Thursday, February 28, 2013

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ኾኑ!!!

የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – 70 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – 39 ድምፅ
BEMjDN4CMAAmQwj.jpg large
ተመራጩ ፮ኛ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ
(ፎቶ ተስፋ ዓለም ወልደየስ)

Monday, February 25, 2013

ማስታወቂያ ለ March 3, 2013 የጉባኤ መጥሪያታላቅ መንፈሣዊ ጉባኤ
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፭ .. (March 3, 2013)  
“. . .በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ. . .” ሉቃ. ፲፫ ፥ ፳፬

ትላንት ዋልድባ ታረሰ፣ ዛሬ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊፈርስ ነው፣ ነገስ . . . ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች፣ የዋልባ ገዳም ችግር እና በሌሎች ተያያዥ የቤተክርስቲያናችን ችግሮች ዙሪያ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ።

ቅድስት፣ ርትዕይት፣ ሐዋሪያዊት የሆነችው የተዋሕዶ ሃይማኖታችን በጌታችን በመድኅኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በዕለተ ዐርብ የተመሠረተች፣ በበዓለ ሃምሳ በርዕደተ መንፈስ ቅዱስ ያሸበረቀች እንከን የሌለባት ንጽህት ሃይማኖት ናት። ያለ ክርስትና የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይደለም ወርሶ ሊኖርባት በዓይኑ እንኳን ሊያያት አይችልም። “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።” ዮሐ. ፫ ፥ ፫ በመሆኑም ይህች ሃይማኖት በነፍስ ዘላለማዊ ሕይወት የምናገኝባት፣ ዘላለማዊ ደስታ የምንጎናፀፍባት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምንደርስባት በሥጋ ምድራዊ በረከት የምናገኝባት መንገድ ናት።
ለዚህም ነው ዓለምዓቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አንድነት፣ በቀድሞ ስሙ ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው በሴንት ፖል ሜኖሶታ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች፣ በዋልድባ ገዳም እየደረሰ ስላላው ችግር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ተጋባዥ መምህራንን ጋብዞ ለመነጋገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በየካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (March 3, 2013)  ጉባኤ አዘጋጅቷል። የእርሶ ተሳትፎ እምን ድረስ ነው? ለቤተክርስቲያንዎ ሊያበረክቱ የሚችሉትን ለመጠቆም ተዘጋጅተናል፣ ኑ! እንመካከር ቤተክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ከነሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍ አብረን እንስራ!

እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን በረደኤት ይጠብቅልን አሜን

        አድራሻው                              ቀንና ሰዓት
በሊኦ ኮሚኒቲ አዲራሽ          የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፭ .. (March 3, 2013)
320 University Ave. W                  5:00 - 8:00 PM. ወይም
St. Paul, MN 55103

ለተጨማሪ መረጃዎች በስልክ ቁጥር 
(612) 242-4928 
(612)702-0722 
(651) 208-1629
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Thursday, February 21, 2013

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሳንዲያጎ ካሊፎርኒያበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
‘‘የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ’’ መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ 20፤3
                          
                        በሀገራቸው ለስደት ለተዳረጉ ለገዳማውያኑ አባቶቻችን እንምከር

በዋልድባ ገዳማችን እና በመነኮሳት አባቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን የማጥፋት ዘመቻ ለመታደግ እንዲሁም በወቅታዊው  የቤተክርስቲያን ጉዳይ እንድንመክር የመወያያ መርሐግብር ተዘጋጅቱዋል፡፡በዚህ ታላቅ ዝግጅት ላይ በልማት ሳቢያ በዋልድባ ገዳምና መነኮሳቱ ላይ እየደረሰ ያለውን የማሳደድ ዘመቻ በምስል እና በድምጽ የተደገፈ መረጃና ማስረጃ እንዲሁም በቅርቡ ከኢትዮጵያ በመጡት የባህረ ሐሳብ ሊቅ መጋቤ ጥበባት በእምነት በአካል በተገኙበት ውይይት ይደረጋል፡፡ እርሶም በዚህ  የመወያያ መርሐግብር ተገኘተው ለቤተክርስቲያንዎ የሚሰማዎትን ይመክሩ ዘንድ ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ከቤተክርስቲያንዎ ጉዳይ የሚቀድም ነገር የለም፡፡በቤተክርስቲያን ጉዳይ ይሉኝታ አይያዝዎ፡፡በሰው በሰው ከሚሰሙ በአካል ይምጡና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በማግኘት     የቤተክርስቲያንዎ የመፍትሄ አካል ይሁኑ ዘንድ በዓለም አቀፍ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት 
                         የሳንዲያጎ ንዑስ ቅርንጫፍ አዘጋጅቷል፡፡

ለዘለዓለም የሚኖር የአባቶቻቸውን ድንበርና ርስት ለሚያፈርሱ ወዮላቸው!!! መጽሐፈ ሄኖክ  38፤17
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር    

አድራሻ፡- 4144 Campus AVE San Diego, CA 92116

ቀንና ሰዓት- እሑድ የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
(Sunday February 24, 2013) 330 PM ጀምሮ

ለተጨማሪ መረጃ- (619) 792-2048 
                      (619) 829-6199 
                      (619) 808-4605 
                      (619) 817-1378
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Friday, February 15, 2013

ዋልድባ በESAT ራዴዮ ዘገባ


በዋልድባ ገዳም እንግልቱ፣ እስራቱ፣ ሰሚ ማጣቱ የአካባቢው ባለጊዜዎች ያለ ርህርሄ ገዳማውያኑን  ማንገላታታቸውን ቀጥለዋል ኸረ ለመሆኑ ገዳሙን ይረሱ፣ ሸንኮራውንም ያልሙ፣ ግድቡንም ይገድቡ ሥራውን እየሰሩ አይደል? እነኝህን ለነፍሳቸው ያደሩትን መነኮሳት ምን እድርጉ እያሉ ነው ቀን ከለሊት የሚያሰቃዩአቸው? ኸረ ለመሆኑ ዋልድባ የመንፈሳውያን፣ የግዑሳን እና የስውራን ቦታ መሆኑ ተረስቶ ነው ዛሬ የወረዳ አስተዳዳሪ እንደፈለገ የሚሆነው? ግፍ አለ ነገ እግዚአብሔር የእጅን ይሰጣል ይሁን እነዚህስ ዛሬ ባለጊዜዎች ናቸው ነገ የማይመሽ  የሚመስላቸው ናቸው፣ እንደው ሌሎቹ በጎንደር ከተማ ቁጭ ብለው የቤተክህነት ሃላፊ ነን ባዩቹ ዓይን ያወጣ ውሸት ሲዋሹ ሰው ይታዘበናል አይሉም እንዴ? ልጆቻችን ምን ይሉናል አይሉም እንዴ? ኸረ እንዴት አይነት ዘመን ላይ ደረስን ጎበዝ. . . 

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Wednesday, February 13, 2013

ዛሬ መምህር ገ/ክርስቶስ፣ መምህር ወልደ ልዑል እና 6 መነኮሳት ለእስራት ተዳርገዋል“ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።” የያዕቆብ መልዕክት ፩ ፥ ፲፪

·         በጎንደር ከተማ የነበሩትን ገዳማውያን አስገድደው ወደ አዲርቃይ ለስብሰባ በሚል ተወስደዋል
·         መምህር ገብረ ክርስቶስን እና መምህር ወልደ ልዑልን ጨምሮ 6 መነኮሳት ለእስር ተዳርገዋል
·         ገዳማውያኑ የድረሱልን ጥሪያቸውን ዛሬም እያስተላለፉ ነው
 ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
አባ ገብረክርስቶስ ከዋልድባ መከኖሳት ጋር
ባለፍት ጥቂት ሳምንታት በዋልድባ ገዳም አካባቢ እየደረሰ ያለውን ፈተና እና ተያይዞም የክልሉ ባለሥልጣናት እያደረሱ ያለውን ኢ-ቀኖናዊ የሆነ ሥራ ለአንባቢያን ማድረሳችን ይታወሳል። ገዳማውያኑም ተባረው ገዳሙን ጥለው ለእርዳታ ጥየቃ ብሎም ለሚመለተው አካል አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ጎንደር ብሎም ባሕር ዳር በመሄድ ለአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ችግራቸውን፣ መገፋታቸውን፣ ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ በሰው ሰውኛ ለማስረዳት ሞክረዋል፥ በምላሹም ችግሮቹ ይስተካከላሉ፣ ከክልሉ አቻቸው አቶ ተወልደ የትግራይ ክልል ፕሬዘደንት ጋር ተነጋግረው መፍትሄ እንደሚሰጧቸው ተነግሯቸው ነበር፥ ሁኔታቹንም በቅርቡ እንደሚያሳውቋቸው ነግረዋቸው በጎንደር እንዲጠብቁ ነበር የተሰጣቸው መልስ፣ በጎንደርም በተመሳሳይ መልኩ ለሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ለሰሜን ጎንደር የጸጥታ ክፍል ሃላፊዎች ስለጉዳዩ ያለማሰለስ ለማስረዳት ሞክረዋል፣ አቤቱታቸውንም የአካባቢው ወጣቶች እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በየአካባቢያቸው የተቻላቸውን እያደረጉ እነኝህን በስደት ከባዕታቸው በግፍ የተባረሩትን አባቶች በረከታችሁ ይደርብን በማለት ሲንከባከቧቸው ቆይተው ነበር።

Monday, February 11, 2013

የመፍትሔ ያለህ! . . . ይላሉ ዛሬም አባቶቻችን!


·         የሰሜን ጎንደር ገዳማት ተወካዮች የዋልድባን አባቶች እልባት ካላገኘ ሌላ ችግር ይፈጠራል
·         አዲሱ ሹም በጎንደር የሚገኘውን የገዳሙብ ባንክ ዘግተን ወደ ሽሬ እናዞረዋለን ብለዋል
·         በማይጸብሪ አቶ ሲሳይ አዲሶቹን ሹሞች እና ጥቂት አባቶችን ለስብሰባ ተጠርተዋል
·         የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል በአዲርቃይ ስብሰባ እያዘጋጀን ነው ተብሏል
·         አራት የመነኮሳት ቡድን ወደ ባሕርዳር ለጥያቄ ተልከዋል
 ሙሉውን ቃል በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ንቡረዕድ ተስፋዬ ተወልደ
የሽሬ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
ባለፈው ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እየደረሰ ያለውን በገዳማውያኑ ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ድርጊት ስናስነብብ ቆይተናል፣ በዚህ በገዳሙ ዙሪያ እየደረሰ ያለውን ችግር ለመንግሥት ባለሥልጣናት አቤት ለማለት ወደ 40 የሚገመቱ የመነኮሳት እና መነኮሳይት ቡድን በጎንደር እንዲሁም በባሕርዳር ተገኝተው አቤቱታቸውን ማሰማታቸውንም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት መዘገባችን ይታወሳል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአካባቢው ባለሥልጣን አቶ ሲሣይ ማስፈራራታቸውንም፣ የወጡትንም መግቢያ እንደሌላቸው ጭምር በስልክ በመደወል ብሎም በተባባሪዎቻቸው ለገዳማውያኑ መልዕክታቸውን ሲያደርሱ ቆይተዋል። በዚህ ባሳለፍናቸው ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት አስቸኳይ እልባት ለገዳማውያን አባቶች ይሰጣቸው በሚል ለሽሬው አቻቸው የተማጥኖ ደብዳቤ መላካቸውንም አስነብበን ነበር፣ የሽሬ እንደሥላሴ ሃገረ ስብከትም በብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ የሚመራው በንቡረ ዕድ ተስፋዪ ተወልደ ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው ደግሞ “በሥራችን ጣልቃ አትግቡብን” በማለት መመለሱን እንዲሁም በዋልድባ ገዳም የተደረገውን ኢ-ቀኖናዊ የሆነውን የገዳሙን አባቶች ሹም ሽር አስመልክቶ በንቡረ ዕድ ተስፋዬ አማካኝነት ሹመቱን መቀበላቸውን እና ከሹመኞቹም ጋር አብረው እንደሚሰሩ ነበር ያስታወቁን።

Friday, February 1, 2013

ዋልድባ ገዳም በVOA ዛሬ February 1, 2013


ዋልድባ ገዳም በESAT February 1, 2013Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

የሽሬ እንደሥላሴ ሃገረ ስብከት የዋልድባ አበረንታንትን ሹመት አጸደቀ


“በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?” ፪ኛ ቆሮንጦስ ፲፫ ፥ ፭

·         አሥር መነኮሳት እና አሥራ አምስት ወታደሮች የመረጡት ምርጫ ተቀባይነት አግኝቷል
·         ከማይጋባ እና አዲርቃይ እቃ ቤተ ሃላፊዎች በአዲሶቹ ሹማምንቶች ተባረዋል
·         ንቡረዕድ ተስፋዬ ተወልደ የሽሬ እንደሥላሴ ሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ “ምርጫውን የሚቃወሙ ጸረ ልማት እና ጸረ-ሰላም ናቸው” አሉ
ባለፈው ጥር አስራ ሦስት ቀን አመሻሹ ላይ በግምት ወደ ፲፩ አካባቢ በዋልድባ አበረንታት የገዳሙን ሥርዓት እና ትውፊት ባልጠበቀ መልኩ እንዲያውም የቀበሌ ምርጫ በሚመስል መልኩ በዋልድባ አበረንታት ገዳም የወረዳ አስተዳዳሪው ባዘጋጁት መሠረት ወደ አሥር የሚጠጉ መነኮሳት ሊያውም የአንድ ብሔር ተወላጆች እንዲሁም ወደ 15 የሚጠጉ ወታደሮች በተገኙበት በቀጣይነት የዋልድባ አበረንታትን ገዳም ሊያስተዳድሩ የሚችሉ አበሜኔት እና እቃቤት ሹም ሽር ተደርጎ ነበር፤ ተዓምር ነው! በቁማችን የማናየው ጉድ የለም ዘንድሮ!