Friday, June 28, 2013

ደቀ መዛሙርቱ የማስገደጃ ርምጃዎችን በመውሰድ የአስተዳር ሕንጻውን ከበውና ቢሮዎቹን ዘግተው አረፈዱ

  • ቋሚ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል
  • ‹‹በኀይል ላይ ኀይል ጨምሬ እጠብቅሃለኹ›› /ዘላለም/
  • ‹‹መናፍቅን ማውገዝ እንጂ ሥልጣን መስጠት አይገባም›› /ደቀ መዛሙርቱ/
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የኮሌጁን አስተዳደር ሕንጻ በመክበብ የማስገደጃ ርምጃዎችንCollege bld 01 መውሰድ መጀመራቸው ተገለጸ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ዛሬ፣ ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከማለዳው 12፡30 ጀምሮ የአስተዳደሩን ሕንጻ መግቢያና ዙሪያ መተላለፊያዎቹን በመክበብ መምህራኑና የቢሮው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንዳይገቡ ሲከላከሉና ቀደም ብለው የገቡትንም በትእዛዝ ቃል ሲያስወጡ መታየታቸው ተዘግቧል፡፡
‹‹ከማለዳው 12፡00 ላይ በመኝታ ክፍሎቻችን ኮሪዶሮች የፊሽካና የጭብጨባ ድምፅ ተሰማ፤ ከክፍላችን ስንወጣ ወደ አቡነ ጢሞቴዎስና ሌሎች መምህራን ቢሮ የሚያስገባው የሕንጻው ደረጃና መተላለፊያ በከፍታ ድምፅ በሚዘምሩ ተማሪዎች ተዘግቶ ነበር፤›› ያለ አንድ የተቃውሞው ተካፋይ የቢሯቸውን ቁልፍ ጥለው የሸሹ ሓላፊዎች እንደነበሩ ተናግሯል፡፡

Wednesday, June 26, 2013

IUEOTCFF በዋልድባ ገዳም እና ገዳማውያኑ ላይ የሚደርሰውን እንግልት በመቃወም መግለጫ አወጣ


ሙሉውን የpress release ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኢትዮጵያ መንግሥት በዋልድባ ገዳም እና አካባቢው ላይ እያደረሰ ያለውን ችግር፥ በገዳማውያኑም ላይ በተለያዩ ጊዜያት እንግልት፣ እስራት፣ ስደት ሲደርስባቸው ቆይቷል እስከ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው። የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ማቅረቡ ይታወሳል። ባለፈው ጥቂት ሳምንታት በዚሁ በገዳሙ ዙሪያ እየደረሰ ያለውን ችግር ከተለያየ ቦታዎች አቤቱታ በመቅረቡ ይመስለናል የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው በማለት የራሱን ሰዎች ልኮ የገዳማውያኑን ችግር እመለከታለሁ፣ ችግሩንም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንፈታዋለን በማለት ሐሰተኞችን አሰባስበው ሲያበቁ፥ በፕሮጀክቱ ዙሪያ ምንም ለውጥ እንደማይኖር እና ገዳማውያኑም አርፈው እንዲቀመጡ፣ ከውጪ ሚዲያዎች ጋር ግንኙነት እንዲያቆሙ፣ መቀመጥ ያልቻለ ገዳሙን ጥሎ መውጣት እንደሚችል ነገር ግን
መመለስ እንደማይቻል እኒሁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ባዮች ሲደሰኩሩ ውለው ተመልሰዋል።

IUEOTCFF እንደተቋም የኢትዮጵያ መንግሥት እያደረገ ያለውን ሥራ እንዲያቆም፣ ታሪክን እና ቅርስን ከማጥፋት እንዲገታ፣ (ነገ ከተጠያቂነት ማምለጥ ስለማይቻል)፣ ገዳማውያኑን ማንገላታትን እና ማሰደድን በአስቸኳይ እንዲያቆም በማለት ለዛሬ ሰኔ ፲ ቀን ቀን ፳፻፭ ዓም መግለጫ በማውጣት ቁጣችንን እና ሐዘናችንን እንገልጻለን።

በመላው ኢትዮጵያ የምንገኝ ለሃገር እና ለሕዝብ ተቆርቋሪ የሆንን ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች፣ የሲቪክ እና ማኅበራዊ ተቋማት በሙሉ በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ሃይማኖት የማጥፋት እና ቅርስን የመዝረፍ ሥራ ተመልክተን በዝምታ መቀመጥ ከታሪክ ወቀሳ፣ ከኅሊና ፍርድ ይልቁንም በመጪው ትውልድ ከመወቀስ እና ከመከሰስ፤ ከፈጣሪም ፍርድ ለማምለጥ በምንችለው መንገድ የተቻለንን ተጽዕኖ እንድናሳድር አደራ በማለት በትህትና እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ሃገራችንን እና ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን በረደኤት ይጠብቅልን አሜንLet's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Sunday, June 9, 2013

የገዳማውያኑን አቤቱታ ለመስማት አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ዛሬ ወደ ዋልድባ ይገባል  • በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
  •      አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን የዋልድባ አባቶችን ለማነጋገር ወደ ወልድባ ከትላን በስቲያ ወደዚያው በማምራት ላይ ናቸው
  • ·        አቶ ሸዊት የማይጸብሪ የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ ለአባ ገብረሕይወት መስፍን ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል
  • ·        ነገ የሚገባው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግሩፕ የሚያነጋግረው እነ አቶ ሸዊት እና አባ ገብረሕይወት ያዘጋጇቸውን የሐሰት መነኮስት ቡድን ነው
  • ·        እስከ አሁን ድረስ ከስድሳ በላይ መነኮሳት ከዋልድባ ገዳም በግፍ ተግዘው በተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት ተሰደው ይገኛሉ
  • ·        እነ አባ ገብረሕይወት ሶስት የጎጠኛው ቡድኖችን ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግሩፑ መልስ እንዲሰጡ አዘጋጅተው እየጠበቁ ነው