Thursday, January 10, 2013

"የገበያ ግርግር፥ ለሌባ ይመቻል" የምርጫው ግርግር ለአጥፍዎች ተመቻችቶ ተገኝቷል

ገዳመ ዋልድባ ዛሬም እንደትላንቱ ያለተቆርቋሪ፣ ያለከልካይ፣ ያለባለቤት እየታረሰ ነው፥ የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የወረዳ እና የአውራጃ ባላባቶች በመንግሥት የተሾሙ እንደመሆናቸው ታሪካዊነቱን ጥንታዊነቱን እንዲሁም ቅድስናውን በአንደበታቸው ቢመሰክሩም ገዳሙን ከጥፋት እና ከመፍታት የታቀቡበት ጊዜ የለም። ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ውስጥ እስከ ዛሬ በርካታ ነገሥታት እና መሪዎች ቢያልፉባትም እንደዛሬው አይነት መንግሥት ታሪኳን ለመቀየር እና ትውፊቷን ለማጥፋት የተነሳበት ጊዜ የለም ብንል ማጋነን ሊሆንብን አይችልም። እውን ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሰዎች እንደሚፈልጉት የክርስትያን ደሴት መሆኗ ቀርቶ የአረማውያን ደሴት ትሆን ይሆን? እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እንኳን ልጇን እና ወዳጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ያዛ በምድረ ኢትዮጵያ ይልቁንም ዋልድባን በረገጡት እግሮቿ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የገባላት ምድር እውን ይሆን ይሆን? አዎ ዛሬ ዛሬ ብዙ ነገሮች መለወጣቸው የለመነውን ልመና ያልሰማን ሲመስለን፣ ይልቁንም የሃይማኖት አባቶቻችን ዝምታቸውን ሲያበዙ፣ መምህራን እና ዘማሪያን ድምጻውን ቢያጠፉ ይህች ርትዕይት ሃይማኖታችን አለሁ ባይ ብጣም በወጀብ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ በዙፋኑ አለ ብለን ለምናምነው ችግር እና መከራ ቢበዛም በመጨረሻ እኛ የምናምነው መድኃኒዓለም ክርስቶስ ቤተክርስቲያናችንን ገዳሞቻችንን ለአረማውያን አሳልፎ እንደማይሰጥ በጽኑ እናምናለን።

የዛሬ ሁለት ሳምንት ይሆናል የማይጸብሪ ወረዳ እና አውራጃ ነዋሪዎች እንዲሁም የወልቃይት አካባቢ ገበሬ ማኅበራት ገዳማችንን ዝም ብለን ሲጠፋ መመልከት የለብንም ከአባቶቻችን ጋር ሆነን እንጸልያለን አለያም እንሰዋለን በማለት ወደ ገዳመ ዋልድባ ለመሄድ የአካባቢውን የመንግሥት ባለ ሥልጣናት የጠየቁን፥ የማይጸብሪ እና ጸለምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መሪሳ ማንም ወደ ገዳሙ መሄድ አይችልም እንዲያውም እኛ እናስተካክላቸዋለን በማለት በትዕቢት ለአካባቢው ነዋሪዎች አቶ ሲሣይ ተናግሮ ነበር፥ ገዳመ ዋልድባ የአባቶች ብቻ አይደለም የዋልድባ ገዳም አባቶች ከእኛ በተሻለ ፍቅረ ክርስቶስን መርጠው ከአለም ተለይተው ለፈጣሪ ያደሩ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሁላችንም ሃላፊነት ናቸው በኃይልም ሆነ በእልህ የሚሰራ ሥራ የለም በማለት ነዋሪዎቹ ቢናገሩም አቶ ሲሣይ ግን


 • የዋልድባ ቤተሚናስ አባቶች በሙሉ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው
 • ለውጪ ዜና ማሰራጫ መግለጫ የሚሰጡትም ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው
 • / ገብረክርስቶስ መጥተው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸውየቀድሞው የዋልድባ አበሜኔት

አለበለዚያ ግንየቤተ ጣዕመ አባቶች የፈቀዱትን ልማት ማንም ሊከለክል መብት የለውምክልሉ የትግራይ ክልል ነው የአማራ ክልል አይደለም በማለት በትዕቢት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምተው ነበር።

የአካባቢው አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ትላልቅ አዛውንት ወደ ሰላሳ የሚጠጉ መንግሥት የሚያደርሰውን ፍራቻ ከቁም ነገር ሳይቆጥሩት እና ማስፈራሪያቸን እንደ ምርቃት በመቁጠር ለገዳማችን መብት ከአባቶቻችን ጋር እንቆማለን በማለት ወደ ገዳሙ ክልል ከትላንት በስቲያ ተጉዘው ነበር፤ በገዳሙ ቆይታቸውም ከገዳሙ አባቶች ጋር ውይይት በማድረግ ሊመጣ የሚችለውን እና በማንኛውም ጊዜ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ኦርቶዶክሳዊያኑ ከጎናቸው መሆናቸውን በማረጋገጥ በጋራ ወደፈጣሪ በማመልከት ነበር ያደሩት ነገር ግን ዛሬ አመሻሹ ላይ ወደ ፲፩ ሰዓት አካባቢ በአቶ ሲሣይ መሪሳ አዝማችነት በርካታ ታጣቂዎች እና ሚሊሻዎች ወደ ገዳሙ ዘልቀው በመግባት የአካባቢው ነዋሪዎችን እያሳደዱ በመያዝ ወደ ሦስት የሚሆኑ ሰዎችን አንጋቹቹ እያዳፉ እና እያንገላቱ ወደ እስር ቤተ ወስደዋቸዋል፥ በእስር ከተወሰዱት የሃገር ሽማግሌዎች መከከል የሦስቱን ስም አግኝተናል እነሱም
/ አቶ አለምሸት ሙሉ
/ አቶ ተክሌ /ኪዳን
/ አቶ አምባቸው የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ እነዚህ የሀገረ ሽማግሌዎች በሙሉ ገዳሙ የኢትዮጵያውያን ሃብት ነው፣ የአባቶች ግዴታ ሳይሆን የጠቅላላው ኦርቶዶክሳዊ ግዴታ ነው በማለት ነበር ወደ ገዳሙ ያመሩት ነገር ግን የደረሰባቸው ወከባ እና እስራት ይልቁንም የመንግሥት ባለሥልጣናት በመሆኑ ነገሮችን በሙሉ ከባድ ያደርገዋል።

በመሰረቱ መንግሥት ማለት የህዝብ ተወካይ ሁሉንም ማኅበረሰብ ወይንም ሰዎች በእሉልነት የሚያይ፣ ለዜጎች መብት የሚጨነቅ እያንዳንዱ ዜጋ የዜግነት ግዴታ እንዳለው ሁሉ የዜግነትም መብት እንዳለው መረዳት፣ ከዜግነት መብቶቹ መካከል የፈለውን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማድረግ መብት ሊኖረው ይገባ ነበር። መንግሥት የዜጎችን እኩልነት የሚያስከብር፣ በሃይማኖት መበላለጥ ሳይኖር በጋር ለሚኖሩባት ሃገር በጋራ የሚሰራ ህዝብን መምራት ሲሆን ነገር ግን የእኛ መንግሥት የፈለገው ካላደረገ ወይም እንዲሆን የማይፈቅዱ ዜጎችን በማሰር፣ በማሳደድ፣ በመግደል መብታቸውን መጣስ በሰውም በእግዚአብሔርም ነገ ያስጠይቀዋል።በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርምይላሉ አበው ዛሬ የገዛ ዜጎችን ማሰር እና ማንገላታት ነገ ምን እንደሚመጣ አይታወቅም እና እና አቶ ሲሣይ እና ግብራበሮቹ ነገን ቢመለከቱ ያሻላል፥ ዛሬ የተቀመጡበት ወንበር መሰበሩ አይቀርም እና ወገንን የመጠበቅ እና ቅርስን ከትውልድ ወደ ትውልድ የማስተላለፍን ታላቅ አደራ በእጅ ይዞ የአንድን ጎጥ ወይም ወንዝ አጀንዳ ይዞ ለማስፈጸም መሞከር በእውነቱ በታሪክም በፈጣሪም ያስጠይቃል እና ልብ ልንለው ይገባል እንላለን።

የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ ዛሬ ድረስ በወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ ሊሰራ ያቀዳቸውን እቅዶች ሲናገር ቆይቷል ነገር ግን ለህዝብ ይፋ ካደረጋቸው ፕሮጀክቶች መካከል
/ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ
/ የወልቃይት ፖርክ እና የመዝናኛ መዕከል
ብቻ ሲሆን እነዚህም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዋልድባ ገዳምን የሚነካ ሲሆን የገዳሙን ህልውናም የሚፈታተን ፕሮጀክት ናቸው፥ ነገር ግን መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያላደረጋቸው በርካታ ፕሮጀግቶች ቀርፆ ሙሉ ለሙሉ የገዳሙን ህልውና መንካት ብቻ ሳይሆን ሌላ ቦታ እንሰጣችሁና ሌላ ቦታ ትሄዳላችሁ በማለት መነኮሳቱን ሲያስፈራራ እና ሲያንገላታ የቆየበትን በርካታ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በእጃችን ገብቷል እና በቅርቡ የፕሮጀክቶቹን ዝርዝሮች እና ለታሪካዊውና ጥንታዊው ገዳመ ዋልድባ የታሰበለትን የታቀደለትን እጣ ፈንታውን በዝርዝር እናቀርባለን እና ተከታተሉን በቅርብ ቀን።
እስከዛው ቸር ወሬ ያሰማን

3 comments:

 1. "ክልሉ የትግራይ ክልል ነው የአማራ ክልል አይደለም በማለት በትዕቢት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምተው ነበር።"
  መንግሥት የዜጎችን እኩልነት የሚያስከብር፣ በሃይማኖት መበላለጥ ሳይኖር በጋር ለሚኖሩባት ሃገር በጋራ የሚሰራ ህዝብን መምራት ሲሆን ነገር ግን የእኛ መንግሥት የፈለገው ካላደረገ ወይም እንዲሆን የማይፈቅዱ ዜጎችን በማሰር፣ በማሳደድ፣ በመግደል መብታቸውን መጣስ በሰውም በእግዚአብሔርም ነገ ያስጠይቀዋል።“በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም”
  ............ይህ አጥፍቶ ጠፊነት ነውና................
  ዛሬ የተቀመጡበት ወንበር መሰበሩ አይቀርም እና ወገንን የመጠበቅ እና ቅርስን ከትውልድ ወደ ትውልድ የማስተላለፍን ታላቅ አደራ በእጅ ይዞ የአንድን ጎጥ ወይም ወንዝ አጀንዳ ይዞ ለማስፈጸም መሞከር በእውነቱ በታሪክም በፈጣሪም ያስጠይቃል እና ልብ ልንለው ይገባል እንላለን።

  ReplyDelete
 2. ድሮስ ከካድሬ ምን ይተበቃል?

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሄር ልብ ይስታችው

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤