Wednesday, May 29, 2013

ቅዱስ ሚካኤል ታዓምራቱን በዋልድባ እያሳየ ነው


በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁበፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ። ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩-፳፪

·         በዋልድባ የሰራተኞች መኖሪያ የቅዱስ ሚካኤል እለት ንፋስ በቀላቀለ ንፋስ ተጠራርጎ ጠፍቷል
·         የዋልድባ መነኮሳት ማኅበረ ቤተ-ሚናስ ተወካዮች ቅዱስ ፓትርያሪኩን አነጋገሩ
·         “እኔ ጉዳዩን አላውቀውም፣ ከሌሎች አባቶች ተወይቼ መልስ እንሰጣችኋለን” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
·         በአፋር እና ትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኘው ታሪካዊ እና እድሜ ጠገብ የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ እሳት ተለኮሰበት፣ አንድ ቤተመቅደስ ተቃጥሏል ሌሎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል መነኮሳቱም ወደ ትግራይ ክልል መሪዎች አቤት ብለዋል

ዘገባውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ኢሮብ-ትግራይ
ኢሮብ ትግራይ

እለቱ ግንቦት 12 ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ነው በዋልድባ ገዳም ዙሪያ በተለይ በዛሬማ ወንዝ አካባቢ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት የሰፈሩት ሠራተኞች፣ መሃንዲሶች፣ የሥራ ተቋራጮች ብሎም ለዚህ ሥራ (ፕሮጀክት) ለማገዝ በአካባቢው ካምፕ ሰርተው ከሰፈሩ ወደ አንድ አመት ይጠጋቸዋል። እነዚህን ሠራተኞች ለማስቀመጥ በርካታ ቤቶች፣ የሚመገቡበት የምግብ አዳራሽ፣ ለሥራ ተቋራጮች እና ለማሀንዲሶች ቢሮዎችን በተጨማሪ ለሥራው የሚጠቀሙበትን መሳሪዎች የሚቀመጡበት መጋዘኖችን ጨምሮ ቦታው በርካታ ቤቶችን እና ትላልቅ መጋዘኖችን የያዘ በዛሬማ ወንዝ ሰሜን በኩል ኮረብታ ላይ የተከተመ ቦታ ነበር። “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩ አረማውያን በየዜው የጌታን ትዕዛዝ በመተላለፍ በቤቱ በድፍረት እና በትዕቢት የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ በቁጣው የተግሳጽ ድምፁን ሲያሰማ ቢቆይም አረማውያኑም ሊሰሙ አልቻሉም እግዚአብሔርም ትዕዛዛሩን በመልዕክተኞቹ በባለሙዋሎቹ እያስተላለፈ ነው ሰሚ ላለው፣ ልቡ ለተሰበረ በፈጣሪ አምላካችን እምነት እና ድህነትን ማግኘት የፈለገ የምሕረት አባት ነውና ሁሌም የጎበኘናል ነገር ግን የፈርዖን ልጆችን በባሕረ ቀይ ባሕር የበላ ዛሬም በየጉድባው ለሚጸልዩት አባቶቻችን መልሱን እየሰጠ ነው በለፉት አንድ አመት ብቻ መድኅኒዓለም ክርስቶስ በርካታ ታዓምራቱን በገዳሙ አካባቢ ስኳር እንመርታለን ያሉትን እድሜ ለንሰሃ እየሰጠ ሥራቸውን ግን እንደ ባቢሎን ግንብ እያመከነው ነው፥ ልክ ባቢሎናውያን አምላክን እናገኘዋለን ብለው ግንብ ሲገነቡ በመጨረሻ ድፍረታቸው ስለበዛ ቋንቋቸውን ቢቀላቅልባቸው እላይ ያለው ሲሚንቶ ሲጠይቅ አፈር ይዞለት ይመጣ ነበር በመሆኑም ሥራቸው መክኖ አምላክም ክብሩ የተገለጸበት ጊዜ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱሳችን ቁልጭ አድርጎ ይናገል፥ ዛሬም ፈጣሪ እለት ተእለት የሚሰለስበትን፣ የሚቀደስበትን ቅዱስ ቦታ ለማፍረስ እና ታሪክን እና የወገን ሃብትን ለማጥፋት የተግዳደሩትን ልክ እንደ ባቢሎናውያኑ ቋንቋቸው ባይጠፋም እርስ በእርስ መግባባት እስኪሳናቸው ድረስ ማድረግ የሚችል የሠራዊት ጌታ ዛሬም እነዚህን አረማውያን አንዴ በቁጣው ሲገስጻቸው፣ ሌላ ጊዜ ሥራውን ሊሰራ የመጣውን ካምፓኒ ሲያበረው ተግዳሮታቸውንም በድፍረት እና በማናለብኝነት እንደቀጠሉ ነው እውን እዳር ያደርሱት ይሆን እስቲ እናያለን።

Friday, May 3, 2013

ዋልድባ በታጣቂዎች እየታመሰ ነው፥ ለምን የሚል የቤተክሕነት ተወካይ ግን የለምገዳመ ዋልድባ ላለፉት 1600 ዓመታት ተከብሮ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ እኛ ላይ ደርሶ ነበር። በአሁን ሰዓት መንግሥት በልማት ሰበብ ሸንኮራ አለማለሁ፣ እምነበረድ ፋብሪካ አቋቁማለሁ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ እሰራለሁ፣ ወዘተ በማለት ልማት እያለ ታላቁን፣ ታሪካዊውን የኢትዮጵያ ሃብት ለማጥፋት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሕናት፣ ዲያቆናት፣ መነኮሳት፣ ቆሞሳት እና ጳጳሳት ምንጭ የሆነውን ገዳም ለማድረቅ እና ለማጥፋት ወገቡን ታጥቆ ከተነሳ ሰንበት ብሏል። ኢትዮጵያውያንም ለሃይማኖት የማይቆረቆር ግዴለሽ ትውልድ ሆኗል እና ዛሬ የመፍረስ እና የመበተን ፍርድ የተፈረደበት ገዳም ገዳማውያን ያለጥፋታቸው እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እንደወንጀለኛ ያለፍርድ በየእስር ቤቱ እየታጎሩ ይገኛሉ፣ ታዲያ ማነው ለምን ብሎ ሊጠይቅ የሚገባው እኛ አይደለንም እንዴ አንዱ በሬዲዮ "ገዳሙን አንነካም ብለዋል" ይለናል እነሱማ ሁሉንም ይላሉ አረማውያን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታን ሲሰቅሉት እኮ ምክንያት አበጅተው ነው ሕይወት የሚሆናቸውን ሰቀሉት ዛሬም የኛ ሰው ለመጪው ትውልድ ታሪክ ማጣቀሻ የሚሆነውን ብርቅ እና ድንቅ ገዳም ለማፍረስ ደፋ ቀና ይላሉ እውን እነዚህ ለኢትዮጵያ አሳቢዎች ናቸው?? ትልቅ ጥያቄ ነው ዛሬ ታሪኮቻችንን ቅርሶቻችንን እና ብርቅና ድንቅ የሃገራችንን ሃብቶች ቀስ በቀስ እያጣናቸው ነው ማን ይጠይቅ?
ትላንት የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት አፈረሱ እውን እቦታው ይመለስ ይሆን? ሁላችንም የምንመለከው እውነታ ነው
የሉሲ ቅሪት በጉብኝት ሰበብ በብዙ ሚሊዮን ብሮች ወጥታለች ትመለስ ይሆን?
እድሜ ጠገብ የሆኑት የብራና መጻሕፍት የወርቅና የብር መስቀሎች ከየገዳማቱ እየተዘረፉ ለገባያ ውለዋል ማን ይጠይቅ
ልብ ያለው ልብ ይበል

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!