Saturday, September 28, 2013

ነገረ ወልድ

ነገረ፡ ወልድ።
በቅዱስ ኤፍሬም። ፫፻፶ ዓ. ም.  


ቸሩ እግዚአብሔር “አብራም” ብሎ ጠራው።
ከዘመዶችህ ተለይና
እኔ ወደማሳይህ ምድር ተሰደድ አለው።

አብራም ከካራን ወጣ
በ፸፭ አመቱ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደከነዓን ወረደ።
ከዘመዶቹም ካገሩም ይልቅ
ልቡ እግዚአብሔርን ወደደ።

ከካራን ሲወጣ
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሊጠብቅ
“ሀ” ብሎ ጀመረ።
እግዚአብሔርም አየ፡ ትእዛዝ ጨመረ።
አረጋዊው አብራም
በብርቱ ፈተናወች ታጠረ።

Wednesday, September 18, 2013

በምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት የተቃጠለው የዳገት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ በዳገት ቀበሌ የሚገኘው የዳገት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በሚያዚያ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ከቀኑ 11 ሰዓት (5:00 PM.) ላይ ባልታወቁ ሰዎች የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል፥ ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ በዚሁ መምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት ውስጥ በጠቅላላው ወደ 4 የሚጠጉ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት የቃጠሎ አደጋ እንደደረሰባቸው ከሥፍራው የደረሰን ሪፖርት ያሳያል።
በዚሁ የምሥራቅ ጎጃም ዞን በርካቶች የመቃጠል አደጋ ደርሶባቸዋል ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው
፩ኛ/ የአንጋታ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓም ተቃጥሏል
፪ኛ/ የዳገት እየሱስ ሚያዚያ 11 ቀን 2005 ዓም
፫ኛ/ ደረባን ሕዳር 8 ቀን 2005 ዓም
፬ኛ/ የደማሞ ማርያም ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓም
፭ኛ/ የሰንደባ ሚካኤል ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓም
፮ኛ/ ጥንታዊው የአንበር ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ኅዳር 13 ቀን 2005 ዓም የቃጠሎ አደጋ ሲደርስባቸው ሃላፊነት የወሰደ ወይንም
ችግሩ ደግሞ እንዳይከሰት ለማድረግ የሞከረ የመንግሥት አካላትም የሉም። የአካባቢው ነዋሪም ቀን ቀን ሦስት ሰው ማታ ማታ አራት ሰው በመሆን ጥበቃ ያደርጋሉ ነገር ግን ይሄ በቂ ሊሆን አልቻለም።
ሰላም ባለበት፣ የሃገር ልዕልና ባለበት የዜጎች መብት በሚከበርት ሃገር እንዴት የእምነት ቦታዎች በተለያየ ጊዜ እንዲህ ቃጠሎ ሊደርስባቸው ይችላል ይህንን የክልልሉ መንግሥትም ጉዳዩን ከምንም አለመቁጠሩ፤ ነገሮች የበለጠ እንዲወሳሰቡ ሆነዋል

በሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ አድባራት፣ ገዳማት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶች ባለፉት 20 ዓመታት ሲቃጠሉ፣ ሲወድሙ ተመልክተናል ነገር ግን ቤተክህነቱ ምንም ሊያደርግ አልቻለም ወይንም የእምነቱ ተከታዮች ምንም ማድረግ አልቻሉም ወይንም አይመለከተንም ብለው ተቀምጠዋል። በጣም በእጅጉ የሚያስፈራው በቀጣይነት ክርስቲያኖች በየቦታቸው እየታደኒ አደጋ እንዳይደርስባቸው ስጋት አለን።
እምነታችንን እና ሃይማኖታችንን ነቅተን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን
እግዚአብሔር ይሁነን

Let's save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Tuesday, September 17, 2013

በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

  • መነኰሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው
  • አስተዳደሩ ለመነኰሳቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም
  • ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ብትውሉ አታድሩም!›› /ጥቃት ፈጻሚዎቹ/
Haro Wonchi Monasteryበደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ወንጪ ወረዳ ሐሮ ወንጪ ቀበሌ በሚገኘው የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ምሽት 5፡00 ላይ ወደ ገዳሙ ቅጽር በተወረወረው ቦምብ ነው፡፡
በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል – ‹‹ቢፈነዳም እርሱ ከልሎናልና ጉዳት አላደረሰብንም፡፡››

Sunday, September 8, 2013

የአክራሪነት ውንጀላ የተሰነዘረበት ማኅበረ ቅዱሳን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ሪፖርት/ክሥ ማቅረቡ ተጠቆመ

  • አክራሪነት ውንጀላው በ‹‹አገር አቀፍ የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ወቅት ማኅበሩንና አገልግሎቱን ከተቀበረ ፈንጂ ጋራ ያመሳሰለውና በአቶ ስብሓት ነጋ አጽንዖት የተሰጠው የአባ ዮናስ ጥቆማ ነው፤ ጥቆማው የተሰማው ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሑፍ ተከትሎ አቶ በረከት ስምዖን በመሩት የውይይት መድረክ ነው፡፡ 
ማኅበረ ቅዱሳን
ማኅበረ ቅዱሳን
  • ከሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ተወክለው የመጡት አባ ዮናስ÷ ማኅበሩን በስም ለይተው ባይጠቅሱም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ለቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚሰጠው ሥልጠና ትውልዱን ‹አክራሪነትን ያደርጋል› በማለት፣ በእነርሱም በኩል የመንግሥትንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ይካሄዳል ያሉት እንቅስቃሴ ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረ ትልቁ የአክራሪነት ፈንጂ›› እንደኾነ ጠቅሰው ማኅበሩን ቅ/ሲኖዶስ አጽድቆ በሰጠው የአገልግሎት ድርሻው በመጠቆም በከፍተኛ ደረጃ ወንጅለዋል፡፡
  • ለአባ ዮናስ በቂምና ጥላቻ የተሞላ ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ያላገኙ የውይይቱ ተሳታፊ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከስብሰባው በኋላ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ ሓላፊዎች በተለይ ከሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ጋራ ከፍተኛ ሙግት ገጥመው ታይተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና የሰጠችውና በመዋቅሯ የምትቆጣጠረው ማኅበርና አገልግሎቱ ከአክራሪነት ጋራ መያያዙና ትርጉሙ በቀላሉ እንደማይታይ ያመለከቱት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ሚኒስቴሩ ማኅበሩን ጠርቶ ለማነጋገርና ለመመካከር ሞክሮ እንደኾነ ጠይቀዋል፤ ጉዳዩንም መንበረ ፓትርያርኩ በጥብቅ ይዞ እንደሚነጋገርበት አሳስበዋቸዋል ተብሏል፡፡

ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም: በዋልድባ ገዳም እና በ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ የተፈጠሩ ዝንባሌዎችን ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ላሉት አክራሪነት/ጽንፈኝነት›› በጉልሕ ማሳያነት አቀረቡ

  • ‹‹በስደተኛው ሲኖዶስ የተሸፈኑና በማኅበረ ቅዱሳን የመሸጉ የትምክህት ኀይሎች የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል››
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባዘጋጁትና ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በተካሄደው ‹‹አገር አቀፍ የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ውይይት ከተካሄደባቸው ጽሑፎች መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡
Dr Shiferaw Teklemariam,Minster of Minstry of Federal Affairs
ፎቶ: ሽግግር ሃገራዊ መጽሔት
በሰባት ንኡሳን አርእስት ተከፋፍሎ በስፋት የቀረበው ጽሑፋቸው÷ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥት አንጻር እንዴት እንደሚታይ፣ በአገራችን ይታያሉ ያሏቸውን የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች፣ አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን የማስፋፊያ ስልቶችን፣ የአክራሪ/ጽንፈኛ ኃይሎች መነሻና መድረሻ ምስጢር፣ ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረጉ የአክራሪነት አደጋዎች እና አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ መሠራት ይገባቸዋል ያሏቸው ስድስት የመፍትሔ ሐሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡
በሚኒስትሩ ጽሑፍ አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቃል የተበየነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ ይኸውም አክራሪነት/ጽንፈኝነት÷ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፯ ንኡስ አንቀጽ ፫ ዜጎች የፈለጉትን እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው የተደነገገውን በመተላለፍ የሃይማኖትና እምነት ነጻነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፭ ስለ እኩልነት መብት በሚደነግጋቸው ንኡሳን አንቀጾች በሃይማኖቶች መካከል የማበላለጥ ጉዳይ እንደማይኖር የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጣስ የሃይማኖት እኩልነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ስለ መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመፃረር መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመሥረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡
አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖቶች ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ገጽታም ያለውና የሚመጋገብ እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም የሚል ሃይማኖትና አገር ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ እንደየአገሩ የሕዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪክ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት ተጋላጭነት የመላቀቅ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት የብዝሃነት አያያዝ ጥበቃ ዋስትና ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

Thursday, September 5, 2013

ስብሓት ነጋ ጥፋቷን ስለሚመኙላት ቤተ ክርስቲያንና መግደያ ብትር ሊያደርጉት ስለሞከሩት ማኅበረ ቅዱሳን ይወተውታሉ

  • ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

Ethio-Mihdar Flag of the day
‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም
/አቶ ስብሓት ነጋ/
(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡