Tuesday, July 23, 2013

አቡነ ጢሞቴዎስ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊነት ተገለሉ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ኮሌጁን በጊዜያዊ ሓላፊነት እንዲመሩ ተመድበዋል

 • አቡነ ጢሞቴዎስ ጉዳያቸው ከሚታይበት ስብሰባ ላለመውጣት ሲለመኑ ውለዋ
 • ፓትርያሪኩ ስለ አቡነ ጢሞቴዎስ ብዙ ከመናገር ተጠንቅቀዋል፤ ተቆጥበዋል
 • ደቀ መዛሙርቱና መምህራኑ ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር እየገለጹ ነው
 • የቦርድ አባላቱ በሲኖዶሱ ፊት ያሰሙት ያልተጠበቀ ምስክርነት አስተዳደሩን አጋልጧል
 • የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ቅ/ሲኖዶሱ መመሪያ ሰጥቷል
 • የንቡረ እድ ኤልያስ ምደባ ከሚያስነሣው ግዙፍ ጥያቄ ጋራ የምረቃው ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል..
His Grace Abune Timothy
ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ
ላለፉት 14 ዓመታት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን በበላይ ሓላፊነት ሲመሩ የቆዩት ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ ከሥልጣናቸው እንዲገለሉ ቅዱስ ሲኖዶስ መስማማቱ ተገለጸ፡፡

Thursday, July 18, 2013

ዜና ብሥራት ዘሥላሴ! ሐኬተኛው እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ወሰነ!

 • መ/ር ፍሥሐ ጽን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ
 • የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው
 • የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሌጁ አስተዳደርና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ላለፉት ስድስት ወራት እየተባባሰ የመጣውን ውዝግብ ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ከኮሌጁ መምህራንና የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች ጋራ ከመከረ በኋላ ነው፡፡
ትላንት እና ዛሬ ቋሚ ሲኖዶሱ በወቅታዊ የኮሌጁ ኹኔታ ላይ ሲያካሂድ በዋላቸው ተከታታይ ስብሰባዎች፣ አጣሪ ኮሚቴው የኮሌጁንአካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ይዞታ ለማሻሻል ከአጭር እና ረጅም ጊዜ አኳያ በመፍትሔነት ያቀረባቸውን የውሳኔ ሐሳቦች መርምሯል፡፡ በዚህም መሠረት በኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት ቅሬታ ከቀረበባቸው መካከል አንዱ የኾነውና ተደራራቢ ሓላፊነቶችን የያዘው ዘላለም ረድኤት ከሐላፊነቱ መነሣት እንዳለበት ተስማምቷል፡፡
በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ዘላለም ረድኤት ‹‹መምህር፣ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽንና የአስተዳደር ጉባኤ አባል›› ነበር፡፡ በሐኬተኛውና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ላይ የታዩበትን ጉድለቶችና ድክመቶች ኮሚቴው በሪፖርቱ ገጽ 14 ላይ  እንደሚከተለው ዘርዝሮታል፡-

Tuesday, July 16, 2013

የቤተክርስቲያን ፈተናዎችLet's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!

ዋልድባ በቪኦኤ July 2, 2012Let's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!

ESAT RADIO Feb 14 2013Let's save waldba! togetherዋልድባ እንታደግ!

Monday, July 15, 2013

ሰበር ዜና - ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ

የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ምድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል
·  ደቀ መዛሙርቱ በቀጣ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው
በዘረኝነት እና በጎሰኝነት ታንቆ የተያዘው የቅ.ሥ.መ.ኮ. የመዘጋት ፍርድ ተበየነበት! ያሳዝናል! ! ! ! 

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡
ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ ፰ እስከነገ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ››ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

‹‹የቀኑ ትምህርት የተቋረጠ መኾኑን ስለማሳወቅ›› በሚል በቁጥር ል/ጽ/445/339/05 በቀን 8/11/05 ዓ.ምበፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ ተፈርሞ በአድራሻ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተላከው ይኸው ደብዳቤ፣የቀኑ መርሐ ግብር የተዘጋው ከኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከተመረመረ በኋላ መኾኑን አስታውቋል፡፡

ምእመኑ በቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲኾን ደቀ መዛሙርቱ ጠየቁ

 • በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
 • አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል
 • የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው

St Trinity College Disciples demonstrating at the gate of the Patriarchate
ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር በተቃውሞ ትዕይንት ላይ
ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡

የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት በዛሬው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል ላይ ለመጣው ምእመን ተቃውሟቸውን የገለጹባቸው ኀይለ ቃሎች

image417
 • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!
 • ልጆቹን የማጠይቅ አባት አለን?
 • ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!
 • የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ!
 • ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳)
 • ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን!
 • የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን!
 • ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ!
 • ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው ሊበረታታቱ እንጂ ሊባረሩ አይገባም!
 • ከአየህጉረ ስብከቱ ቤተ ክርስቲያንን አምነን ወጥተን ለረኀብ ተጋለጥን፡፡
 • ኮሌጁ በመዘጋቱ ከተመገብን ሰባተኛ ቀናችን ነው፡፡
 • አቤቱ የኾነብንን አስብ፡፡
 • ኮሌጁን የሚዘጋው የከፈተው ሲኖዶስ ነው፡፡
 • ኮሌጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የግለሰቦች አይደለም!
 • እውነትን ሙስና አይደለም መቃብር አያሸንፈውም!
 • ጌታ ሆይ፣ ከመቅደሳችን ውስጥ የሙስናን እሾኽ ንቀል!
 • እየሞትንና እየተራብን ሙስናንና ዘረኝነትን እንቃወማለን!
 • ሙስና ከቤተ ክርስቲያናችን ይወገድ!
 • ከሓላፊነት መሸሽ በራሱ ሙስና ነው!

Thursday, July 11, 2013

ፖሊስ ደቀ መዛሙርቱን ከኮሌጁ ግቢ እንዲያስወጣ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ጠየቀ፤ የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ውሳኔውን በጽኑ ተቃውመዋል


 • ኮሌጁ እንዲዘ የውሳኔ መነሻ የሰጠው ከአቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ያልወጣው የኮሌጁ ቦርድ ነው
 • የኮሌጁ ምግብ ቤት አገልግሎቱን እንዲያቆም በመታዘዙ ደቀ መዛሙርቱ ምሳና ራት ተከልክለው ውለዋል
 • አቤቱታቸውን ለመንግሥት አካላት ያሰሙት ደቀ መዛሙርቱ ‹‹ቅ/ሲኖዶስ እና ምእመናን የከፈቱት ኮሌጁ የሚዘጋው በመቃብራችን ላይ ነው!›› በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል፤ በአስተዳደር ሕንጻው ዙሪያ የሚያደርጉትን ቁጥጥር አጠናክረዋል
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የፌዴራል ፖሊስ ኀይልን እገዛ መጠየቁ ተገለጸ፡፡
በልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ስም ተፈርሞ የወጣውና ለፌዴራል ፖሊስ እንደተጻፈ በተገለጸው ደብዳቤ÷ ልዩ ጽ/ቤቱ የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በሰላም ነሽነት በመወንጀል ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን ያስታወቀ ሲኾን በዚህም መሠረት ፖሊስ ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው የሚወጡበትን ርምጃ እንዲወስድ እገዛ መጠየቁ ታውቋል፡፡
የልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ የተጻፈው በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ የሚነገረውና በደቀ መዛሙርቱ የችግሩ አካል ተደርጎ የሚተቸው የኮሌጁ ቦርድ ኮሌጁ እንዲዘጋ በሰጠው የውሳኔ መነሻ መኾኑ ተነግሯል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በአቡነ ገሪማ የበላይ ሓላፊነት የሚመራው የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የቦርዱን መነሻ በመቀበል ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑንና ደቀ መዛሙርቱም ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መጠየቁን በጽኑ ተቃውመዋል፡፡
ፓትርያሪኩ ኮሌጁን የመዝጋት ሥልጣን እንደሌላቸው የገለጹት የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሓላፊው ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ‹‹በኮሌጁ ላይ ለመወሰን ሙሉ ሥልጣን ያለው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነው፤›› በማለት በመንበረ ፓትርያሪኩ ስምምነት በተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ተግባራዊ እንዲኾን ተሟግተዋል፡፡ ከኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ጋራ የሚስማማው ይኸው የብፁዕነታቸው አቋም ከፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጋራ በትይዩ እንዳቋማቸውና የከረረ ውዝግብ ውስጥ እንደከተታቸው ተዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ አኳኋን አምስት አባላት የሚገኙበትን አጣሪ ኮሚቴ በተወካዩ አማካይነት በሰብሳቢነት የመራው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ኮሌጁ እንዲዘጋ ያስተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ኮሚቴው አጣርቶ ያቀረበውና ፓትርያሪኩም እንደተስማሙበት የተመለከተው የመፍትሔ ሐሳብ ተፈጻሚ እንዲኾን መጠየቁ ተሰምቷል፡፡
Source: Hara Zetewahedo
Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያርኩ ቅጽር የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው

Board members of the college
 • ፖሊስ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ አነጋግሯ
 • ‹‹ከሣሾቼን እንዳታነጋግሩ›› ያሉት አቡነ ጢሞቴዎስ ቋሚ ሲኖዶሱ በጉዳዩ ላይ እንዳይወያይ ማከላከላቸው ተሰምቷል
 • በተቃውሞው የተበሳጩት ሊቀ ጳጳሱ ራሳቸውን ስተው እንደነበር ተጠቁሟል
 • ‹‹አልፈው በመቃብራቸው ላይ መሣቅ እንፈልጋለን›› – የጥላቻው ምሬት
 • ‹‹በተራዘመው መርሐ ግብር ሳቢያ የተጨመረው በጀት ለብክነት እየተዳረገ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
ዛሬ ጠዋት ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያመሩት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር ላይ የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው፡፡
ጥቁር የአገልግሎት ቀሚሳቸውንና መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ በሰልፍ ያመሩት ደቀ መዛሙርቱ፣ ወደ ቅጽሩ እንዳይዘልቁ በጥበቃ ሓላፊው በታገዱበት ነው የተቃውሞ ትዕይንታቸውን በማካሄድ ላይ ያሉት፡፡
ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ለመግባት የተፈቀደላቸው የደቀ መዛሙርቱ መማክርት መሪዎች/ተወካዮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች ጋራ እየተነጋገሩ እንዳሉ የተመለከተ ሲኾን ቋሚ ሲኖዶሱም በጉዳዩ ላይ እየመከረበት ስለመኾኑ፣ ‹‹በግቢው ጥበቃ ሓላፊ አቶ ብርሃኔ ኀይሉ ተነግሮናል፤›› ብለዋል፡፡

Tuesday, July 9, 2013

በዋልድባ ገዳም ግፉ እና እንግልቱ እንደቀጠለ ነው፥ አረማውያን የግፍ በትራቸውን በገዳማውያን አባቶች ላይ እየሰነዘሩ ነው!

ገዳማውያኑ ያለበደላቸው ለምን ይንገላቱ?

ከትናንት በስቲያ በደረሰን ሪፖርት እንደሚያመለክተው ላለፉት ጥቂት ወራቶች ሲደረግ እንደነበረው ታጣቂዎች በመነኮሳቱ ላይ ድብደባ፣ እንግልት፣ ስድብ እና እስራት እየፈጸሙባቸው ይገኛሉ። መንግሥት በዋልድባ ገዳም ላይ የሥኳር ፋብሪካ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ፣ የፖርክ ይዞታን እከልላለው ብሎ በመነሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሏት በርካታ ገዳማት በጥንታዊነቱ እና በታሪካዊነቱ የሚታወቀውን የዋልድባ (ዋሊ) ገዳም ለማፍረስ እና ገዳማውያኑን ለማሰደድ አረማውያን ደፋ ቀና ማለት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በገዳማውያኑ ላይ ሲደርስ በሰዎች ዘንድ ምንም ጥያቄ እና የመከላከል እርምጃ ባይደረግም ነገር ግን የቤተክርስቲያኒቱ መስራች መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ተዓምራትን እያሳየ በርካታ እንቅፋቶችን ቢፈጥርባቸውም፥ ነገርግን በእምቢተኛነት ተግዳሮቱን እንደቀጠለ ነው፥ ነገር ግን የልብሳቸውን አዳፋነት፣ የሰውነታቸውን ክሳት አይቶ ሳይፈራ ስቃይንና መከራን ያበዛባቸውን አረማዊ እንዳይፈሩ በትንቢተ ኢሳያስ ፶፩ ፥ ፯ ላይ የሰፈረውን ቃል መመልከት በቂ ነው፤ እንዲህ ይላል “ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።” ኢሳ. ፶፩ ፥ ፯

Thursday, July 4, 2013

IUEOTCFF (ዋልድባን እንታደግ) በሰሜን አሜሪካ ስፖርትና ባሕል ፌዴሬሽን ፴ኛ ዓመት በዓል ላይ በመገኘት ዝጅቶችን እያቀረበ ነው

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከያዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በርድ ስታዲዮም በሚደረገው የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባሕር ፌዴሬሽን 30ኛ ዓመት በዓል ላይ በመገኘት በዓሉ ላይ ለመገኘት ለሚመጡት ኢትዮጵያውያን ግንዛቤት በማስጨበጥ እና ተቋሙን ለማጠናከር የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር ከሰኔ ፳፭ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓም (June 30 – July 6, 2013) የሚቀጥል ሲሆን በበዓሉም ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከመላው ዓለም የሚገኙበት ሲሆን ምዕመናን፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጆች፣ የቤተክርስቲያኒቷ ወዳጆች በርካታ እርዳታዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል እያበረከቱም ነው ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ዘወትር የማያልቅበትን በረከቱን ለምዕማናን እንዲያበዛልን እየተመኘን በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ዝግጅቱ ስለሚቀጥል በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በትብብራችሁ እንትበረቱ እና ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከጥፋት፣ ገዳማት አድባራቱን ከምዝበራ፣ ንጹሐን መነኮሳትና መነኮሳይትን ከስደት፣ ዋልድባን ከመፈታት እንድንታደግ አደራ እንላለን።
በዚህ በዓል ላይ እጅግ በሚያኮራ እና በሚያስደስት ፍፁም የቤተክርስቲያን ቅንዓት ጫማዎችን በመጥረግ (ሊስትሮ)

በማስጠረግ በርካታ ክርስቲያኖች ትብራቸውን እያደረጉ ነው በዚህም ቤተክርስያናቸውን ከጥፋት ለመታደግ፣ ዋልድባን እና የተለያዩ ገዳማትን ለመታደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ተባባሪነታቸው አሳይተዋል እና በመጨረሻው ዘመን አምላከ ቅዱሳን በክብር በሚገለጽበት ጊዜ “ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን” ተብለው ከሚጠሩት ከቅዱሳን ወገን እንዲደምርልን ለአምላካችን ዘወትር በጸሎት እናመለክታለን።


በመጨረሻ በበዓሉ መጨረሻ ላይ ማለትም አርብ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (July 5, 2013) 4:00 PM. ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እና የመንግሥት ተግዳሮት በሚል ርዕስ ዝግጅት ስለሚኖረን በድንኳን ቁጥር 41 ፊትለፊት በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።   

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!