Wednesday, May 29, 2013

ቅዱስ ሚካኤል ታዓምራቱን በዋልድባ እያሳየ ነው


በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁበፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ። ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩-፳፪

·         በዋልድባ የሰራተኞች መኖሪያ የቅዱስ ሚካኤል እለት ንፋስ በቀላቀለ ንፋስ ተጠራርጎ ጠፍቷል
·         የዋልድባ መነኮሳት ማኅበረ ቤተ-ሚናስ ተወካዮች ቅዱስ ፓትርያሪኩን አነጋገሩ
·         “እኔ ጉዳዩን አላውቀውም፣ ከሌሎች አባቶች ተወይቼ መልስ እንሰጣችኋለን” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
·         በአፋር እና ትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኘው ታሪካዊ እና እድሜ ጠገብ የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ እሳት ተለኮሰበት፣ አንድ ቤተመቅደስ ተቃጥሏል ሌሎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል መነኮሳቱም ወደ ትግራይ ክልል መሪዎች አቤት ብለዋል

ዘገባውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ኢሮብ-ትግራይ
ኢሮብ ትግራይ

እለቱ ግንቦት 12 ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ነው በዋልድባ ገዳም ዙሪያ በተለይ በዛሬማ ወንዝ አካባቢ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት የሰፈሩት ሠራተኞች፣ መሃንዲሶች፣ የሥራ ተቋራጮች ብሎም ለዚህ ሥራ (ፕሮጀክት) ለማገዝ በአካባቢው ካምፕ ሰርተው ከሰፈሩ ወደ አንድ አመት ይጠጋቸዋል። እነዚህን ሠራተኞች ለማስቀመጥ በርካታ ቤቶች፣ የሚመገቡበት የምግብ አዳራሽ፣ ለሥራ ተቋራጮች እና ለማሀንዲሶች ቢሮዎችን በተጨማሪ ለሥራው የሚጠቀሙበትን መሳሪዎች የሚቀመጡበት መጋዘኖችን ጨምሮ ቦታው በርካታ ቤቶችን እና ትላልቅ መጋዘኖችን የያዘ በዛሬማ ወንዝ ሰሜን በኩል ኮረብታ ላይ የተከተመ ቦታ ነበር። “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩ አረማውያን በየዜው የጌታን ትዕዛዝ በመተላለፍ በቤቱ በድፍረት እና በትዕቢት የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ በቁጣው የተግሳጽ ድምፁን ሲያሰማ ቢቆይም አረማውያኑም ሊሰሙ አልቻሉም እግዚአብሔርም ትዕዛዛሩን በመልዕክተኞቹ በባለሙዋሎቹ እያስተላለፈ ነው ሰሚ ላለው፣ ልቡ ለተሰበረ በፈጣሪ አምላካችን እምነት እና ድህነትን ማግኘት የፈለገ የምሕረት አባት ነውና ሁሌም የጎበኘናል ነገር ግን የፈርዖን ልጆችን በባሕረ ቀይ ባሕር የበላ ዛሬም በየጉድባው ለሚጸልዩት አባቶቻችን መልሱን እየሰጠ ነው በለፉት አንድ አመት ብቻ መድኅኒዓለም ክርስቶስ በርካታ ታዓምራቱን በገዳሙ አካባቢ ስኳር እንመርታለን ያሉትን እድሜ ለንሰሃ እየሰጠ ሥራቸውን ግን እንደ ባቢሎን ግንብ እያመከነው ነው፥ ልክ ባቢሎናውያን አምላክን እናገኘዋለን ብለው ግንብ ሲገነቡ በመጨረሻ ድፍረታቸው ስለበዛ ቋንቋቸውን ቢቀላቅልባቸው እላይ ያለው ሲሚንቶ ሲጠይቅ አፈር ይዞለት ይመጣ ነበር በመሆኑም ሥራቸው መክኖ አምላክም ክብሩ የተገለጸበት ጊዜ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱሳችን ቁልጭ አድርጎ ይናገል፥ ዛሬም ፈጣሪ እለት ተእለት የሚሰለስበትን፣ የሚቀደስበትን ቅዱስ ቦታ ለማፍረስ እና ታሪክን እና የወገን ሃብትን ለማጥፋት የተግዳደሩትን ልክ እንደ ባቢሎናውያኑ ቋንቋቸው ባይጠፋም እርስ በእርስ መግባባት እስኪሳናቸው ድረስ ማድረግ የሚችል የሠራዊት ጌታ ዛሬም እነዚህን አረማውያን አንዴ በቁጣው ሲገስጻቸው፣ ሌላ ጊዜ ሥራውን ሊሰራ የመጣውን ካምፓኒ ሲያበረው ተግዳሮታቸውንም በድፍረት እና በማናለብኝነት እንደቀጠሉ ነው እውን እዳር ያደርሱት ይሆን እስቲ እናያለን።

ከአራት ቀናት በፊት በቅዱስ ሚካኤል እለተ ቀን ነፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ዝናብ እና ነፋስ አማካኝነት በዛሬማ ወንዝ ኮረብታ ላይ ያሉትን ካምፕ ጠራርጎ ወደ ገደል ከቶታል፣ በእለቱም ምንም አይነት በህይወት ላይ የደረሰ አደጋ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል። እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው እግዚአብሔር አምላክ “ልብሱ እሳት፣ ቃሉ እሳት፣ እርሱ እሳት ነው ማንም ከፍጥረታት ወገን ወደእርሱ ሊቀርብ የሚችል ማንም የለም፥ ነገር ግን ምሕረቱ እና ቸርነቱ እሳቱን እያቀዘቀዘው በፊቱ ለመቆም ችለናል” ነበር ያለው አሁንም አረማውያኑን በእለቱ በጊዜው ከምድረ ገጽ ማጥፋት ሲችል በምሕረቱ እና ቸርነቱ ስለበዛ እድሜ ለንሰሃ ይሰጣቸዋል (የሚመለስ ካለ) ዛሬ በንብረታቸው በሥራቸው ያልተመለሰ ነገ ወደራሳቸው ካልተመለሱ ወየውላቸው እንላለን። ዛሬ በቅዱስ ሚካኤል እለተ ቀን የደረሰው የፈጣሪ ቁጣ ቢማሩበት እና ከመድኅኒዓለም ቦታ ላይ (ከዋልድባ ገዳም) ዘወር ቢሉ ይሻላል እንላለን፥ እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት የቅዱስ ሩፋኤል እለት በዛሬማ ወንዝ ላይ ሲሰራ የነበረውን ድልድይ እና የችግኝ ማፍያ የተሰራውን ግድብ በእለቱ ለበረከት የሚዘንበው ዝናም (ጸበል) ለእነሱ መዓት ሆኖባቸው የተሰሩትን ግድብ እና ድልድይ ጠራርጎ ወስዶ ታዓምራቱን አሳይቷል፣ ሌላው ገና የወልቃይት ሥኳር ፋብሪካ ጥናት የመጣው የመጀመሪያው ዲዛይን ኢንጂኔር የዋልድባን ምድር ከመርገጡ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፣ በተለያየ ጊዜ ከገዳሙ የሚወጡ አውሬዎች በርካታ ሰራተኞችን ለህልፈት አብቅተዋል፣ በዋልድባ ገዳም የዮርዳኖስ ጸበል ውስጥ በድፍረት የታጠቡ የሰራዊቱ አባላት (ታጣቂዎች) በእባጭ እና ተመሳሳይ በሽታዎች ተመተዋል፣ በመነኮሳት አባቶቻችን ላይ የድፍረት እጆቻቸውን ያነሱ ታጣቂዎች ሁለቱ ወዲያውኑ ለህልፈት ሲዳረጉ ሌሎች ደግሞ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ሆነው እስከ አሁን ድረስ በስቃይ እንደሚገኙ ይታወቃል፥ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ታዓምራት ትምህርት ካልሰጧቸው እነዚህ አረማውያን ነገ ምን እንደሚሆኑ መገመት የሚያዳግት አይመስለንም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋልድባ ገዳም በተለይም በማኅበረ ቤተ-ሚናስ እና ቤተ-ጣዕመ መካከል የነበረው ልዩነት ሳይፈታ ለዘመናት መቆየቱ ይታወሳል በገዳሙ ታላላቅ አባቶች ችግሮቹን ሊፈቱ ካለመቻላቸውም ባሻገር አገልግሎታቸው እንኳን በየተራ እስኪሆን ድረስ የደረሰ ትልቅ ልዩነት ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፥ ባለፉት ብዙ ዓመታት ከወረዳ ወደ አውራጃ ቤተክህነት፣ ከሃገረ ስብከት ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታው ቀርቦ የሃይማኖት ልዩነት አለን ችግሩን ሥር ሳይሰድ ፍቱልን ሃይማኖታችንን እየበረዙት ነው በማለት በተለይም የማኅበረ ቤተሚናስ በተለያየ ጊዜ ከወረዳ ቤተክህነት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ብሎም ቅዱስ ፓትርያሪኩ ድረስ ቢደርስም ለነገሩ ቦታ ባለመስጠት ወይንም እኛ ምን አገባን በሚል አስተሳሰብ ነገሩ ሲንከባለል ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሩ ሁሉ እየተካረረ እስከ መጠላላት ደርሰዋል። በዋልድባ አበረንታት ገዳም ሁለቱም ማኅበራት የሰርክ አገልግሎታቸውን እንኳን ለየብቻ እንዲፈጽሙ ነበር ቆየት ያሉት የሲኖዶስ አባላት የወሰኑት፥ እግዚአብሔር ያሳያችሁ በሃይማኖት መወሰን የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን ሆኖ ሌላ አካል መጥቶ ውሳኔ የሚሰጥ እስኪመስል ድረስ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ባለመወሰኑ እንዲሁ በእንጥልጥል ዘመን ተሻግሮ የመጣ ችግር እንደሆነ ቆየት ያሉት አረጋውያን አባቶች እናገራሉ። ጥንት በአፄ ዘርዓያቆብ ዘመን “ቅባት እና ቅድስት” በሚል ኦርቶዶክሳውያኑ ተለያይተው ነበር ይባላል፥ ብልሁ መሪ አፄ ዘርዓያቆብ ችግሩን በጊዜው የፈቱት ቢመስልም ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ እንዳለ ለዚህም ብቸው የችግሩ ፈቺ እና ፈራጅ ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ ነገሩን ወደ ጎን በመተው እስካሁን አለ። ዛሬ ይሄ ለምን መጣ የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ስለሚችል ወደሚቀጥለው ርዕሳችን እንሄዳለን።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዚሁ በቤተ - ሚናስ እና በቤተ - ጣዕመ ማኅበራት መካከል ያለውን ልዩነት የማይጸብሪ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለማየት ሞክሮ ነበር ነገር ግን ችግሩ ከአቅማችን በላይ ነው፣ እኛ ልንመለከተው አንችልም በማለት ከአባሪ ደብዳቤ ጋር የሁለቱንም ማኅበራት አምስት አምስት ተወካዮች ተደርገው ቅዱስ ፓትርያሪኩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ለማነጋገር ከየማኅበሮቻቸው ደብዳቤ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ያመራሉ ባለፈው አርብ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ ቢደርሱም ቅዱስ ፓትርያሪኩን ለማግኘት ባለመቻላቸው ለሰኞ ማለትም ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ. ም. ገብተው ቅዱስ ፓትርያሪኩን በጉዳዩ ላይ ሊያነጋግሯቸው ችለዋል በጣም የሚገርመው በውይይቱ ላይ የቤተ - ጣዕመ ተወካዮች ሊገኙ አለመቻላቸው ግን ብዙዎችን አስተርሟል ቅዱስ ፓትርያሪኩም በመልሳቸው (bulet dodge) እንደሚባለው ለማምለጫ ምክንያት ሳይሆናቸው እንዳልቀረ ይገመታል፣ ቅዱስ ፓትርያሪኩም እንደመለሱት ከሆነ “እኔ ጉዳዩን አላውቀውም፥ አሁን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አለብኝ እና ከሌሎች አባቶች ተማክሬ ውሳኔያችንን እናሳውቃችኋለን” በማለት የመጡትን የቤተ-ሚናስ ተዋካዮች ለመመለስ ሞክረው ነበር። የቤተ-ሚናስ ተወካዮችም እኛ እና እነሱ ልዩነታችን የሃይማኖት ነው ይሄ ደግሞ አስቸኳይ ውሳኔ ያሻዋል የቤተ-ጣዕመ መነኮሳት የሚያምኑት ዘጠኝ መለኮት አለን ብለው የሚምኑ ናቸው ለዚህ ምስክራችን ደግሞ “ሚስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት” የተሰኘውን መጽሐፍ በእነዚሁ አባቶች የተጻፈው ነው ደጋግመን ለቅዱስ ሲኖዶስ መልስ ይስጥበት በማለት ለዘመናት ስንወተውት ቆይተናል አሁንም ቢዘገይም አልመሸም እና የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጠቅም አበክረው ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር እና ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው ታው እና እድሜ ጠገቡ የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ የተለኮሰ የእሣት ቃጠሎ እንደደረሰበት የገዳሙ መነኮሣትና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። በመነኮሳቱ ላይ ድብደባ መፈፀሙንም VOA ዘገባ ገልጿል። ድርጊቱ ያስቆጣው በመቶዎች የቆጠሩ መነኮሳት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ሰኞ፣ ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ወደ መቀሌ ተጉዞ በተወካዮቹ አማካኝነት ለክልሉ መንግሥት ፕሬዘዳንት ቢሮ አቶ አባይ ወልዱ አቤቱታቸውን ማሰማታቸውን ከአካባቢው ተዘግቧል የአባላ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ አካባቢው የፖሊስ ኃይል መላኩን አስታውቋል። ለለፉት አስር ዓመታት በርካታ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ይልቁንም የሊቃውንት መፍለቂያ ብሎም ለታላቋ ሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ሥልጣኔዎችን ለምሳሌ: ስነ-ጹሁፍ፣ ስነ-ስዕል፣ ስነ-ሕንጻ፣ ስነ-ምግባር እንዲሁም የሀገሪቱን መተዳደሪያዎች ጨምረሮ በርካታ መመሪያዎችን ያበረከቱ ገዳማት ገዳማት ዛሬ ዛሬ እንደዋዛ ተቃጠሉ፣ በቦታውም በርካታ ቅርሶች ተመዘበሩ፣ ገዳማውያኑም ተደበደቡ፣ ተሰደዱ፣ እና የመሳሰሉት ዜናዎች እየተለመዱ መጥተዋል። ለሃገሪቱ ያበረከቱት ታላቅ አስተዋጽዖ ቀርቶ የሀገርን እና የወገንን ታሪክና የታሪክ ቅርሶችን ይዘው በመገኘታቸው ለሃገሪቱ በየዓመቱ በርካታ የውጪ ምንዛሬዎችን ማስገኘታቸው ሊዘነጋ አይገባውም ነበር፥ ነገር ግን ምንም አስተዋጽዖ እንደሌላቸው እና ምንም እንዳላበረከቱ በተለያዩ ወራሪዎች ሲቃጠሉ፣ መነኮሳቱ ሲደበደቡ፣ ቅርሶቹ ሲመዘበሩ እነዚህን ሃገራዊ ቅርሶች የመጠበቅ እና የመንከባከብ ሃላፊነት የመንግሥት ሆኖ ሳለ ነገር ግን መንግሥት በአንዳንድ ቦታዎች ተባባሪ በመሆን እነዚህን በርካታ የሀገሪቱ ቅርሶች ሲቃጠሉ እና ሲዘረፉ አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሚገኝ ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ ከነዚህም መካከል በዋናነት መንግሥት ካልጠፋ ቦታ እነዚህ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት ባለበት ቦታ ሁሉ ሀገርን አለማለው በሚል ሰበብ የሀገርን ቅርስ እና ሃይማኖትን ሲያጠፋ እየታየ ነው ለዚህም ዋቢ የሚሆነን ዋልድባ ገዳም ላይ መንግሥት የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን እገነባለው በማለት በእልከኝነት ተግዳሮቱን እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ቢቀጥልም ነገር  ግን በመድኅኒዓለም ቸርነት ገዳሙ አካባቢ ምንም መስራት ሳይችሉ ቀርተዋል እንደውም አሁን አሁን በየዜና ማሰራጫው ሁሉ በጀት አንሶን ነው፣ ማስተር ፕላኑን ሪቫይዝ እናረጋለን በሚል የማስተባበያ ቃላት ቢሰሙም ከአማኙ በላይ እግዚአብሔር ለቤቱ ቀናዒ የሆነ አምላክ እንደሆነ እናምናልን በመሆኑም የዛሬ ባለጊዜዎች ታሪክን እና ሃይማኖትን ለማጥፋት ቢሞክሩም ዮዲት ጉዲት እንኳ አርባ ዘመን ሞክራ አለመቻሏን ሊገነዘቡት ይገባል እንላለን። እግዚአብሔርም ከንቱ ምኞቻቸውን እና ግብራቸውን ተመልክቶ የእጃቸውን እንደሚያገኙ የታወቀ ነው ያም ቢሆን እንኳ ዛሬ የንሰሃ እድሜ ለሁላችን ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቶናል እና ስንበድለው የነበረውን ሕዝብ እና ንጽሕይት እና ርትዕይት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይቅርታ ብለው ወደ በጎ ምግባራቸው ቢመለሱ የተሻለ ነው እንላለን።


ለሁሉም ቸር ይግጠመን እያልን እንሰናበታለን
ወስብሃት ለእግዚአብሔር


Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

4 comments:

 1. Amlakachin temesgen heylachin anteneh, esun yeyaze manis yafral, mechereshawun asamirlin amen!!!

  ReplyDelete
 2. ለመድኃንያለም ምን ይሳነዋል?

  ReplyDelete
 3. ቀናዒ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶSaturday, June 1, 2013 at 5:11:00 AM EDT

  እግዚአብሔር በአንድም በሌላም እየሰራ ነው እኛ ግን የድርሻችንን እንደመወጣት ተኝተናል። ሌላው ስለሃይማኖቱ ይታገላል። እኛ ግን ይሄ ሁሉ መከራ በቤተክርስቲያናችን ላይ እየደረሰባት እንደማይመለከተው ሰው ዝም ብለናል ፤ የዋልድባ አባቶች ገዳሙን ለመታደግ ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ በሃገራቸው ተሰደዋል። መንግስት ይህ አልበቃ ብሎት ገዳማውያኑን እያሳደደ ነው ገዳማውያኑ ይህንን ሁሉ መከራ ሲከፍሉ እኛ ግን ተኝተናል። ገዳማውያኑ የእህል ዘር ያልሆነ እንስሳ እንኳን የማይቀምሰውን ቋርፍ ያውም በቀን አንድ ጊዜ እየቀመሱ በፆምና በጸሎት የደከመ ገላችውን በፌደራል ፖሊስ ዱላ ሲደበደቡ እኛ ለደለበ ሥጋችን ምን አሳሳን? ገዳማዊያኑና የአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያኖች ሲታሰሩ እኛስ ለመታሰር ምን አሳሳን? ቤተክርስቲያን የነሱ ብቻ ናትን? ወግኖቼ እስከመቼ ነው የምንተኛው? ገዳማችንን አትንኩብን ቤተክርስቲያናችንን አታቃጥሉብን ሃይማኖታችንን አታጥፉብን ብለን በመነሳት ቤተክርስቲያናችንን መታደግ አለብን። እንደ ዋልድባ አባቶች መልካሙን ገድል መጋደል አለብን።
  በ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፮፥፩፪ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። የተባልነውን እንተግብር ዋልድባን ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያናችንን ለመታደግ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተቋቋመው ይህ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድነት የተባለው ማህበር በውጭ ሃገር የምንኖረውን የተዋህዶ ልጆች ለቤተክርስቲያን እንድንቆም እያሰባሰበን ነው። እስከዛሬ እንዲህ አይነት መልካም ተጋድሎ ለመጋደል የተቋቋመ ቀርቶ የሞከረም የለም። ስለዚህ በርቱልን የበለጠ ቀስቅሳችሁን አደራጅታችሁን ለቤተክርስቲያናችን አጥር ቅጥር እንድንሆናት አድርጉን። በተለይ የሃገርቤቱን ሕዝበ ክርስቲያን አግኝታችሁና አደራጅታችሁ ሁለቱን ማለትም በሃገር ቤትና በውጭ ያለውን ሕዝብ በማደራጀት ለእናት ቤተክርስቲያናችን እንድረስላት። እግዚአብሔር ያበርታችሁ። በርቱ በርቱ።

  ReplyDelete
 4. ከምንም በላይ ተሰምቶኛአል፣የዋልደባ መታረስ ፣ዉድ የሆናችሁ እና የተከበራችሁ ክርስቲያኖች በሙሉ ዝም ብለን የምናሣልፍበት ምክንያት ምንድነው ሁሉም ክርስቲያን በመቆርቆር ሰላማዊ ሰልፍ የማያደርግ ምን ሆኖ ነው ፣እባካችሁ እግዚአብሔርን
  መከታ በማድረግ እንነሳ ።እኛ ክርስቲያኖች በስንቱ እንበደል ፤ኧረ በዛ የእኛ መብት የማይከበርስ ፡እንደሌሎች
  ሔንሀይማኖቶች በነቂስ ብንወጣስ ምን አለ፡ኧረእባካችሁ፦ቆይ ወጣቱ ፥ማህበረ ቅዱሳን ምን ትሰራችሁ ዽሮ ያላጣነወን
  ይዞታ ዛሬ ሁሉ ራሱን ባወቀበት ሰአት እንዴት ይዞታችን እናጣለን ፡አያሳፍርም፡ለማንኛዉም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን፡አሜን።

  ReplyDelete

እግዚአብሔር ያክብርልን ስለ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መልሰን እናገኝዎታለን፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፤