሳችን እስኪደርስ ዝም ብለን እንምለከታለን ምናምን እያሉ መቀስቀስ ለኔ አይገባኝም የሄ የሁለችንም ሀላፊነት እስከሆነ ድረስ በመረጃ መረብ ሳይሆን በአካል መሰዋዕትነት ለምክፈል ዝግጁ መሆን ይገባናል ከዛም ተከታይ እናገኛለን .... እምላክ ቤተክርስቲያናችንን/ገዳማቶቻችንን/አባቶቻችንን ይጠብቅልን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንባቢያችን እንዳሉት እኛ መረጃ ማድረስ እና በገዳሙ ያሉትን ችግሮች አቅም በፈቀደ በመርዳት ይህ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ገዳም፥ ሳይፈታ ተጠብቆ ከነ ሙሉ ክብሩ ለትውልድ እንዲተላለፍ ብሎም በጸሎት ተወስነው የሚኖሩ አባቶችን መንግሥት እንዳይነካብን የምንችለውን ያህል ጥረት እናደርጋለን። ከዚህ በተጨማሪ በዋልድባ ገዳም ዙሪያ በመጀመሪያ መነኮሳቱ ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው፣ ክቡር ሕይወታቸውን ጨምሮ ያጡትን አባቶች እግዚአብሔር አምላክ የራሄልን እንባ የሰማ የእነሱንም ጩኸት ሰምቶ በሞታቸው ለገዳሙ ሕይወት እንዲያደርጋቸው ልመናችን ነው። የአካባቢውም ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው በይበልጥ የወልቃይት፣ ጃናሞራ፣ ጨው በር፣ ጸለምት ነዋሪዎች ብዙ መስዋዕትነት ከፍለዋል እየከፈሉም ይገኛሉ በአሁን ሰዓት በእነ አቶ ሲሣይ መሬሳ እስር ቤት ውስጥ የሚሰቃዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ገዳማችንን አታፍርሱ ነው ጥያቄያቸው እንጂ የወረዳው አስተዳዳሪ ይቀየር አላሉም። ስለዚህ አንባቢያችን እንዳሉት ዝም ያለ የለም ወደፊትም እግዚአብሔር እስከፈቀደ ድርስ ዝም አንልም፥ ምናልባት እኛን አይመለከትንም ብለን ዝም ያልን ክርስቲያኖች ብንኖር ሕሊና ይፍረደው። ሃይማኖታችንን መጠበቅ የእኛ የአማኞቹ ፋንታ ነበር፥ ነገር ግን በተቃራኒው መናኒያኑ መስዋዕትነት እየከፈሉ ኑ ገዳማችሁን ተረከቡን . . . ሌላው ቀርቶ የገዳሙን አበሜኔት ዘረኞች ለነሱ እንዲመቻቸው ካድሬ አምጥተው ሲያስቀምጡ የተቃወሙት መነኮሳት እና መናኒያን ጺማቸው ነተጭቶ፣ ቆባቸውን አውልቀው አናታቸውን በሰደፍ ሲደበደቡ፣ በቁማቸው ባህር ከተው ሲደበድቧቸው የደረሰ የሃይማቱ ሰው እኮ የለም ታዲያ ስለምን ብለው አንባቢ ዝም ብለን እንመለከታለን ይላሉ እኔና እርሶ ነን እንጂ አባቶች መነኮሳት እና መናኒያን ሰማዕትነት እየተቀበሉ ነው ኑ . . .ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እየተባባሉ ነው በአሜሌቃውያን እንተወገሩት ሐዋርያት ዛሬም በአረማውያን ኮሚኒስቶች አባቶቻችን እየተወገሩ ነው መስዋዕት እየሆኑ ነው እኔና እርሶ ግን ዝምታ ይሻላል ብለን ከባሕር ማዶ ተቀምጠን አይመለከተንም በማለት በዝምታ ተሸብበን ዝም ብለናል አረማውያኑም የልብ ልብ እያገኙ ዛሬ የራሳቸውን ካድሬ የገዳሙ አበሜኔት አድርገዋል በገዳሙ የሚገኙ በርካታ ቅርሶች እና የእኔና የእርሶ ኢትዮጵያዊነት እና የሃይማኖታችን መለጫ ቅርሶች በነዚህ አረማውያን በግፍ እየተመዘበረ በአውሮጳ እና አሜሪካ ገባያ ላይ ይውላሉ እነዚህ አረማውያን ይከብራሉ ቅርሶቻችን ይመዘበራሉ አባቶቻችን ይገፋሉ፣ ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ እረ ምኑ . . .
   እውን ኦርቶዶክሳውያን ከስም ውጪ ምን አድርገን ይሆን? ለመኮነንማ ማን ብሎን እነ አቡነ እከሌ ይህን ማድረግ ነበረባቸው፣ ማኅበረ እገሌ ለምን ይህን አላደረገም፣ የዚህ ፕሮግራም አዘጋጆች ለምን ሄዳችሁ መስዋዕት አልሆናችሁም፣ እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመደርደር ገዳማችን እየተፈታ ነው። ወንድሜ/እህቴ በወሬ የተገነባ ሕንጻ የለም እስከዛሬ ወይም የፈረሰ የችግሩ ገፈት ቀማሾች ገዳማውያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪ ብቻ ነው እኔና እርሶም የበኩላችንን ብናደርግ ሃይማኖታችንን ለማጥፋት ከተነሳብን መንግሥት ጀምረን ዝም አንልም እንናገራልን እንመሰክራለን ማለት ካልቻልን ትላንት በተለያዩ ነገሥታት ታፍሮ እና ተከብሮ የኖረው ገዳመ ወልድባ ነገ ምናልባት የስኳር ፋብሪካ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ፣ የእጣን ማምረቻ፣ የእምነበረድ ማምረቻ፣ ብሄራዊ ፖርክ የመሳሰሉት መንግሥት በስውር ያቀዳቸውን ሥራዎች ቀስ በቀስ የሚዘረጋበት እና የእኔና የእርሶ መኩሪያ እና የጸሎት ቦታችን እንደዘበት ሊጠፋ እንሚችል ቅንጣት ጥርጥር የለውም።
   ሊሆን የሚችለውን ዛሬ እነ እገሌ ምናደረጉ ሳይሆን፣ እኔ ምን አበረከትኩ፣ ወይስ ምን ይጠበቅብኛል በማለት እራሳችንን እናነሳሳ።
   ገዳመ ዋልድባን እግዚአብሔር አምላክ በረደኤት ይጠብቅልን
   አባቶቻችንን በሃይማኖት ያጽናልን

   Delete
 4. አዎ መረጃዎችን በወቅቱ እንዲደርሰን ማድረጋችሁ እግዚአብሄር ይስጣችሁ ነገር ግን ሁሉም በመረጃ መረብ ውስጥ ተሸሽጎ ለምን ዝም ብለን እናያለን ለምን በእራሳችን እስኪደርስ ዝም ብለን እንምለከታለን ምናምን እያሉ መቀስቀስ ለኔ አይገባኝም የሄ የሁለችንም ሀላፊነት እስከሆነ ድረስ በመረጃ መረብ ሳይሆን በአካል መሰዋዕትነት ለምክፈል ዝግጁ መሆን ይገባናል ከዛም ተከታይ እናገኛለን .... እምላክ ቤተክርስቲያናችንን/ገዳማቶቻችንን/አባቶቻችንን ይጠብቅልን!!

  ReplyDelete
 5. yeabatochachin menegelatate lisemane yegebal genezeb yalewe begenezebu yelelew be eweqetu endihum be tselotu masebe alebete .
  egiziabeheare bizegeyem yemetal yeferedal.

  amelake yeabatochachinene mekera yemeleketal

  ReplyDelete
 6. የመጋቤት ወር ውስጥ እንባ አባሽ አምላክ ይደርስልናል።

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤