Tuesday, April 23, 2013

መናኝ ኃይለመለኮት ከእስር ተፈቱ


·         መናኝ ኃይለመለኮት ከእስር ተፈቱ፥ ነገር ግን በአስቸኳይ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው 
የጸሎታቸው በረከት ይደርብን
·         ከትንሳኤ በኃላ ከገዳሙ የሚባረሩ እንደሚኖሩም ተጠቁሟል
·         ማቄን ጨርቄን ሳትሉ ቦታውን ጥላችሁ ውጡልን
 በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  
ባለፈው አርብ እለት ማታ በተከሰተው በታጣቂዎች በማይለበጣ እናበዳንዶሮቃ ዘረፋ ከተፈጸመ በኃላ በቀጣዩ እለት ማለትም ቅዳሜ መናኝ ኃይለመለኮት የተባሉትን አባት ያለ ጥፋታቸው ወደ ማይጸብሪ በመውሰድ በእስር ላይ እንደነበሩ ይታወሳል። በእለቱ አሉ ተብለው ለእስር የዳረጋቸውም “ታጣቂዎች ይዘርፉናል፥ ታጣቂዎች የዳኙናል” በሚል ሰበብ እንደነበረ ዘግበን እንደነበረ ይታወሳል። በዚሁ እለትም በታጣቂዎች ተደብድበው የሕክምና እድል እንኳን ማግኘት ያልቻሉትንም አባ ፍቅረማርያምን እስከ አሁን ድረስ ደማቸውን ከሚጠራርጉላቸው ወንድሞቻቸው በቀር የረባ ሕክምና ወደ ማይጋባ ወስደን እናሳክም ብለው የጠየቁትን “አይመለከታችሁም አርፋችሁ ተቀመጡ” በማለት ማስፈራራት ደርሶባቸዋል፥ እኝህ አባትም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ምንም አይነት ህክምና ሳያገኙ መቆየታቸውን ስጋታቸው አባቶች ገለጸውልናል፥ ነገር ግን ከሰዎቹ ፈቃድ ውጪ ምንም ለማድረግ አለመቻላቸውም በእጅጉ አሳዝኗቸዋል።

Monday, April 22, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ችግር በVOA ራዴዮ ዘገባ


በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለዘመናት እየተንከባለለ የመጣው ችግር ዛሬም ለመመረቅ ጥቂት ወራት የቀራቸውን ደቀ መዛሙርት ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ ከቅዱስ ፓትሪያርኩ ጀምሮ እስከ ኮሌጁ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስን ጨምሮ ሁለት መምህራን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርት አያስተምሩም፣ ችግር አለባቸው ቢባሉም እኛ ያልነው ብቻ ልክ ነው በሚል፣ ይልቁንም ሌላ ተልዕኮ አላችሁ፣ የቀደመ የቤተክርስቲያን ትምህርት የላቸውም እና የመሳሰለውን ምክንያት በመስጠት ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ምክንያት መደርደር የሚወዱት የኮሌጁ የቦርድ አባላት እና የበላይ ጠባቂው ኮሌጅን ያህል የቤተክርስቲያኒቱን ትልቅ ተቋም እንደግል ቢሮአቸው በሰረገላ ቁልፍ ክርችም ካደረጉት ወራት ተቆጥረዋል። የደቀ መዛሙርቱን ችግር ለማዳመጥ ጆሮውን የሰጠ የኮሌጁ ዲን የለም፣ የበላይ ጠባቂውም በችግሩ ላይ ችግርን ጨምረው፣ የሚመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስም ዝም ብሏል፣ ምዕመናንም ዝም ብለዋል፣ ሁሉም ዝም ብለዋል በመካከሉ ግን ስውር ዓላማ ያላቸው ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ሌላ ተቋም ለመቀየር የሚጣጣሩት አካላት ተሳክቶላቸዋል፡፡ ነገ እነዚህ ደቀ መዛሙርት ተመርቀው ወጥተው ወልድ ዋሕድ ብለው የሚያጠምቁ፣ የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ይዘው ዓለምን በወንጌል ሊያዳርሱ የሚችሉ በሁለት ሰዎች ምክንያት ከ5000 በላይ የሚሆኑ ደቀመዛሙርት ለረሃብ፣ ለጥም፣ እና ለዕርዛት ተዳርገዋል። ኸረ የቤተክርስቲያን አምላክ በማለት ጩኸታቸውን እያሰሙ ባሉበት ወቅት የVOAው ዘጋቢ አቶ አዲሱ አበበ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቀደምት ተማሪ እና መምህራን ከነበሩ እንዲሁም በአሁን ሰዓት ችግር አለብን ብለው የሚጠይቁትን የደቀመዛሙርቱን ተወካይ እንግዶችን አነጋግሯል ከነዚህም መካከል 

በዋልድባ ገዳም ማይለባጣ እና ዶንዶሮቃ ላይ በታጣቂዎች ዘረፋ ተካሄደ

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  
·         ማይለበጣ ቤተ-እግዚአብሔር በታጣቂዎች ተዘረፈ
·         ዶንዶሮቃ ላይ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም ወፍጮ ቤትም በተመሳሳይ ታጣቂዎች ተዘርፏል
·         አባ ፍቅረማርያም የተባሉ አባት በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ በህክምና ላይ ናቸው
·         መናኝ ገብረመድኅን የተባሉ ስመ እግዚአብሔር ጠርተው ለምነው ከድብደባ ድነዋል
·         መናኝ ኅይለመለኮት የተባሉ አባት “ታጣቂዎች ዘረፉን፣ ደበደቡን፥ ታጣቂዎችም ሊዳኙን መጡ” ብለዋል በሚል ወደ እስር ቤት ተጥለዋል

እለቱ አርብ ሚያዚያ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ማታ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጭልም ድቅድቅ በሆነበት ሰዓት ላይ ማይለበጣ በሚገኘው ቤተ እግዚአብሔር ላይ በከባድ የሚሊተሪ ልብስ እና ትጥቅ የታጠቁ በግምት ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች በውጪ በረንዳ ላይ ተኝተው የነበሩትን መነኮሳት እና መናንያን ደብድበው እና ብዙ እንግልት አድርሰውባቸው ገንዘብ ያለው የት ነው ተናገሩ በሚል ብዙ እንግልት እና ድብደባ እንዳደረሱባቸው ከቦታው በደረሰን መረጃ መመልከት ችለናል። በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት ጽ/ቤቱን በሰደፍ ሰብረው ሲያበቁ በጽ/ቤት ውስጥ ያለውን ንብረት በመወርወር ሲያምሱ ቆይተው ምንም ባለማግኘታቸው ተበሳጭተው መነኮሳቱን ደብደበው እና አንገላተው ጥለው ወጥተው ለመሄድ ችለዋል።

Thursday, April 4, 2013

ESAT Radio በዋልድባ ገዳም አባቶች ዘገባ መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.


በርካታ መነኮሳት ማስፈራራቱን እና አፈናውን ፈርተው ከዋልድባ ገዳም ተሰደው በተለያዩ የሃገሪቱ ክልል በሚገኙ ገዳማት ተጠግተው እንደሚገኙ ይታወቃል። ESAT ራዲዮ በአንድ ገዳም ያገኛቸውን ገዳማዊ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል ይከታተሏቸው።
በዋልድባ ግፉም፣ እንግልቱም፣ አፈናውም እስሩም ቀጥሏል፤ እንደ ፈርዖን ልባቸውን ያደነደኑ የመንግሥት ተወካዮች እሚቢ አሻፈረን ይህንን ገዳም ሳናፈርስ አናቆምም በሚል ተግዳሮታቸውን ቀጥለዋል፣ እግዚአብሔርም ተዓምራቱን እያሳየ መልስ እየሰጠ በፈጣሪ ላይ የተከፈቱ አንደበቶች ልሳናቸው ተዘግቷል፣ በመድኅኒዓለም ላይ የተነጣጠሩ እጆች ተቆርጠዋል ታዲያ እንዴት ዓይነት ተዓምራት እንዲያሳየን ነው የምንጠብቀው ዛሬም የአባቶቻችን አምላክ ከእኛ ጋር እንደሆነ እየታየ ነው
የዋልድባ ገዳም ለብዙዎች ማረፊያ እንደሆነ ይቀጥላል
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በረደኤት ይጠብቅልን አሜን


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Tuesday, April 2, 2013

የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስ በማለታቸው የተነሳ ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ


·         የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስገነባቸው ያሰባቸው የስኳር ፋብሪካዎች
·         በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
·         የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
·         የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
·         የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
·         የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  

የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።